@mykeysjourney: አንድ ጊዜ ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ሲያስተምሩ፣ "መርሳት እግዚአብሔር የሰጠን ጸጋ ነው" ማለታቸውን አስታውሳለሁ። በወቅቱ ንግግራቸው እንግዳ ሆኖብኝ ፤"እንዴት! መርሳትም ጸጋ ሊሆን ይችላል?" በማለት እጅግ ተደንቄ ነበር። ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስበው ግን፣ እውነትም መርሳት ትልቅ ጸጋ ነው። ከወዳጆቼ ጋር ተሰብስበን ስንጫወት፣ መሃል ላይ ድንገት ሐሳብ ጠልፎኝ ጭልጥ እላለሁ። "ያለብኝን ሁሉ አስቸጋሪ ነገር ረስቼ ነው እንዴ አሁን ከልቤ የምስቀው?" ብዬ ራሴን እጠይቃለሁ። አንዳንዴ የረሳሁትና አልተፈታም ብዬ የማሰብውንም የትላንትንም ሸክም መልሼ ላስበው ስሞክር፣ አእምሮዬን ይከብደውና "የራሱ ጉዳይ" ብዬ እተወዋለሁ። ነገር ግን፣ ፈጽሞ የማይፈታ የሚመስል፣ መቆሚያ መቀመጫ የሚያሳጣ ጭንቀት ሲበረታብኝ፣ መሸሸጊያዬን አውቀዋለሁ፤ በቀጥታ ወደ ቤተክርስቲያን እሄዳለሁ። በአንድ ወቅት የኢንስታግራም ገጼ 'Highlight' ላይ "Emergency" የሚል ማህደር ከፍቼ አንዲት አጭር ቪዲዮ አስቀምጬ ነበር። ነፍሳችን ስትዝል፣ እግዚአብሔር "ብርታት" በተባለ አምቡላንስ ጠልፎ ወደ ቤተክርስቲያን ያመጣንና (First Aid) ይሰጠናል። ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ሆስፒታል አይደለችም እንዴ? እጅግ የሚገርመው ደግሞ፣ እዚያ ስንደርስ "መርሳት" የሚባል ማስታገሻ ይሰጠናል፤ ያንን መድኃኒት ከዋጥን በኋላ፣ የተቀረው ውጣ ውረድ ሁሉ በእግዚአብሔር ጊዜና ጥበብ ቀስ በቀስ ሲስተካከል ሰላም ሆነን እንመለከታለን። ከእነዚህ የነፍስ ድንገተኛ ሆስፒታሎች መካከል፣ ሐመረ ኖኅ እንጦጦ ኪዳነምህረት ገዳም አንዷ ናት። በዚያች ስፍራ ያለችው ሐኪም ደግሞ እጅግ ልዩ ናት፤ ስሟ ራሱ ፈውስ የሆነ፣ ምሕረትን የምታድል "ኪዳነ ምሕረት"! ወደ ሆስፒታል ሄዳችሁ፣ የምታክማችሁ ሐኪም የገዛ እናታችሁ ብትሆን ምን ዓይነት መረጋጋት እንደሚሰማችሁ አስቡት! መልካም ጾመ ፍልሰታ ሚክያስ ልየው | Mikiyas Liyew ነሐሴ ፬ - ፳፻፲፰ ዓ.ም ምሽት 7:54 አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ Sound Source :- TikTok page of Dessie Medhanealem School. #Ethiopia #Addisababa #Ethiopiaorthodoxchurch #Entotokidanemihret #shotoniphone
ሚክያስ ልየው | MIKIYAS LIYEW
Region: ET
Tuesday 11 August 2026 15:17:01 GMT
Music
Download
Comments
abela :
እኔ ብቻ ከቤትሽ እርቄ ሐጢያትን በሐጢያት እየደገምኩት ሰላም ያጣሁት እናቴ ኪዳነምሕረት ልቦና ስጪኝ🙏🙏🙏🙏
2026-08-12 14:15:13
112
ሆሴዕ :
የኔ እናት ብቻ
የኔ መድሀኒት ብቻ
የኔ የክፉቀን ደራሼ
ብቻ ትመሥለኝ ነበር ለካ ለሁላችንም ናት 🥰🥰🥰🥰
2026-08-12 20:26:00
11
shalom :
እውነት ነዉ ማርያምዬ ባትኖርልን ምን እንሆን ነበር
2026-08-12 05:18:44
43
የኪዳነምህረት ወዳጅ :
የኔ ኪዳነምህረት
2026-08-12 14:23:52
5
naniy :
የኔ መአዛ ማርያም
2026-08-11 21:04:18
18
Tirusew Edma :
Amen 🙏
2026-08-12 18:27:21
1
clothes by fre :
This is me kidane meheret ❤️
2026-08-12 09:31:07
4
የማርያም 🦋 :
ewent new
2026-08-11 18:14:45
12
Euphrates ❤️ :
True🙏🙏
2026-08-12 14:10:49
3
AB Man:-♍️⚽️🎶🎧 :
the power of ስምሽን ስጠራው ማርያም ማር በምድር ያም በሰማይ🙏🙏🙏🥰🥰
2026-09-09 08:18:28
2
my life :
enate🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-08-12 05:10:47
2
AMIOPIA JUTRI 📈 :
ገና ደጇን ስረግጥ 😔
2026-08-17 12:08:29
4
Kali ✨⛪️ :
እግዚአብሔር በሕይወታችን ከሰጠንትልቁ ስጦታ አንቺ ነሽ እኮ እናቴ ማርያም🥰 ተመስገን
2026-08-14 14:05:39
5
🌸𝓱𝓪𝓷𝓲𝓽𝓪🌸 :
mom♥️
2026-08-17 09:06:35
7
Melu421 :
eweyyyyyyyy🥰🥰🥰
2026-08-11 17:34:16
4
🌸Bebe🌸ቤቤ🌸 :
የሚያውቀው ያውቀዋል❤
2026-09-19 12:44:38
1
btgn21 :
maryam🥰
2026-08-12 14:32:11
5
Kal :
ኪዳነምህረት ❤️❤️❤️
2026-08-12 09:56:19
3
haylush ሞተር :
1616161616161616
1616161616161616🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-08-12 19:09:43
1
muletesfa :
የእንጦጦዋ ንግስት ኪዳነምህረት እናቴ🥰🥰🥰🙏🙏🙏
2026-08-12 20:16:19
1
Leul የ ኪዲዬ❤️ :
እናቴ የኔ ሁሉ ነጌሬ እወድሻለዉ❤️🙏🥰
2026-08-12 09:36:28
2
Kidist🌸 :
The caption🥹💯
2026-08-12 03:42:24
3
Sitotaye :
የልቤን ሞላችልኝ ሰላም ሰጠችኝ
2026-08-12 07:39:34
3
user2761263501625 :
Yne werq enat
2026-09-24 13:58:17
0
𝔂𝓪𝓵𝓯𝓪𝓵 :
2026-08-13 16:47:37
0
To see more videos from user @mykeysjourney, please go to the Tikwm
homepage.