@dapurnajib: dah lams ga masak krecek gini🫰🏻 #cooking #masakanindonesia #cookingathome #resepmudah

dapurnajib
dapurnajib
Open In TikTok:
Region: ID
Wednesday 12 August 2026 01:56:16 GMT
9373
120
4
10

Music

Download

Comments

dapursakhiy
dapursakhiy :
selaluu medok bumbuny🤤🤤🤤
2026-08-12 03:00:29
0
novie_mpie7
🇻𝖎𝖊𝖊 :
Spil resep nya dong ka 😁
2026-08-12 03:41:00
0
cintaaakamuuu
kauaja :
Spil resep kk ngiler🤤
2026-08-12 05:36:55
0
miraangguns
Mira ✨ :
Nasi mana nasiii 🤤
2026-08-12 11:35:30
0
To see more videos from user @dapurnajib, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


"ህፃናቱን መሬት ላይ አስተኝተሽ ከእኔ ጋር አልጋ ላይ ተኚ!" አለኝ። ልጆቼ በረሃብ እንዳይሞቱብኝና ጎዳና ላይ እንዳንወድቅ ስል እሺ አልኩት... ጎረቤት "ባለጌ ነሽ" እያለ በስድብ ሲያሸማቅቀኝና ሲያማኝ የነበረው፣ ውስጤ የተሸከመውን ሲኦል ሳያውቅ ነበር!» 💔😭 ይህ ልብን በሀዘን የሚሰብርና ማህበረሰባችን ያለበትን የግብዝነት ገጽታ እርቃኑን የሚያሳይ እውነተኛ ታሪክ የ22 ዓመቷ ወጣት የመንታ ልጆች እናት መቅደስ ተስፋዬ ናት። መቅደስ ገና በጨቅላነቷ የወላጆቿ ፍቅር ተነፍጓታል። በሰባት ዓመቷ ለማያውቋት አረጋውያን ተሰጥታ በዱርና በበረሃ የከብት እረኛ ሆና ተሰቃየች፤ በዛ ለጋ ዕድሜዋ ከሚሊሻዎች አስገድዶ መድፈር ጥቃት ተአምር ሆኖ እያመለጠች አደገች። ትምህርት ፍለጋ ወደ ከተማ ብትመጣም ያገኘችው የከፋ የቤት ውስጥ ባርነት ነበር። «አረብ አገር እልክሻለሁ» ባላት ሰው ቤት ሙሉ ዓመት ያለ ምንም ክፍያ ደክማ መጨረሻው ባዶ እጇን ወደ ውጭ መጣል ሆነ። አድራሻ በማታውቅባት አዲስ አበባ ለሁለት ዓመታት ባላለቁ የኮንዶሚኒየም ፍርስራሾች ውስጥ በረሃብ፣ በብርድና በጎዳና ላይ ወድቃ ኖረች። ከዛ ሁሉ ሰቆቃ በኋላ ከአንድ የስጋ ቤት ባለቤት ጋር በፍቅር ወደቀች። ፍቅርና እንክብካቤ ያገኘች መስሏት ሳለች፣ የሶስት ወር ነፍሰጡር መሆኗን ስትነግረው ግን የገጠማት ምላሽ አስደንጋጭ ነበር፦ «"ያምሻል እንዴ! እኔ ገጠር የታጨችልኝ እጮኛ አለችኝ፤ ይሄ ልጅ መውረድ አለበት! ጎዳና ወጥተሽ ብትለምኚ እንኳን እኔ አላውቅሽም" ብሎ ወረወረኝ። ሆስፒታል ወስዶ ውጤቱ ሲረጋገጥ በድንጋጤ አፍንጫው በደም እስኪታፈን ድረስ ነሰረው። እኔ ግን ፅንሱን ማስወረድ ነፍስ መግደል ነው ብዬ ልጆቼን ለማዳን ወሰንኩ!» ትላለች። መከራዋ የከፋው ግን በማህፀኗ ያለው አንድ ልጅ ሳይሆን መንታ መሆኑን ስታውቅ ነበር። በድብቅ እየሰራች በነበረችበት መጠጥ ቤት ሰዎች ኳስ እየተመለከቱ እርጉዝ መሆኗን ሳያውቁ «አንቺ ቦርጭሽን ቀንሺ» እያሉ ሆዷን ሲመቷት በድንጋጤ ታለቅስ ነበር። በመጨረሻም የሆስፒታል ጓንት መግዣ 200 ብር አጥታ እያለቀሰች፣ ያለ ማንም ረዳት በስምንት ወሯ መንታ ልጆቿን ተገላገለች። አራስ ቤት የሚበላ ገንፎና ወተት አጥታ የቤተክርስቲያን ሰዎች ባዋጡላት የጣሳ ወተት ልጆቿን መገበች። ነገር ግን ከሁሉ በላይ አንጀት የሚበላውና እጅግ አሳዛኙ ፈተና የተከሰተው ልጆቿን ለማሳደግ በነበራት ብርቱ ትግል ወቅት ነበር፦ ልጆቿ የተመጣጠነ ምግብና ፀሐይ አጥተው እግራቸው ታጥፎ መቆም አቅቷቸው ነበር። ስራ አጥታ፣ የቤት ኪራይ ተቸግራና የልጆቿ ወተት አልቆ በከፋ አጣብቂኝ ውስጥ ወደቀች። በዚህ ወቅት አንድ ትልቅ ባለትዳር ሰው የተቸገረችበትን አጋጣሚ ተጠቅሞ ክብሯንና ሴትነቷን ዋጋ እንድትከፍል አስገደዳት። «ያ ሰውዬ አይዞሽ እያለ ይቀርበኝ ነበር። መጨረሻ ላይ ግን ወይ ልጆቼን ይዤ ጎዳና መውጣት አልያም ከእርሱ ጋር መተኛት ግድ ሆነብኝ። ህፃናቱን መሬት ላይ አስተኝቼ እኔ ከእርሱ ጋር አልጋ ላይ እተኛለሁ... የልጆቼን የቤት ኪራይና ወተት የሚሸፍነው በዚህ መንገድ ነበር። ጎረቤቶቼ ግን "አንቺ ባለጌ ነሽ" እያሉ ያሙኝና ይሰድቡኝ ነበር። እኔ ለልጆቼ ህይወት ስል ክብሬን መስዋዕት አድርጌ እንደኖርኩ ማንም አላወቀልኝም!» ስትል ያንን የህይወቷን እጅግ መራራ ምዕራፍ በዕንባ ታስታውሳለች። ይህች ብርቱ እናት ልጆቿን ከሞት ለማዳን አንዱን ከፊት አንዱን ከኋላ አዝላ የባህር ዛፍ ዘይት በየመንደሩ እየዞረች ሸጣለች። ዛሬ ልጆቿ አራት ዓመት ሊሞላቸው ነው፤ አባታቸውን አይተውት አያውቁም። ስልክ ሲጠራ «እማዬ አባዬ ነው?» እያሉ ሲጠይቋት ልቧ በሀዘን ይደማል። ዛሬ መቅደስ የሰው ቤት ልብስ እያጠበች የቀን ጉርስ ብቻ ነው የምታገኘው። የጠየቀችው ምፅዋት አይደለም፤ እርሷ የተነፈገችውን የትምህርት ዕድል ልጆቿ እንዲያገኙና ሰርታ የምታሳድግበት አነስተኛ የስራ መነሻ ካፒታል ብቻ ነው። «ጎዳና ወጥቼ ብለምንም ልጆቼን አልጥልም ብዬ ነው የወለድኳቸው» የምትለው መቅደስ፣ ዛሬም የነገ ተስፋቸውን ብሩህ ለማድረግ የሁላችንንም እጅ ትሻለች። ማህበረሰቡ እንደሚያደርገው በሩቁ ቆመን ከመፍረድ ይልቅ፣ የዚህችን የቆረጠች እናትና የንፁሃን መንታ ልጆቿን እንባ ለማበስ ሁላችንም አቅማችን በፈቀደው መጠን ከጎኗ እንቁም! ❤️🙏

About