@dizinova2026: Usta Balıkçı (Türkçe Dublajlı) - Bölüm 5 #koreandrama #shorts #viral_video #koredizi #keşfett

Dizi Nova 🎬🍿
Dizi Nova 🎬🍿
Open In TikTok:
Region: TR
Wednesday 12 August 2026 09:28:34 GMT
7715
123
1
2

Music

Download

Comments

sunshine.aksesuar
Qima :
❤️❤️❤️
2026-08-12 12:50:31
0
To see more videos from user @dizinova2026, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

አፈንዲ ሙተቂ ---- በአማርኛ ቋንቋ የነቢዩ ሙሐመድን የህይወት ታሪክ የሚተርክ ቀዳሚ መጽሐፍ የጻፉት ሐጂ ሙሐመድ ሣኒ ሐቢብ ሲሆኑ ዘመኑ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1961 ነው። በተመሳሳይ ርእስ የተጻፈው ሁለተኛ መጽሐፍ ደግሞ በዚህ ፎቶ ላይ የምትመለከቱት ነው። የመጽሐፉ ደራሲ ወልደገብርኤል አሰጌ ይባላሉ። መጽሐፉ የታተመበት ዘመን ደግሞ 1965 ነው።  በዚህ መጽሐፍ ከተጻፈው ታሪክ በላይ በብዙዎች ዘንድ የተደነቀው የደራሲው ነፃ እና ሚዛናዊ የሆነ አቀራረብ ነው። አውሮጳዊያንና አሜሪካዊያን እንኳ የነቢዩን ታሪክ በትክክለኛው መልኩ ለመጻፍ አዕምሮአቸው በሚለግምበት ዘመን በሀገራችን ውስጥ እንዲህ ዓይነት ሚዛናዊ ድርሰት ተጽፎ ነበር። ደራሲው መጽሐፉን ከማሳተማቸው በፊት ረቂቁን ለሁለት ታላላቅ ዑለማዎቻችን አሳይተው ነበር። እነዚያ ዑለማ ሐጂ ዩሱፍ ዐብዱራሕማን ገራድ እና ሐጂ ሙሐመድ ሣኒ ሐቢብ ናቸው። ሁለቱ ዑለማ ረቂቁን ካነበቡ በኋላ በደራሲው ሚዛናዊነት ተገርመው በጻፉት መቅድም ውስጥ የሚከተለውን ምስክርነት ሰጥተዋል።
አፈንዲ ሙተቂ ---- በአማርኛ ቋንቋ የነቢዩ ሙሐመድን የህይወት ታሪክ የሚተርክ ቀዳሚ መጽሐፍ የጻፉት ሐጂ ሙሐመድ ሣኒ ሐቢብ ሲሆኑ ዘመኑ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1961 ነው። በተመሳሳይ ርእስ የተጻፈው ሁለተኛ መጽሐፍ ደግሞ በዚህ ፎቶ ላይ የምትመለከቱት ነው። የመጽሐፉ ደራሲ ወልደገብርኤል አሰጌ ይባላሉ። መጽሐፉ የታተመበት ዘመን ደግሞ 1965 ነው። በዚህ መጽሐፍ ከተጻፈው ታሪክ በላይ በብዙዎች ዘንድ የተደነቀው የደራሲው ነፃ እና ሚዛናዊ የሆነ አቀራረብ ነው። አውሮጳዊያንና አሜሪካዊያን እንኳ የነቢዩን ታሪክ በትክክለኛው መልኩ ለመጻፍ አዕምሮአቸው በሚለግምበት ዘመን በሀገራችን ውስጥ እንዲህ ዓይነት ሚዛናዊ ድርሰት ተጽፎ ነበር። ደራሲው መጽሐፉን ከማሳተማቸው በፊት ረቂቁን ለሁለት ታላላቅ ዑለማዎቻችን አሳይተው ነበር። እነዚያ ዑለማ ሐጂ ዩሱፍ ዐብዱራሕማን ገራድ እና ሐጂ ሙሐመድ ሣኒ ሐቢብ ናቸው። ሁለቱ ዑለማ ረቂቁን ካነበቡ በኋላ በደራሲው ሚዛናዊነት ተገርመው በጻፉት መቅድም ውስጥ የሚከተለውን ምስክርነት ሰጥተዋል። "መጽሐፉን ከተመለከትን በኋላ እንደተረዳነው ደራሲው ምንም እንኳ በግል እምነታቸው ክርስቲያን ቢሆኑም የታሪክን ትክክለኛ ዓላማ ተከትለው አድልዎ በሌለበት ቅን መንፈስ ተመርተው እውነተኛውን ተግባር በመመራመርና የህሊናቸውን እውነተኛ ፍርድ በመስጠት ያደረጉት ሙከራና ያሳዩት አርቆ አስተዋይነት ለሀገራቸው አንድነት ቅን አስተሳሰባቸውን ከማረጋገጣቸውም በላይ በሁለቱ ሀይማኖቶች በሚያምኑ ኢትዮጵያዊያን መካከል የመቀራረብንና የመግባባትን መንፈስ የሚያፋፋ አንድነትን ለማጠንከር የሚረዳ መሆኑን ለመረዳት ቻልን" ሐጂ ዩሱፍ ዐብዱራሕማን (የደጃች ዑመር ሰመተር ት/ቤት ዲሬክተር) ሓጂ ሙሐመድ ሣኒ ሐቢብ (የመስጊድ አልአንወር አሰጋጅ) ---- ይህንን መጽሐፍ በቅድሚያ ያነበብኩት በልጅነቴ (በ1980 ገደማ) ነው። ሁለቱ ዑለማ በአጽንኦት የጠቀሱትን የደራሲውን ሚዛናዊነት በደንብ ተረድቼ ለመጽሐፉ አድናቆቴን የሰጠሁት ግን በ1990 የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሳለሁ በድጋሚ ባነበብኩበት ወቅት ነው። በርግጥም መጽሐፉ በገጽ ብዛቱ አነስተኛ ቢሆንም ታሪክን መጻፍ የሚፈልግ ሁሉ እንደ ሞዴል ሊገለገልበት የሚገባ ድርሰት ነው። ------ ጸሐፊው ወልደገብርኤል አሰጌ በአሁኑ ወቅት በሰሜን አሜሪካ እየኖሩ ነው። በቅርቡ ስለዚህ መጽሐፍ የተጠየቁበት ቃለ-ምልልስ በቪዲዮ ተለቆ አይተነዋል። በYouTube ላይ ብትፈልጉት ልታገኙት ትችላላችሁ። ----- አፈንዲ ሙተቂ ሃምሌ 9/2017 ----- (መጽሐፉን በPDF የምትጠይቁ ሰዎች ላስተናግዳችሁ አልችልም። እኔ ራሴ ጸሐፊ ሆኜ የሌሎችን መጻሕፍት በPDF ካሰራጨሁ ነገር ተበላሸ ማለት ነው። መጻሕፍትን በPDF መበተን የCopyright ህጉ ይከለክላል። ጸሐፊው በSoftcoy እንዲሰራጭ ፈቃደኛ ከሆነ፣ ወይንም መጽሐፉ 70 ዓመት ከሞላው ብቻ ነው በPDF ማሰራጨት የሚቻለው)

About