@musictube369: ፍቅር አያልቅበት 🤒 ✍️ያኔ አዲስ ዘፈን በወጣ ቁጥር ቆመን እንሰማባቸው ከነበሩ ሙዚቃ ቤቶች ውስጥ :-ዋሊያ ሙዚቃ ቤት (ኢትዮ ሙዚቃ ቤት አቅራቢያ)፣ ገነት ሙዚቃ ቤት (መርካቶ)፣ አክሱም ሙዚቃ ቤት (ሲኒማ አዲስ ከተማ ፊት ለፊት)፣ የምስራች ሙዚቃ ቤት (ቁጭራ)፣ ብሔራዊ ሙዚቃ ቤት (ከሶል ኩኩ አጠገብ)፣ ቮይስ ሙዚቃ ቤት (ሰባተኛ)፣ ሶላር ሙዚቃ ቤት (ከመስጊድ መብራት ወረድ ብሎ) አውቶቢስ ተራ አካባቢ:- ናይል መዚቃ ቤት፣ ኢቲዮ ሙዚቃ ቤት ፣ አምባሰል ሙዚቃ ቤት ፣ ማርስ ሙዚቃ ቤት ፣ ዜድ ሙዚቃ ቤት ። አመዴ ገቢያ አካባቢ:- ሱፐር ሶኒክ ሙዚቃ ቤት ፣ ያሬድ ሙዚቃ ቤት ፣ ሳምሶን ሙዚቃ ቤት ። አንዋር መስጊድ አካባቢ:- ሴንትራል ሙዚቃ ቤት ፣ አለም ሙዚቃ ቤት ፣ ኤሌክትራ ሙዚቃ ቤት ፣ ሶልኩኩ ሙዚቃ ቤት ፣ ማራቶን ሙዚቃ ቤት .... የሙዚቃ ፕሮውዲሰሮቹ ....የኢትዮጵያ ሙዚቃ ባለውለታ ናቸው 🙌🥰 ✨ውድ ቤተሰቦቼ የሰው ልጅ በትዝታ ማዕበል ወደ ኋላ ተጉዞ የሕይወቱን ወርቃማ ዘመናት ሲያስታውስ፣ በልቡ ውስጥ ትልቅ ሥፍራ ይዘው የሚነሱት በወቅቱ ይደመጡ የነበሩ የሙዚቃ ዜማዎች ናቸው። በኢትዮጵያ የዘመናዊ ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ከአሥራ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ስድስት እስከ አሥራ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሰባት ያሉት ዓመታት፣ በርካታ ድንቅ አልበሞች የፈሰሱበት ብቻ ሳይሆን፣ ዛሬም ድረስ በነፍሳችን ውስጥ ሕያው ሆነው የሚደመጡ ዘላለማዊ ዜማዎች የፈለቁበት ልዩ የጥበብ ምዕራፍ ነበር። እነዚያ ዓመታት የኛ ዘመን እውነተኛ ድምቀቶችና የትዝታ ማኅደሮች ነበሩ። ያንን ስሜትና የሙዚቃ ማዕበል ወደ ኋላ መለስ ብለን ስንቃኘው፣ እያንዳንዱ ዜማ የየራሳችሁን የሕይወት ታሪክ አብሮን የኖረ የነፍስ እረኛ ይመስላል፦ የአስቴር አወቀ ንጉሣዊ የድምፅ ልዕልና እና የጨጨሆ ትውስታ ታዲያበዚህ ወርቃማ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ የዘመናዊ ሙዚቃችን ንግሥት አስቴር አወቀ የምትይዘው ሥፍራ ሁልጊዜም ከፍ ያለ ነው። ከአገር ቤት እስከ አሜሪካና ለንደን መድረኮች ድረስ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ልብ የገዛችው አስቴር፣ በልዩ የስሜት መግለጫና የድምፅ ኃይሏ ትውልድን ስታንቀጠቅጥ ኖራለች። በተለይም በጎንደር የምትገኝን አንዲት ትንሽ ታሪካዊ ከተማ መነሻ በማድረግ የሰየመችውና በታላላቅ የሙዚቃ ሰዎች የተቀመረው “ጨጨሆ” የተሰኘው ድንቅ የሙዚቃ አልበሟ፣ ባህላዊውን የአገራችንን የዜማ ስልት ከዘመናዊ የሙዚቃ መሣሪያዎች ጋር ፍጹም አዋህዶ ያቀረበ የጥበብ ልዕልና መግለጫ ነው። አስቴር በዚሁ ነፍሱን ይማረውና ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በሁለት ሙዚቃዎቿ ላይ ከኤልያስ መልካ🙏🥺 ጋር በተጣመረችበት አልበሟ ላይ የሰዎችን የውስጥ ናፍቆት፣ ፍቅርና ትዝታ የምትቀሰቅስበት መንገድ ዛሬም ድረስ በሰዎች አእምሮ ውስጥ የማይደበዝዝ ሕያው አልማዝ ሆኖ እንዲቀጥል አድርጎታል። ልክ ዛሬ በአንዲት መልካም ወዳጄ ግብዣ መሰረት🥰 እንደጋበዝኳቹ በታላቁ ይልማ የተደረሰው "ፍቅር አያልቅበት" ሙዚቃ በእነዚያ ዓመታት የሙዚቃው ዓለም አዲስ የብርሃን ጮራ ሲፈነጥቅ፣ የፍቅር_አዲስ ነቃጥበብ “ልዑል አስወደደኝ” የሚለው ዜማ የብዙዎችን ልብ በንጹሕ ፍቅር አቅልጦ የነገሠበት ዘመን ነበር። ከዚሁ ጎን ለጎን፣ አሁንም ድረስ ሲሰማ አዲስ ሆኖ የሚንቀጠቀጠው የአበባና_ትዕግሥት “እርጅኝ አብሮ አደጌ” የሚለው ድንቅ የጥበብ ሥራ እና የመላው ትውልድ የልብ ጓደኛ የሆነው የታምራት_ደስታ “አንለያይም” የተሰኘው ዜማ የፍቅርን ጥልቅ ትርጉም በነፍሳችን ውስጥ በክብር ያሳረፉ ነበሩ። ላንፎቴን በ“ጓደኛ”፣ ሃይማኖት_ግርማ በ“ኦማሂሬ” እንዲሁም ማርሸ_ዳምጠው “አንተ የኔ” በሚለው ውብ ዜማዋ የዘመኑን ድባብ በናፍቆትና በደስታ አውደውታል። የድምፅ ከፍታ እና የማይረሱ የጥበብ ማኅተሞች👌 📌የአዳዲስ ድምፆችና የባህል ስልቶች መፈራረቅ የዘመኑ ሌላው ትልቅ መገለጫ ነበር። ሞኒካ_ሲሳይ በ“ተይ አትሚኝ” ውብ ሥራዋ፣ ጸደንያ_ገብረማርቆስ በ“ቢሰጠኝ” እንዲሁም ሸዋንዳኝ_ኃይሉ “ስቅ አለኝ” በሚለው የማይረሳ የጥበብ ሥራው የሰዎችን ስሜት ማርከውት ነበር። ሄኖክ_አበበ “ያምርባታል” በሚለው አልበሙ አደባባዩን በደስታና በውበት በድምቀት አጅቦታል። እነዚህ ሁሉ ታላላቅ የጥበብ ሰዎችና ያወጧቸው ድንቅ ሥራዎች፣ ተራ የዜማ ስብስቦች ሳይሆኑ ትላንትን ከአሁኑ ማንነታችን ጋር የሚያገናኙ፣ በውስጣችን ያሉትን ውብ ስሜቶች በሙሉ ቀስቅሰው የሚያሳዩ የኛ ዘመን እውነተኛ የነፍስ መስተዋቶች ናቸው። ይህንን ወርቃማ ዘመንና የሙዚቃ ትዝታ መለስ ብላችሁ ስታስቡ፣ በውስጣችሁ የሚቀሰቅሰው ስሜትና ናፍቆት ለሁሉም ወዳጆቻችሁ ሊደርስ የሚገባ ታላቅ የውስጥ ሀብት ነው🥰 📌ታዲያ ጥበብ ትላንትን በክብር ያቆያልና የጋራ ትዝታችንን ስናስብ ከላይ የጠቀስኳቸው አሳታሚዎች ሳያመሰግኑ ማለፍ ንፉግነት ነው በተለይም ደሞ ለበርካታ አመታት በክብር የዘለቀውን ታላቁን ኤሌክትራን እና ተሾመ ፀጋዬ (ተሼ ኤሌክትራ) የኤሌክትራ ሙዚቃ ቤት ባለቤት ለበርካታ አመታትአስቴር ከታንጎ አሻግሮ ብቸኛ ሊባል በሚችል ደረጃ የሀገር ውስጥ ዋልታ🙏 በተጨማሪም ወንድማማቾቹ ፍቃዱ ዋሪ እና አስራት ዋሪ ደግሞ የአምባሰል እና የኢትዮ ሙዚቃ ቤት ባለቤቶች ነበሩ ። የበርካታ ድምፃዊያን ስራዎችን ፕሮዲውስ አድርገው ለሙዚቃ ወዳጆች ጆሮ አድርሰዋል 🙏 🗣️ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡 Musictube #fyp #አስቴርአወቀ #ፍቅርአያልቅበት #musictube369 #ethiopianmusic
🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱️🅴
Region: ET
Thursday 13 August 2026 18:59:32 GMT
Music
Download
Comments
Andken ayele :
bewnet lezi track kal yelegnm
endet endi music perfect yehonal💯👌👌
2026-08-13 19:44:38
45
dagm jhon :
ይሄን ዘፈን ከኔ በላይ የተመሰጠበት የለም believe me.
2026-08-14 14:57:53
21
ተበቺሳ :
የበለጠ ከአስቱ አልበሞች ምወደው አልበም
2026-08-13 19:30:12
35
mihretu507 :
Negstua 👑👑 ✍️✍️✍️💔💔💔 thanks 🙏 so much music 🎶🎵 tube
2026-08-13 19:29:04
10
Tewodros183tedy :
እናመሰግናለን ሀብትሽ🥰🥰🥰🥰👍🙏!
2026-08-14 18:25:03
3
muzeyinjemal31 :
ይሄንን አልበም ኤላ ልጨርሰው ፈልጎ ነበር አልተስማሙም
2026-08-14 08:02:00
2
gold dish :
2003 mechem maresaw
2026-08-15 00:22:25
4
ኤሎራ በሱፋቃድ :
ይሄ አልበም ራሱን የቻል ትዝታ አለብኝ 🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-08-19 10:06:49
2
Makeda2121 :
አስቱዬ የልጅነት ትዝታዬ ዛሬም ከእኔው ጋር አለሽ ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
2026-08-18 23:21:37
1
ermi kebede :
ሁሎም የሚገርመኝ ሙዚቃ
2026-08-27 12:57:12
1
Sebawden Sultan Ahimd Sebawden :
አስቱ የፍቅር ሰው.🌹
2026-08-14 23:03:35
1
solkuku :
ማራቶን ሙዚቃ ቤትስ
2026-08-15 17:55:45
1
zelatan wingate :
astuka love🙆🙆😍😍😍😍😍👌👌👌
2026-08-14 19:09:31
1
Sammy :
ይህን ወር ይህን ብቻ እኮ ነው እያዳመጥኩ ያለሁት🥺❤️
2026-08-14 08:37:39
5
💕kuku19💕 :
ከልቡ ቃዚሙ ነው
2026-08-14 05:50:17
4
it's me😎 :
My Queen 👑🥰
2026-08-13 19:03:30
4
Abrham :
2026-08-13 19:03:00
1
ab decor shambu :
🎧
2026-08-14 18:18:42
1
Yafet Daniel :
Thank you so much for posting this masterpiece its one of my fav astu song
2026-08-13 20:47:25
5
Sammy :
ሁሌም አመስጋኝህ እና አድናቂህ ነኝ።
2026-08-14 08:42:07
1
mili :
ስሰማዉ ሆድ ሚብሰኝ ዘፈን😥
2026-08-14 13:51:40
1
alazar5282 :
ስፈልገው
2026-08-14 04:09:37
4
mili :
ሰዉ እንዳልተሰራ
ካንተ በቀር ለኔ🥺🥺🥺
2026-08-14 13:50:47
5
Z mallo :
For the caption 🫡🙏
2026-08-13 19:55:32
2
yaredahailu :
ayi aster geraminech eko
2026-08-13 20:56:17
2
To see more videos from user @musictube369, please go to the Tikwm
homepage.