@sr36377378: እህቶቻችን ለራሳችሁ ተጨነቁ! {ኖህ ዳንኤል} ትናንት ማታ ቲክቶክ ላይ እንደተለመደው “ስክሮል” እያደረግኩ Live ላይ ስለፌሚኒስቶች የሚወያዩ እህቶች አጋጠሙኝ። ሴቶቹ በዋነኝነት ፌሚኒስቶች ምን ያህል ባህላችንን፣ ትዳርንና ያረጀ ያፈጀ እሴታችንን እየናዱ እንደሆነ በምሬት ያወራሉ። በተለይ ወንድ ጠል መሆናቸውን ደጋግመው ይናገራሉ። አንዷማ እነዚህ ፌሚኒስቶች ምን ያህል የወንዶችን ስም እያጠፉ እንደሆነ ስትተነትን እኔ ወንድማችሁ እንባ ሁሉ ተናነቀኝ 😭 እነዚህ እህቶቻችን በሀገሪቱ ውስጥ በየቀኑ ስለሚሰሙት የሴቶች እንግልት፣ ጥቃትና ግድያ እንቅልፍ አጣን ሲሉ አልሰማናቸውም። ሴቶች እንደሎጥ ዘመን በሰልፈሪክ አሲድ ሲታጠቡ፣ ህፃናቶች በጉሩፕ ሲደፈሩ ጉዳዩ ከንክኗቸው ቤት ከፍተው ሲወያዩ አላየንም። ነገር ግን የሆነች ፌሚኒስት ነኝ የምትል ወጣት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ «ወንዶች እንዲህ ናቸው» ብላ ስትናገር፣ የእኛ ስሜት መጎዳት እንቅልፍ ያሳጣቸዋል! እንዴት ቢወዱን ነው ጃል! ደግሞ ስለባህላቸውም በጣም ይጨነቃሉ። የሴቶችን መራቢያ አካል በመርፌ ስለሚሰፋው አስቀያሚ ባህል ደፍረው ባይናገሩም የኢትዮጵያ ባህል በነዚህ ፌሚኒስቶች የህልውና አደጋ እንደገጠመው ያምናሉ። ሐገሪቱ ውስጥ የሙሽራ እጥረት ያለ ይመስል ትዳርን ሊያጠፉ መጡም ይሉናል። ብዙ ነገር ያሳስባቸዋል። በተለይ የኛ የወንዶች በጅምላ መፈረጅ ያስጨንቃቸዋል። ስለዚህ እዚህ ሚዲያ ላይ ለራሳቸው “Feminist” የሚል ስያሜን ሰጥተው የሚንቀሳቀሱትን ሴቶች ከፍ ዝቅ በማድረግ የባህል አቢዮት አስጠባቂ ሆነው እያገለገሉን ይገኛሉ። በስነ-ልቦና ጥናት Internalized Misogyny ወይም በተለምዶ "Pick-Me" Culture የሚባል ነገር አለ። በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ጨቋኝ ወይም የበላይ እንደሆነ የሚታሰብ አካል ሲኖርና ያንን ለመቀልበስ የሆኑ አቢዮተኞች ሲነሱ ከተጨቋኝ ወገን የሆኑ ጥቂት ሰዎች ከጨቋኙ አካል ጋር በመወገን «እኔ እንደ አብዮተኞቹ አይደለሁም፣ እኔ ታዛዥ ነኝ፣ እባካችሁ እኔ እነደነሱ ስላልሆንኩ ውደዱኝ» እያሉ ይመጣሉ። ይሄንን ነው ስም ማውጣት የማይሰለቻቸው ነጮች Pick-Me" Culture እያሉ የሚጠሩት። የጥቁሮች የነፃነት መብት ተሟጋቹ Malcom X በዘመኑ የነበሩትን ጥቁሮች "House Negro” እና “Field Negro” ብሎ ለሁለት ይከፍላቸዋል። ፊልድ ኔግሮ የሚላቸው አቢዮተኞቹን ሲሆን ሃውስ ኔግሮ ወይም (Uncle Tom) የሚላቸው ደግሞ ለገዢዎቻቸው ፍፁም ታማኝነት ያላቸውንና ገዢዎቻቸውን በጣም ከማክበራቸው የተነሳ እንደነሱ የሚለብሱና በነሱ አክሰንት የሚናገሩ እንዲሁም የበታችነታቸውን በደስታ የተቀበሉ ናቸው። ከዚያም አልፎ በባርነት ውስጥ ያለውን ጥቅምም ሊያስረዱ ይጋጋጣሉ። እነዚህ ወዶገብ ባሪያዎች በጣም ለአለቆቻቸው ከማሽቋለጣቸው ብዛት አለቃቸው ሲታመም ራሱ “ጌታችን ታመምን እንዴ?” ነው የሚሉት ይላል ማልኮም X 😀 እነዚህ ሴቶችም ከራሳቸው ጥቃት ይልቅ "የወንዶች ስም መጥፋት" እንቅልፍ ይነሳቸዋል። ባላቸው ፕላትፎርም ስንት ነገር መስራት ሲችሉ ስለፌሚኒዝም ታሪካዊ የስም አመጣጥና አስከፊነት ሌክቸር ሲሰጡ ያመሻሉ። እንዲህ አይነት ሴቶች በታሪክ ውስጥም ታይተዋል። በ1970ዎቹ አሜሪካ ውስጥ ሴቶች መብታቸውን ለማስከበር እጅግ ትንቅንቅ ውስጥ ይገቡ በነበረበት ዘመን በፎቶ ላይ የምታይዋት Phyllis Schlafly የተባለች ሴት ግን የሴቶች እኩል መብት ያረጋግጣል የገባለውን Equal Rights Amendment (ERA) ህግ እንዳይፀድቅ ትልቅ ዘመቻ ከፍታ በታሪክ ተመዝግባለች። በግዜው ከወንዶቹ ከፍተኛ አድናቆይና ሙገሳ ስታገኝም ነበር። እናማ እህታለም.... ነፃ አውጪሽን ማጥቃትና ለመብትሽ የሚሟገተውን ከአጥቂ ጋር ሆኖ "ይሰቀል” ማለት ዛሬ ባንቺ አልተጀመረም እያልኩሽ ነው። በአፓርታይድ ዘመን አብዛኛው ጥቁር የደቡብ አፍሪካ ህዝብ ከአፓርታይድ ጨቋኝ ስርዓት ጋር ሲታገል Inkatha Freedom Party የተባሉ ጥቁሮች ግን ትግላችን ከአፓርታይድ ጋር ሳይሆን አፓርታይድን ለመታገል ከተቋቋመው ከአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ (ANC) እና ከኔልሰን ማንዴላ ጋር ነው ብለው አወጁ። ይሄ በታሪክ ውስጥ ከታዩ አሳዛኝም አስቂኝም ነገሮች አንዱ ሆኖ በታሪክ ተመዝግቧል። ማንዴላ አፍሪካን እየዞረ ጥቁሮችን ነፃ ለማውጣት መሳሪያ ይለምናል፣ ኢትዮጵያ ድረስ መጥቶ ወታደራዊ ስልጠና ይወስዳል፣ ሐገሩ ላይ ግን ነፃ ላውጣችሁ የሚላቸው ጥቁት ወንድሞቹ “እነማንዴላ አላስፈላጊ ግርግር እየፈጠሩ ነው” ብለው ድርጅት አቋቁመው እራሳቸውን ይወጓቸዋል። ለማንኛውም ውድ የቲክቶክ እህቶቻችን... እኛ ወንዶች ጠንካራ ነን። የተቆጡ ሴቶች መብታቸውን ለማስከበር ሲሮጡ ከመስመር ወጥተው ትንሽ ላስ ላስ ቢያደርጉን ልባችን አይሰበርም፣ ስሜታችንም አይጎዳም። አትጨነቁልን! ባይሆን ለራሳችሁና ለፆታችሁ ተጨነቁ። ከእህቶቻችሁ ጎን ቁሙ። ባሁን ሰአት ከፍተኛ አደጋ ውስጥ የወደቀው የእናንተ ፆታ ነው። ይሄ የኛ ፆታ ለግዜው ብዙም የሚያስጨንቅ ሁኔታ ላይ አይገኝም። በሀገራችን የሴቶች ጥቃት፣ ያለዕድሜ ጋብቻ እና ግድያ በየቀኑ እየተሰማ፣ የእናንተ ትልቁ ጭንቀት «የወንዶችን ስሜትና ባህላችንን መጠገን» ከሆነ ነገሩ አሳዛኝም፣ አስቂኝም ይሆናል። ታሪክ ሁልጊዜ የሚያስታውሰው መብታቸውን ያስከበሩትንና የታገሉትን እንጂ፣ ለተጫናቸው አካል ታማኝነታቸውን ለማስመስከር የራሳቸውን እህቶች መልሰው የታገሉትን «የቤት አበጋዞች» አይደለም።
Noah Daniel
Region: ET
Friday 14 August 2026 17:02:42 GMT
Music
Download
Comments
New hope :
ችግሩ አያነቡትም ,አንተን እናመሰግናለን🙏
2026-08-15 08:23:53
134
ሮሃዊቷ 🌸 :
የተረዳሃቸው አልመሰለኝም ።
2026-08-15 02:08:40
12
Phozy❤️ أمُّ عناية :
Thank you Brother ❤️
2026-08-18 17:46:30
0
mercy 👸Fan :
ሰው የለም እንዳልል እንዳንተ አይነት የተባረከ ሰው አለ🥰
2026-08-18 17:06:15
17
Yenenesh Ayele :
ያሳፍራል እኝ እያልን ያለነው አትግደሉን ብቻነው
2026-08-15 08:39:09
46
SGM :
abo thank you bro
2026-08-16 19:05:40
1
𓆩 🪷 𓆪 :
This is the kind of honesty I appreciate ! Tebarek !!!
2026-08-18 17:29:06
0
Cinnamon girl :
Tell them eski, those ppl only listen things when it's from a man,well articulated
2026-08-15 06:53:21
53
beauty with habel :
ኖህ ምን አይነት የበሰልክ ሰው ነህ በፈጣሪ? በጣም እናመሰግናለን
2026-08-15 10:50:16
61
Mekdes 🇺🇸 🇨🇦 :
what a gentle man 🙏🙏🙏
2026-08-18 16:56:20
0
Dr Zehara gynecologist :
appreciate your honesty and boldness 🙏.
2026-08-18 18:15:59
0
Netsi Berhanu✝🔊 :
እየሳቅኩ ነዉ የጨረስኩት😂😂
ለምን እስከዛሬ ያንተ caption በኔ for you page ላይ እንዳልመጣልኝ ነዉ የገረመኝ🙄 በጣም ተጎድቻለሁ። anyways እጅህ ይባረክ
2026-08-15 13:51:37
19
samri est :
አቦ ምንላድርግህ ብርክ በል🙏🥰🥰
2026-08-14 18:20:08
27
Tebeka Sinan (Lawyer)🍋🍋 :
እናመሰግናለን👌👌👌
2026-08-15 05:04:49
13
miracle223 :
አንጀት አርስ🥰🥰🥰
2026-08-14 17:26:08
13
Luna🌙✨ :
ተባረክ ወንድሜ።
2026-08-15 06:04:21
5
Tsion esayas :
ከጆርዲ post በኋላ የመጣ🥰
2026-08-18 18:16:56
12
Ruth Daniel :
Thank you brother 🙏
2026-08-16 14:47:04
3
judi🍉 :
#ትሰማ
👌👌
2026-08-16 12:21:46
2
ጠይባ ጭፈታ🦋 :
ክበርል በረካ ሁን የነካሀዉ ሁሉ ይመርልህ አቦ🥰
2026-08-18 17:55:12
6
🎀Nura :
I like the point of view .i appreciate
2026-08-15 19:15:17
2
To see more videos from user @sr36377378, please go to the Tikwm
homepage.