@abebawmebratu: #የኩላሊት_ጠጠርን_ለመከላከል_የሚረዱ_ምግቦች #ETHIOPIA ✅ ችግሩ እንዳይከሰት ምን እናድርግ? 👉 የኩላሊት ጠጠር እንዳይከሰት የመከላከያ ዋነኛ መንገድ ምንድን ነው? 🐶 የኩላሊት ጠጠርን ለመከላል ከሚረዱ ተግባራቶች ዋነኛውና ወሳኙ ነገር በየቀኑ ብዙ ውሃ መጠጣት ነው። ይህም ብዙ ጊዜ ሽንት እንድንሸና በማድረግ የኩላሊት ጠጠር የሚያመጡትን የካልሺየም እና ዩሪክ አሲድ ንጥረ-ነገሮች ክምችትን ይቀንሳል። 🐶 ላብ በሚያልበን ጊዜ ብዙ ውሃ መጠጣት፡- የሰውነት ላብ በሚኖርበት ጊዜ ችላ አለማለት እንዲሁም ብዙ ውሃ መጠጣት ያስፈልጋል። 🐶 ሌላው ማወቅ ያለብን ነገር ሳውና፣ ዮጋ እንዲሁም ከባባድ የአካል ብቃት እንስቃሴዎች ለጤና ጥሩ ቢሆኑም፤ ለኩላሊት ጠጠር ግን ሊያጋልጡን ይችላሉ። ምክኒያቱም በእነዚህ እንቅስቃሴዎችም ሆነ በአየር ሙቀት ለውጥ ምክንያት የሚወገደው ውሃ የሽንት መጠን እንዲቀንስ ያደርጋል። ብዙ ላብ ባላበን ቁጥር የሸንት መጠናችን ይቀንሳል። ይህም የኩላሊት ጠጠርን የሚፈጥሩት ማዕድናት ኩላሊት ውስጥ እና የሸንት ቧንቧ ወይም ቱቦ ውስጥ እንዲከማቹ ያደርጋል። 🐶 በቂ ውሃ ይጠጡ! በቂ ውሃ እንደጠጡ እርግጠኛ ይሁኑ በተለይም ሰውነት እንዲያልብ የሚያደርጉ እንቅስቃሴዎች ወይም ተግባራቶች ሲያደርጉ። ጥሩ ወይም በቂ የሽንት መጠን እንዲኖር ቢያንስ በቀን ከ2 እስከ 3 ሊትር ወይም ከ8 እስከ 12 ኩባያ ውሃ መጠጣት ያስፈልጋል። 🐶 በተቻለ አቅም የለስላሳ መጠጦች (በውስጣቸው ብዙ ፍሩክቶስ ወይም ጣፋጭነት ያላቸውን) የጣፈጠ ሻይ እና የወይን ጥማቂ ለመቀነስ ይሞክሩ። ✅ ምን አይነት የአመጋገብ ዘዴ እንከተል? 👉 የኩላሊት ጠጠር ለመከላከል ምን አይነት የአመጋገብ ስልት ይመከራል? ብዙ አይነት የኩላሊት ጠጠር አይነቶች ስላሉ ሁሉንም አይነት የኩላሊት ጠጠር ለመከላካል የሚረዳ አንድ ወጥ የሆነ የአመጋገብ ስልት የለም። አብዛኛዎቹ የአመጋገብ ስልቶች እንዳለብን የኩላሊት ጠጠር አይነት ይወሰናሉ። 1️⃣🔴 የካልሲየም ኦክስሌት ጠጠር! 👉 በብዛት የሚገኘው/የሚታየው የኩላሊት ጠጠር አይነት ነው። 🦊 እስከ 80% የሚደርሰው የኩላሊት ጠጠር የካልሲየም ኦክሳሌት የሚባለው አይነት ነው። ኦክሳሌት የኩላሊት ጠጠር እንዲከሰት ከሚያደርጉ በምግብ ውስጥ እና በሰውነታችን ውስጥ ከሚገኙ ንጥረ ነገሮች አንዱ ነው። 🦊 ኦክሳሌት በተፈጥሮ ብዙ ምግቦች ውስጥ ይገኛል፤ እነዚህም እንደ ኦቾሎኒ (ለውዝ)፣ ባቄላ ፣ቸኮሌት፣ ስፒናች፣ ስኳር ድንች፣ ቡና እና ሻይ የመሳሰሉት ናቸው። ለኩላሊት ጠጠር ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች እነዚህን ምግቦች እንዲቀንሱ ይመከራሉ። 🦊 በሌላው መልኩ በምግብ ውስጥ የሚገኝ ካልሲየም ፣ ለምሳሌ:- አንደ ወተት፣ እርጎ፣ አይስክሬም እና አይብ የመሳሰሉ ምግቦች ኦክስሌት የተባለውን ንጥረ-ነገር ሰውነታችን ውስጥ ከመግባቱ በፊት ጨጓራ እና አንጀት ውስጥ እንዲቀር በማድረግ የኩላሊት ጠጠር የመፈጠር ዕድሉን ይቀንሳሉ። 🦊 የኩላሊት ጠጠርን ለመከላከል እንድናገኘው የሚመከረው የካልሲየም መጠን በቀን ከ100-1200 ሚሊ ግራም ነው። ይህም በቀን ሶስት ጊዜ የወተት ተዋፅኦችን ከምግባችን ጋር በመጠቀም ልናገኘው እንችላለን። 🦊 በተቃራኒው ግን በእንክብል መልክ የሚቀርቡ የካልሲየም እንክብሎች ከሐኪም ትዕዛዝ ውጪ ከተወሰዱ ለኩላሊት ጠጠር ሊያጋልጡን ይችላሉ። 🦊 ጨው በምግባችን ውስጥ ማብዛት ለኩላሊት ጠጠር መከሰት ሌላኛው ዋና ምክንያት ነው። በምግብ ውስጥ ጨው (ሶዲየም) ማብዛት ብዙ የካልሲየም መጠን በሽንት ውስጥ እንዲኖር ያደርጋል። 🦊 ብዙ ጨው ወይም ሶዲየም በተጠቀምን ቁጥር በሽንት ውስጥ ያለው ካልሲየም ይጨምራል። ስለዚህም ከፍተኛ የሶድየም ወይም ጨው መጠን ያለው ምግብ መመገብ ለተጨማሪ የኩላሊት ጠጠር ይደረጋል። 🦊 እኛ እራሳችን ከምንጨምረው ጨው በተጨማሪ በየእለቱ በጣም ብዙ “ድብቅ” የሶዲየም ምንጮች ይገኛሉ። ለምሳሌ ያህል:- የታሸጉ ወይም በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦች እንዲሁም በሬስቶራንቶች ውስጥ የሚዘጋጁ እና ፈጣን ምግቦች ከፍተኛ ጨው ስላላቸው እነዚህን አይነት ምግቦች መመገብ በጣም መቀነስ ይኖርብናል። 🦊 በምግባችን ውስጥ ያለውን የጨው መጠን መቀነስ የኩላሊት ጠጠርን ብቻ ሳይሆን የደም ግፊትን ለመከላከል ይረዳል። 2️⃣ ሌላኛው አይነት የኩላሊት ጠጠር! ይህ የዮሪክ አሲድ (Uric Acid) ጠጠር ነው። ቀይ ሥጋ፣ የአካል ሥጋ (እንደ ጉበት) እና ሼል ፊሽ የሚባለው የዓሣ ዝርያዎች በውስጣቸው ከፍተኛ የሆነ ፒዩሪን (Purine) የተሰኘ ንጥረ-ነገር ይዘዋል፡፡ ከፍተኛ ፒዮሪን ይዘት ያላቸውን ምግቦች መመገብ ለከፍተኛ የዩሪክ አሲድ መመረት እና ከፍተኛ የአሲድ ጫና በኩላሊት ላይ እንዲኖር ያደርጋል። በሽንት ውስጥ የአሲድ መጠን በጨመረ ቁጥር የዮሪክ ጠጠር የመመረት ዕድልም ይጨምራል። የዮሪክ አሲድ ጠጠርን ለመከላከል ከፍተኛ የፒዮሪን መጠን ያላቸውን አንደ ቀይ ስጋ፣ የሆድ ውስጥ ዕቃ ስጋ፣ ቢራ (የአልኮል መጠጥ)፣ የስጋ ሾርባ፣ ሰርዲን ያሉ ምግቦችን ማስወገድ ያስፈልጋል። አትክልቶችን፣ ፍራፍሬዎችን፣ እህሎችን፣ እና ዝቅተኛ ቅባት ያላቸውን የወተት ተዋፅኦዎችን በብዛት ያካተተ የአመጋገብ ስልት መከተል ተገቢ ነው። ስኳር የበዛባቸው ምግቦችን እና መጠጦችን በተለይም ከፍተኛ ጣፋጭነት ያላቸውን (ለስላሳ፣ ከረሜላ፣ የ ፓን ኬክ ሽረፕ አይነት ጣፋጮችን) መቀነስ ያስፈልጋል። አልኮል በደም ውስጥ የሚገኘውን ዬሪክ አሲድ መጠን ስለሚጨምር መቀነስ ያስፈልጋል። ✅ መከላከያ መንገዶች! 👉 የኩላሊት ጠጠርን ለመከላከል ልናደርጋቸው የምንችላቸው ወይም የሚገቡ ነገሮች ምን ምን ናቸው? 🐷 የኩላሊት ጠጠር ህመም እስኪመጣ አይጠብቁ። የሚያስከትለው ህመም አስቸጋሪ ነው፤ ህክምናውም እስከ ቀዶ ጥገና ሊደርስ ይችላል። ስለዚህ አስቀድመው ራስዎን ይጠብቁ፤ ቅድመ ጥንቃቄ ያድርጉ። 🐷 ትክክለኛውን መድሃኒት፣ የአመጋገብ ስልት፣ እና በቂ ፈሳሽ መውሰድ ይኖርብዎታል። አንድ ጊዜ የኩላሊት ጠጠር ከተፈጠረ ተመልሶ የመምጣት እድሉ ከ50% በላይ ነው። ስለዚህ የአመጋገብ ስልትን ስለመቀየር እና የታዘዙ መድሃኒቶችን በአግባቡ ሰለመውሰድ ማሰብ ጠቃሚ ነው። 🐷 ማወቅ ያለብዎት አንድ ጠቃሚ ነገር፤ ውሃ በብዛት መጠጣት፣ እና ውሃን ከሎሚ ጭማቂ ጋር ቀላቅሎ መጠጣት የኩላሊት ጠጠርን ለመከላከል ከፍተኛ ጥቅም አለው። 🐷 ሥር የሰደደ የኩላሊት ጠጠር በሽታ አብዛኛውን ጊዜ በፓታሺየም ሲትሬት ይታከማል። ጥናቶች አንደሚያሣዩት፤ የሎሚ ጭማቂ፣ እና ሌሎች ፍራፍሬዎች፣ እንዲሁም ከፍተኛ የሲትሬት ይዘት ያላቸው ጭማቂዎች የኩላሊት ጠጠርን ይከላከላሉ። ✅ ችግሩ ላለባቸው የሚመከር የአመጋገብ ስልት! 👉 ለኩላሊት ጠጠር ታማሚዎች የሚመከሩ አጠቃላይ የአመጋገብ ስልቶች የሚከተሉት ናቸው:- 1️⃣ በቀን ከ2-3 ሊትር የሚሆን ውኃ ወይም ፈሳሽ ነገር መውሰድ! ይህም እንደ ውሃ እና ብዙ ጥቅም ያለውን የሎሚ ጭማቂ የመሳሰሉትን ያካትታል። ይህን ማድረግ የቀጠነ እና በቀን ሁለት ሊትር የሚደርስ የሽንት መጠን እንዲኖር ያደርጋል። #ETHIOPIA #መረጃዎችን 📶 fb.com/yejubietenamerja/ 🔥 fb.com/abebaw3367/ 🛜 tiktok.com/@abebawmebratu 🌐 t.me/abebaw3367 🆓 youtube.com/@abebawmebra
Abebaw Mebratu
Region: ET
Saturday 15 August 2026 06:51:16 GMT
Music
Download
Comments
Yassin Ebrahim :
ምን ይላል መንገዱ ትዘታ ቀሰቀስክብኚ ወድምየ👍👍👍👍👍👍
2026-08-15 16:57:49
1
hafiz jihad :
muchi kafallgshi
2026-08-17 19:55:51
0
joker🤡 :
♥️♥️♥️♥️
2026-08-30 10:18:10
0
Alamuddin kamaal :
🥰🥰🥰
2026-08-17 03:03:15
0
Mahammad Said :
@
2026-08-30 22:43:13
0
To see more videos from user @abebawmebratu, please go to the Tikwm
homepage.