@big_bini_: jordana kitchen እናቴ ላይ የሰራችው ግፍ እንደዚ በቃላት ብቻ የሚገለፅ አደለም brotherይ, ሲጀመር ያች jordana ምትባል ሴትዬ BBC lifestyle ሚለው tv show ላይ apply አረጋለው ብላ ተሳስታ ነው መሰለኝ EBS ላይ የገባችው, እንደው ደመቀ ግርማ እኮ በጣም ተራቀቀ ከተባለ የሰራው ፍርፍር ላይ የጥብስ ቅጠል ነበር ጣል የሚራግባት, ለህሊናችን ሲጠነቀቅ ሁላ rosemary አይልም ሁላ, በክስትና ስሙ "ከጎን የጥብስ ቅጠል እንጨምርበታለን" ነበር የሚለን እሺ አሁን አሁን ለብዙ ሀገራት ባህል, አመጋገብ ተጋላጭ ሰለሆንን አሁን ላይ የምግብ tv show ቢሰራ normal ነው ትላለህ, ግን የዛሪ አስራ ምናምን አመት, ሻይ በዳቦ እንደ main course breakfast የሚበላበት አገር መጥታ " እሺ ዛሪ ምንሰራው ቃለል ያለች የዶሮ አሩስቶ ነው" ትላሃለች, ወንድሜ እኛ ቤት ዶሮ በአመት ሶስት ጊዜ ነው የምትገባው, ለአዲስ ዘመን መለወጫ ለገና እና ለፋሲካ ነው, እሱንም father አንኩዋር አንኩዋር የሚባለውን የዶሮዋን part ይበላል እኛ በቅባት የራሰውን እንጀራ ነበር ምናጣጥመው, ልክ በፍጥነት ሲሄድ የነበረ መኪና ፍሬን ሲይዝ አስፓልት ላይ የሚያወጣው የጎማ ቅርፅ እስኪያወጣ ድረስ ነበር ትሪውን ጥርግግግግ አርገን የምንበላው, ታዲያ jordi'ያችን በየሳምንቱ እየመጣች የምግብ ይሁን የ palnet ስም ይሁን የማናቀው ምግብ ስም እየጠራች የስንቱን እናቶች ህይወት traumatized አደረገች መሰለህ እንደውም አስታውሳለው የሆነ ቀን እናቴ "እንደው እቺ ሴትዬ ምትሰራውንማ ዛሬ እሰረዋለው" ብላ እማዬ ከ tv ፌት ነጠላዋን ጣል አርጋ መሰረተ ትምህር እንደሚማር ሰው ደብተር እና እስኪርቢቶዋን ይዛ ቁጭ አለች jordi'አችንም "ዛሬ ምንሰራው በAzerbaijan ዓሳ አስጋሪዋች ተወዳጅ የሆነው ምግብ Luis de la Fuente የተባውን ምግብ ነው, ለዚ የሚያስፈልገን ዋናኛ ግብዓት የተገረዘ እና በጎልማሳ እድሜ ላይ የሚገኝ የmediterranean ዓሳ ይሆናል, የትም supermarket ብትሄዱ ታገኙታላቹ" ትላለች ወንድሜ እማዬ እኮ ከነስሩ ሱቅ ውጭ ገዝታ አታቅም, በቃ እቺ ሴትዬ የእናቴን ልብ ልትሰብረው ነው እያልኩ እጨነቃልው ቀጠለች እና "ዓሳውን የምንጠብስበት 3 ሊትር ከ hiroshima እና nagasak የመጣ የ dolfin ዘይት እንጠቀማለን....." አዬ እማዬ በሰፊው ተዘጋጅታ የያዘችው በጀት 500 ብር, jordi ዘይቱዋ ብቻ 5000 ብር ገባ, እማዬም ላለመሸነፍ እና እልህ ውስጥ ገብታ "ይሁን ምን ይደረግ" እያለች ማስታወሻ ላይ ትፅፋለች jordi ቀጠለች እና ያን ዓሳ ልክ make up እንደምትሰራ ሙሽራ ዱቄት ውስጥ አስገብታ ታገላብጠዋለች, አዬ እኛ ቤት ፉርኖ ዱቄት ከእኛ ልጆቹዋ በላይ ክብሮ ነው, እንደዚ jordi ስትጫወትበት ስታይ እማዬ ደሙዋ ፈልቱዋል, ግን አሁንም "ይሁን ይሁን" ትላለች ያንን ዓሳ አንስታ "አሁን በ 240 ዲግሪ ሙቀት አድረገን oven ውስጥ እናስገባዋለን, እሱ እስኪደርስ በጎን side dish እንሰራለን" አለች......ምን አለች? oven አ? አባቢ እኛ ቤት 2ድስት ነው ያለው, አንዱ ድስት ስጋ ብቻ ነው ሚሰራበት, አልፎ አልፎ ስለሚሰራበት ያብለጨልጫል, ሌላኛው ደሞ አለልህ ጥቁርርርርርር ያለ ድስት, የሽሮ ድስት ነው, ወዛደር በለይ ቀን በቀን ነፍሱ እስክትወጣ ነው ሽሮ ምትዘልበት ታዲያ jordi ምን አለች? oven, haha አይ oven, እማዬም jordi oven ውስጥ ስታስገባው አይታ "አንተ ልጅ እንደው እቺ ሴትዬ ምን ውሰጥ ነው ያስገባችው ዓሳውን? ኮሞዲኖ ውስጥ ነው ያስገባችው? እ?" አለችኝ እማዬን ስለ oven ከማስረዳት ስለ quantum physics ባስረዳት ይቀላል, በዛ ላይ ዋጋውን ምኑን ስነግራት ሞራሉዋ እንደሚጎዳ ገባኝ, እንዲው በደፈናው "የምግብ መስሪያ ማሽን ነው" አልኩዋት "ማሽን? ለመሆኑ ስንት ነው ሚባለው ዋጋው" አለችኝ እጅ ላለመስጠት, አይይይይ በቃ ቁርጡዋን ልንገራት ብዬ በወቅቱ ከ 10,000 አይዘልም ነበር እና "10ሺ አከባቢ እማዬ" አልኩዋት በውስጢዋ ይዛው የነበረው ንዴት ገንፍሎ "እንዲነችናናናናና ምግብ አሰራር ላሳያቹ ብላ ፋፍሪካ ቤት ልታከፍተን ነው እንዴ!!! በል አጥፋልኝ እሄን tv አንተ ነህ ምኑንም ምኑንም እየከፈትክ እዚ......" አለችኝ ከዛ በሁዋላ ዜና ከመድረሱ በፌት የሚታዩት የሰሜን ፓርክ ጦጣ ዋች ሲመጡ ሁላ jordi እየመሰሉዋት "አጥፋ ልኝ እቺን ሴትዬ" ማለት ጀምራ ነበር አይ jordi
big_bini_
Region: ET
Sunday 16 August 2026 09:03:36 GMT
Music
Download
Comments
skuna :
luis de lafuente 😂 i can't
2026-08-16 09:37:54
18
tinsu yz :
ያልተወራልህ 👐🤌
2026-08-16 17:54:17
17
Judy :
I ant stop laughing weyna I love your mom😂😂😂😂😂😂
2026-08-16 19:05:42
4
🍰 :
ende humour another level🙌💞
2026-09-01 23:08:19
0
የኤማን አባት :
አሪፍ ነው
2026-09-18 00:29:59
0
bisratti Bugatti 👑 :
the man😎
2026-09-29 08:58:44
0
orthoselina :
😅weyni
2026-08-17 14:53:10
1
Rue📚🇪🇹🦋 :
ሞትኩ🤣
2026-09-11 17:25:40
0
Aki :
Bini is here 😁😁
2026-08-16 20:35:46
0
Abrham.solomon :
👏
2026-08-16 09:18:52
2
Kalkidan :
tchilaleh bini 🔥🔥
2026-08-17 07:48:23
1
robela :
2026-08-16 11:22:08
1
አባ :
በjordana አድገን jordin ለቀቀብን
2026-08-17 00:51:55
4
@mahi :
ሉዊስ ደ ላፎንቴ አርጀቲናውስጥ ተወዳጅ ምግብ ነው😂
2026-08-16 19:41:50
0
Bu..chu :
I like your way of explanation she traumatized all of our mothers Bro😁😁😁😁
2026-10-10 19:42:17
1
እምነት🌖🌷 :
u have talent i sware 😂
2026-08-16 12:35:40
1
Nardi :
😂😂😂
2026-08-16 14:17:06
1
grmay.k.a :
Luis de la Fuente ኣይከኣልኹይ 😁😁😁
2026-08-16 09:29:39
2
HKT 💊 :
ንስኻ ኣውግዕ🥰🤣
2026-08-19 09:52:16
1
Roba :
😂😂😂
2026-09-04 10:59:15
0
Wossy🦅 :
😂😂😂😂
2026-09-09 10:57:16
0
Meklit 💕 :
🤣🤣🤣
2026-08-16 09:09:37
1
Dan :
😂😂😂🤩
2026-08-16 09:11:12
1
To see more videos from user @big_bini_, please go to the Tikwm
homepage.