@hiyab19a: ጠቢቡ መነኩሴ ከዛፍ ስር ተቀምጦ ፀሎት እያደረሰ ነው፡፡ ፀሎቱን እያደረሰ እንዳለ ከዛፉ ላይ ወደ ጉንጩ ትኩስ እንባ ይንጠባጠብ ጀመር፡፡ _ ፀሎቱን አድርሶ ጉንጩን እያበስ ሽቅብ ወደ ዛፉ ቅርንጫፍ አማተረ፡፡ ቁራ ከቅርንጫፉ ላይቆሞ አምርሮ እያለቀሰ አየው፡፡ ‎ ‎''ቁራ ምን ገጠመህ ? ለምንድን ነው እንዲህ አምርረህ የምታለቅሰው?'' አለው መነኩሴው፡፡ ‎ ‎"ደስታን አጥቻለሁ፤ ህይወት በጣም አስጠልታኛለች፤ ያየኝ ሰው ሁሉ በድንጋይ ፡በቀስትና ወንጭፍ ወርውሮ ሊገድለኝ ይምክራል፡፡ ለአፍታ ከዛፎች ቅርንጫፍ ላይ ሳርፍ ሰው አየኝ አላየኝ ሰቀቀን ነው፡፡ ለምን እንዲህ እንደምጠላ አላውቅም፡፡ ደስታን አጥቻለሁ፡፡ ህይወት በጣም አስጠልቶኛል፡።" አለ፦ ቁራ ሳግ እየተናነቀው፡፡ ‎ ‎"እኔ ጠቢብ ነኝ፤ የምትፈልገውን ልሰጥህ እችላለሁ፡፡ ምን እዳደርግልህ ትሻለህ?" አለ ሞነኩሴው፡፡ ‎ ‎''ከፊትህ ሞገስ ካገኘሁ እባክህን ዳክዬ አድርገኝ፡፡'' ‎ ‎"እንደ ፍቃድህ ዳክዬ አደርግሃለሁ፡፡ ነገር ግን ከዚያ በፊት ዳክዬን ፈልግና በህይወቱ ደስተኛ መሆኑን ጠይቅ?'' ቁራው ዳክዬ ፍለጋ በረረ...ከብዙ ድካም በኋላ ዳክዬዋ ከሀይቅ ውስጥ እየዋኘች አገኘና ‎በጣም ታምርያለሽ፤ የላባሽ ላዛነትና ንጣት ግሩም ነው፡፡ በዚያ ላይ ሰዋች ይወዱሻል ከአዋዋፍት መካከል እንዳንቺ ደስተኛ የለም'' አለ ቁራ፡፡ ‎ ‎"ኧረ ተወኝ ወዳጄ ምኑን አማርኩኝ ካልጠፋ ቀለም ድፍን ነጭ አርጎኝ፤ በዚያ ላይ ክንፍ እያለኝ መብረር ነፍጎኝ፤ ከአሁን አሁን አዞ መጥቶ ሰለቀጠኝ ብዬ በፍርሃት ሰውነቴ እያለቀ ስለምን ደስተኝነት ነው ምትደሰኩርብኝ? ደስተኛ አዕዋፋት ፈልገህ ከሆነ ሂድ ወደ ፒኮኮች በቀለማት ወዳጌጡት፡፡በጎብኚ ታጅቦ በዙ(zoo) እና ፓርክ ተጠብቀው ከሚኖሩ ፒኮኮች ጋ ሂድ፡፡" ‎ ‎ቁራ ወደ ፒኮክ በረረ፡፡ ፒኮክ በመቶዎች በሚቆጠሩ ጎብኚ ተከብቦ ነበር ቁራው የደረሰው፡፡ ቀስ በቀስ ጎብኚዎች ሂደው ሲያልቁ ቁራ ወደ ፒኮክ ጠጋ በማለት፦ ‎ ‎"ፒኮክ በቀለማት ያሸበረቅሽ ቆንጆ፡ በሰዎች የተወደድሽ እድለኛ ፍጥረት ነሽ መቼም ከአዋዋፍት መካከል እንዳንቺ ደስተኛ የለም..!' አላት፡፡ ‎ ‎"በሰው መወደዴ ምን ፈየደልኝ? ዘመኔን በሙሉ በዙ(zoo) ‎ ‎ውስጥ ተቆልፎብኝ እስረኛ እንድሆን አረገኝ እንጂ፡ በቀለማት ያጌጠ ላባየን ለቁስ ማስጌጫ የሚፈልጉ ሰዋች፣ ድፍት አርገው ሊነጫጩኝ እንደሚሹ ብታውቅ፡ እድለኛ ባላልከኝ... እድለኝነቱ ቀርቶ ለአንድ ቀን እንዳንተ በነፃነት ከአድማስ እስከአድማስ በርሬ ብሞት..!' ‎ቁራ በሰማው ነገር እየተደመመ ወደ ሰማይ ከፍ ብሎ በረረ። ደስተኛ ለመሆን ከፈለግን ትኩረታችንን ባለን ነገር ላይእናድርግ፡ አላስፈለጊ ንፅፅር እናስወግድ ‎ ‎ይህ አስተማሪ ሆነው ካገኛችሁኋቸው ሌሎችም ይማሩባቸው ዘንድ Like እና share እያደረጋችሁ | አመሰግናለሁ ። ‎#viral #fyp @Estifanos Teshome

🅗🅘🅨🅐🅑19❉
🅗🅘🅨🅐🅑19❉
Open In TikTok:
Region: ET
Monday 17 August 2026 08:00:48 GMT
19540
640
16
88

Music

Download

Comments

user6322737776527
Hana :
ትክክል
2026-08-17 20:53:56
4
danilasefadani
danilasefadani :
አመሰግናለሁ አስተምሮኛል
2026-08-20 05:53:14
2
nataneyem1
nataneyem tanashi agelgay :
በስማም ተባረክ
2026-08-19 02:16:21
1
user4291184780534
userተዋነይ ዘ ጎንጅ :
ባለን ነገር እንደሰት ነው መልእክቱ እናመሰግናለን
2026-08-19 18:38:29
2
eyosiyasadonay
eyosiyasadonay :
እውነት ነው
2026-08-17 14:10:51
1
brneshmulu
የማርያም ልጅ@21ምስለ ፍቅር ወልዳ :
አውነት ነው
2026-08-19 13:09:55
1
selam06784
selam :
betkkl
2026-08-22 11:11:54
0
tarekegn5944
semaye & tarekaye :
reply
2026-08-19 15:24:23
1
user276654201541
h z :
wow
2026-08-20 07:04:49
0
lingerewwagaw
D/nlingerew :
Grum nw emamlakn
2026-08-19 16:30:07
1
grezman166
Grez man :
🙏🙏🙏
2026-08-17 09:11:03
2
user8613833725982
bruk :
🥰
2026-08-19 09:19:23
1
abi64793
Abi :
🥰🥰🥰🥰
2026-08-19 14:47:24
1
etsegenete.eyob
Etsegenete Eyob :
👌👌👌👌
2026-08-18 03:10:16
1
hune1827209785426
hune@1827209785426 :
🥰🥰🥰
2026-08-19 06:25:05
1
user21eliyabe
ዘኤልያብ ኤልዮኤናይ :
🥰🥰🥰
2026-08-19 04:04:43
1
To see more videos from user @hiyab19a, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About