@viewer_1221: ብዙ ሴቶች የአንድ ወንድ የትዳር ምርጫ ምን ላይ እንደሚመሰረት አይገባቸውም። “ቆንጆ ነኝ፣ እወደዋለሁ፣ እሱም ይወደኛል፣ ትዳርም እፈልጋለሁ፤ ታዲያ ምን ይጎድለኛል?” ይላሉ። ነገር ግን ትዳር የፊት ውበት የሚመዘንበት መስፈርት አይደለም። ለአቅመ ሄዋን መድረስም ብቻውን በቂ መስፈርት አይደለም። መዋደድም ብቻውን ትዳርን ለመሸከም ዋስትና አይሆንም። አንድ ወንድ አንዲትን ሴት ለትዳር ሲያስብ የሚያየው ፊቷን ብቻ አይደለም። ከፊቷ በኋላ ያለውን ሰውነት ይመለከታል። ውበት ዓይንን ይስባል፤ ባህሪ ግን ልብን ያስቀምጣል። አንድ ወንድ ለትዳር የሚመርጣት ሴት በችግር ጊዜ እንዴት እንደምትሆን ያስባል። ሁሉም ነገር ሲስተካከል ከጎኑ መቆም ቀላል ነው፤ ነገር ግን ሕይወት ሲከብድ እጁን የምትይዝ ሰው መሆኗን ይፈልጋል። በደስታው ጊዜ የምትስቅለት ብቻ ሳትሆን፣ በመከራው ጊዜ የምታጽናናው መሆኗን ይመዝናል። ሲቆጣ ወይም ሲበሳጭ እንዴት ትናገራለች? ከእሱ ጋር ብትለያይ ክብሩን ትጠብቃለች? ሚስጥሩን ትጠብቃለች? በሌለበት ስለ እሱ እንዴት ትናገራለች? ገንዘብ ሲበዛ ብቻ ትደሰታለች ወይስ አብራ ለመገንባት ትችላለች? እነዚህ ናቸው የሚመዘኑት። ምክንያቱም ትዳር አብሮ ፎቶ መነሳት አይደለም። አብሮ ሕይወት መሸከም ነው። አንዲት ሴት ቆንጆ ልትሆን ትችላለች፤ ግን ቆንጆ ባህሪ ከሌላት ውበቷ ትዳርን ለመጠበቅ አይበቃም። አይኗ ስለሚያም ልትቁለጨለጭ ትችላለች። ዳሌዋ ስላማረ ልትገላበጥ ትችላለች። ነገር ግን እሱ ለስሜት እንጅ ለትዳር መስፈርት አይሆንም ። ይህ ማለት ቁንጅና ወይም ተክለ ቁመና አያስፈልግም ማለት አይደለም ግን የመጀመሪያና ዋነኛው አይደለም። በጣም ልትወደው ትችላለች፤ ግን ፍቅርን በክብር፣ በታማኝነትና በትዕግሥት መጠበቅ ካልቻለች ፍቅሯ ብቻውን አይበቃም። ትዳርን የምትፈልግ ልትሆን ትችላለች፤ ግን ትዳርን መፈለግና ትዳርን መሸከም ሁለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው። አንድ ወንድ ለትዳር የሚመርጣት ሴት የራሷ ሕይወት ያላት መሆኗንም ይመለከታል። ሁሉንም ነገር በእሱ ላይ ብቻ የማትጭን፣ ራሷን የምታከብር፣ የራሷን ውሳኔ መወሰን የምትችል፣ በፍቅር ውስጥም ራሷን የማታጣ ሴት መሆኗን ይፈልጋል። ከሁሉም በላይ ግን አንድ ወንድ ራሱን የሚጠይቀው ጥያቄ አለ... “ከዚህች ሴት ጋር በዕድሜዬ ሁሉ አብሬ ብኖር፣ ቤቴ የሰላም ቦታ ይሆናል ወይስ የጦርነት?” የሚል ነው። ይህን ጥያቄ የሚመልሰው አፍንጫዋ አይደለም። ቁመቷም አይደለም። ውበቷም ብቻ አይደለም። ማንነቷ ነው። ባህሪዋ ነው። እሴቷ ነው። ልቧ ነው። ስለዚህ ለትዳር ብቁ መሆን ማለት “አንድ ወንድ እንዲወደን ምን እናድርግ?” የሚለው ጥያቄ አይደለም። “አንድ ሰው ሕይወቱን ከእኛ ጋር ሲያጋራ የሚያገኘው ምንድነው?” የሚለው ጥያቄ ነው። ትዳር የሚጀምረው “እኔ ምን አገኛለሁ?” ሳይሆን፣ “እኔ ምን አመጣለሁ?” ከሚለው ጥያቄ ነው። በአጠቃላይ፣ የሚያምር ፊት የሚያልፍ ውበት ነው፤ የሚያምር ልብ ግን በየቀኑ የሚያድግ ውበት ነው። ለትዳር የሚመርጥ ወንድ የሚፈልገው ፍጹም ሴት አይደለችም፤ ከእሱ ጋር ፍጹም ለመሆን በየቀኑ የምትሞክር ሴት ናት። ይህ የእኔ እይታ ነው ✍️ ቀጣይ ሌሎች እይታዎች እንዲደርስዎት የእኔ እይታን ፔጅ Follow, Like, Share, Repost እና Copy Link በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ! #foryou #fyp #viral #fypシ #viralvideo
የእኔ እይታ
Region: SO
Monday 17 August 2026 17:48:01 GMT
Music
Download
Comments
🔥MY❤Orthodox👑🙏 :
ሰላምከሁሉም በላይነዉ🙏
2026-08-17 20:11:07
5
Mahi ✅️ :
እውነት ነው ትዳር ቀልድ አይደለም የምንመረጠውን ሰው በትግስት ማወቅ አለብን መልኩ ሲስበን ልቡ ሊያባርረን ይችላል እና ያለ የሌለ ውበታችንን ከማሳየት ይልቅ ልባችንን እናቀራረበው የሚያፀናን እሱ ነው 🙏
2026-08-17 21:17:25
4
ሜሪ :
ትክክል ነዉ ወንድ ልጅ ሰላም ይፈልጋል ሴት ልጅ እምነት ትፈልጋለች የሁለቱ ጥምረት ፍቅር ይወልዳል ፍቅር ደግሞ ከሁሉ በላይ ነዉ ለእዉነተኛ ፍቅር እንኑር
2026-09-12 09:16:38
2
Umu Sitra :
አደኛ ነው
2026-08-29 00:07:44
0
seya k s :
ያልካቸው ሁሉ በኔ ሀሳብና ፍላጎት ውስጥ ያሉ ናቸው
2026-09-17 08:12:57
0
444 keyo (Agumas )❤️manche ❤️ :
2026-08-20 12:22:17
1
W Man :
በትክክል🥰🥰🥰
2026-08-18 19:21:55
1
wesen164 :
🙏🙏🙏🙏🙏🙏 ተቀብለናል 🙏🙏🙏🙏
2026-08-17 18:36:15
1
ዜድ የ/ኮቻዋ :
2026-09-11 05:19:16
0
ፍቅሩ የሻንበል :
❤️❤️❤️
2026-09-06 07:40:05
0
betsi .leo♌️ the lion. :
absolutely true
2026-08-17 18:54:50
1
betisemu :
bimnt
2026-08-17 19:20:13
1
wube :
betikekele gn. dehana. gebiya. ayegenagnme
2026-08-17 18:29:03
1
farxiyaxashi3 :
እስኪ ለኔ አገናኙኚ አትመር አትድመቅ ክብሯን ማንነቷን ጸባይዋን አካላት ለኔ በቂ ነው ከስራም በምመጣበት ግዜ ሁሉ ነገሩ የተዘጋጀ መሆኑን ከነጽዳቷ ለኔ በቂየ ነች🙏🙏
2026-09-09 08:05:33
0
ሙሉ ሸዋ ተጉለት :
🥰🥰🥰🥰🥰
2026-08-18 04:17:15
2
እኔ እና ጨረቃዬ💫 Ⓜ👸Ⓑ🍎🔐 :
🥰🥰🥰🥰
2026-08-18 02:11:44
1
zuzu😍 :
🥰🥰🥰🥰
2026-08-17 19:20:37
1
Tg ጎጃሜዋ❤ :
🥰🥰🥰
2026-08-17 19:32:45
1
yhunew ✝️የገብርኤል ባርያ!!! :
👍👍
2026-08-24 06:29:10
0
Habtamu Sisay :
🙏🙏🙏🙏🥰🥰🥰🥰
2026-09-04 10:18:46
0
ZED ነኝ የራያዋ :
🥰🥰🥰
2026-08-17 23:39:53
1
tig_21🙏❤ :
❤️❤️
2026-09-06 00:21:35
0
tigstilove :
👍👍👍
2026-08-19 19:49:22
1
ተመስገን 💐🥰 :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-08-18 18:28:09
1
To see more videos from user @viewer_1221, please go to the Tikwm
homepage.