@damot_post: ወጣት ነው፤ቁመናው ሸበላ ነው፤ድምፁ ጆሮ ገብ፥መልከ መልካም ወንዳወንድ ነው። #ዮ_ማሪዎስ ይባላል።በመሀል ባህር ዳር ቀበሌ 5 ተወልዶ ያደገ ድብን ያለ ዘመናዊ የከተማችን ልጅ ነው። ዮ ማሪዎስየባሕር ዳር ልጆች ምን ያህል ዓለም አቀፍ እሳቤ ያላቸው ዘመናዊ ፈርጦች መፈልፈያ እንደሆኑ በተግባር ያሳዬ እንቁ ወንድማችን (ልጃችን) ነው። ይህ ወጣት የመጣባቸው የሙዚቃ ስልቶች ብዙዎቻችንን ካለንበት የጦርነት እና የመከራ ስሜት ለተወሰነም ግዜ ቢሆን ወጥተን በተለይ #በራፕ ቅላፄ ራሳችንን እንድናዝናና በእጅጉ ማህበረሰባችንን ጠቅሟል። የታሪክ መዛግብት እንደሚያስረዳው "ራፕ"' የተባለ የሙዚቃ ቅላፄ ምንጩ አማራ ነው ይባላል።መዛግብቶች ይሄንንም ሲያስረዱ በሀገራችን በገጠሩ አካባቢ በሚደረጉ የደስታ ዝግጅቶች በተለይ የሰርግ ስነስርዓት ላይ ታዳሚው እራሱን እና ማህበረሰቡን ለማዝናናት ከሚጠቀሙበት የጭፈራ ስልቶች ውስጥ አንዱ "ቀረርቶዎች ከዚያም በመቀጠል የሚመጡት "ፉከራዎች..." ለራፕ ሙዚቃ መነሻነት እንደዋነኛ ማስረጃነት ይቀርባሉ። ስለሆነም ከእንደዚህ አይነቱ ቱባ የባህል ስሪትና ጥበበኛ ህዝብ የፈለቀው ዮ_ማሪዎስ "ገጠር ግባ..." በሚለው ስራው ከፍተኛ ተወዳጅነት ያገኘ ሲሆን አሁን ደግሞ አንስቶ የማይጠግባትን የትውልድ ከተማውን (ባህር ዳር ከጣና ዳር...) በሚል የጎጃምን ውበት ከጣና እፁብ ድንቅ እይታ ጋር አጣምሮ ከፍ ባለ ደረጃ ለጆሮ ምቹ ካስፈለገም ከመቀመጫችን ብድግ ብለን ካስፈለገን በእስክስታ ካሻን ደግሞ በራፕ እራሳችንን የምናዝናናበት ዜማ አሞካሽቶ ሰርቶልናል። እኛም እያየንህ በቅርቡ የዓለም ስታር እንደምትሆን እርግጠኞች ስለሆንን በዚህም ደስ ይለናል።ስለከተማችን እና ህዝባችን ላደረግከው አስተዋፅኦ እናመሰግናለን። ጨዋ የጨዋ ልጅ የተነሳበትን የማይረሳ ነው፤ እርሱ ደግሞ ጀግና ነው ይሉናል አባቶች። ያባቱ ልጅ፤ ደሜ በርታ!!! ቻው!

ኢትዮጵያዊው ትራዎሬ  ፖስት
ኢትዮጵያዊው ትራዎሬ ፖስት
Open In TikTok:
Region: ET
Tuesday 18 August 2026 04:47:10 GMT
34120
1421
29
47

Music

Download

Comments

elloha1916
𝔹𝔼ℝℍ𝔸ℕ𝕌💥 :
ባሕርዳር ጎጃም, አማራ አፍሪካ🥰
2026-08-18 08:01:28
6
abreham6008
abreham :
ኦ 4 ነዉ ቀበሌዉ
2026-08-18 09:24:54
2
user2585361419704
213 :
Home of Gojjam Bahir dar
2026-08-18 08:59:29
1
kasahunworka380
Kasahun Worka :
እረ ቀበሌ 4 ሎተሪ ሰፈር ነው
2026-08-21 07:17:16
1
yizengawkwt
ማርዳ :
ክበርልን አቦ
2026-08-19 16:42:24
1
ephu416
Ephu :
እናመሰግናለን ወንድማችን
2026-08-18 17:03:40
1
hiwotasemahegn
hiwot11 victor door seals :
yemcheh bro♥️♥️♥️♥️♥️enamsegenhaln egna gojamiwoch
2026-08-18 15:11:25
1
shanbelabr
shanbel aber :
ዋውውው ድምጹ ሲያምር ዮየ ጀግና
2026-08-18 08:46:09
1
alemnesh.ybka
ፍቅር የሕግ ሁሉ ፍፃሜ ነው ። :
አንደኛ የሆነ ራፐር ግን በክሊፕ ሲሆን ደሞ እናያለን
2026-08-18 09:44:33
2
beruh.tesefa
Beruh Tesefa :
እናመሰግናለን
2026-08-18 14:06:20
1
beiablmulu.1
ስውሩ አርበኛ :
ገና ሁሉም አርቲስት ስለጎጃም ይዘፍናል
2026-08-19 00:24:19
1
ligpiter2
ligpiter :
ሰላሞን ይመልስልን
2026-08-18 06:30:46
1
creater.search.insite
Tiruneh.K :
🥰🥰🥰
2026-08-18 04:59:27
1
zewdu_tagele
Zewdu_Tagele Melkie :
😍😍😍😍 አንበሳ ልጅ ነው
2026-08-18 07:46:46
1
mahi.love489
Mahi Love :
yo
2026-08-18 18:19:20
1
berhanu2127
berhanu🇪🇹21💞27🇪🇹 :
2026-08-18 10:50:48
1
hanayitayew6
hani🔐 :
💪💪💪💪
2026-08-19 05:34:55
1
morisberhanie
Moris :
🥰🥰🥰
2026-08-19 09:16:23
1
user7932388193213
helen :
🥰🥰🥰🥰
2026-08-18 08:38:58
1
maryam.....11
Melsew Tilahun :
🔥🔥🔥
2026-08-18 08:54:10
1
ephrem_kidane
ephrem k user5202215892594 :
🙏
2026-08-18 14:11:56
1
hewan0330
hewan :
🙏🙏🙏
2026-08-18 19:23:47
1
nebiyu.kindie
ዋው ዋው :
❤️❤️❤️❤️
2026-08-18 10:26:58
2
To see more videos from user @damot_post, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About