@tame6396: ደብረ ታቦር [ቡሔ] የደብረ ታቦር [የቡሄ] በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቀኖና መሰረት ከዘጠኙ አብይ በዓላት ውስጥ አንዱ ሲሆን የሚከበረውም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በማስተማር በነበረበት ጊዜ በደብረ ታቦር ላይ ብርሃነ መለኮቱን፤ ክብረ መንግስቱን የገለፀበት ዕለት ለማስታወስ ነው። ይህ በዓል በየዓመቱ ነሃሴ ፲፫ [13] ቀን ይከበራል። የዚህ በዓል መሠረት የክርስቲያን እምነት ሲሆን፣ ደብረ ታቦር በግዕዝ የታቦር ተራራ ማለት ነው፡፡ የታቦር ተራራ የሚገኘው አሁን ፍልስጤም ተብሎ በሚጠራው ሃገር ነው፡፡ ደብረ ታቦር ወይንም የታቦር ተራራ ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት ደቀመዛሙርቱን ይዞ ወደ ተራራው የወጣበትና ፊቱ እንደ ፀሐይ የበራበት ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ የሆነበት ቦታ ነው፡፡ ይህ ቦታ ጌታ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ተራራ ነው፡፡ የደብረ ታቦር በዓል በኢትዮጵያውያን ዘንድ የቡሄ በዓል በመባል ይጠራል። ቡሄ ማለት መላጣ [ገላጣ] ማለት ነው። በሃገራችን ክረምቱ፤ አፈናው ተወግዶ፤ የብርሃን ወገግታ የሚታየው በዚሁ በዓል አካባቢ ስለሆነ ቡሄ ያሉት ለዚህ እንደሆነ ይነገራል። በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ህፃናት ይህ በዓል ከመድረሱ በፊት ጅራፍ ሲገምዱና ሲያጮሁ ይሰነብታሉ፤ እናቶችም ለዚሁ በዓል የሚሆን ዳቦ ለመጋገር ዝግጅታቸውን ያደርጋሉ። በዓሉ እንደ ነገ ሊሆን እንደ ዛሬ በዋዜማው ዕለት የሰፈር ህፃናት በየቤቱ እየዞሩ ቡሄ ቡሄ እያሉ ይጨፍራሉ። በዚህ ጊዜም እናቶች ካዘጋጁት ዳቦ እያነሱ ይሰጧቸዋል። የጅራፉ ማጮህ ተምሳሌቱ የጅራፉ ድምፅ ሲጮህ ማስደንገጡ የሐዋርያትን [የጴጥሮስን፣ የያዕቆብንና የዮሐንስን] በድምፀ መለኮት መደንገጣቸውን ለማስታወስ ነው። በአንዳንድ አካባቢዎች በቡሄ ዋዜማ ዕለት ችቦ ያበራሉ። ይህም የሚደረገው በደብረ ታቦር ለታየው ብርሃነ መለኮት ምሳሌ ነው ። የቡሄ እለት ለዘመድ አዝማድ ለእያንዳንዱ ቤተሰብ በልጆቹ ልክ ዳቦ ይሰጣል። በተጨማሪም ለክርስትና ልጅ፣ ለጡት ልጅ፣ ለአማች፣ ለምራት፣ የቅርብ እውቂያ ላለው ሁሉ የቡሄ ዳቦ ይሰጣል። እንኳን ለደብረታቦር (ቡሄ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ /አደረሰን የአመቱ ሰው ይበለን!!

ፍኖተ  ሎዛ
ፍኖተ ሎዛ
Open In TikTok:
Region: ET
Tuesday 18 August 2026 16:18:25 GMT
719
26
2
3

Music

Download

Comments

nafigrace888
nafi grace :
3 tu ደቀመዛሙርት ena manchew
2026-08-19 18:23:00
0
To see more videos from user @tame6396, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About