@debretsehaymedia: በዓለ ደብረ ታቦር በአዳማ ደብረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ካቴድራል በታላቅ ድምቀት ተከበረ ዛሬ ነሐሴ 12 ቀን 2018 ዓ.ም የአዳማ ደብረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ካቴድራል ምእመናን የደብረ ታቦርን በዓል በአውደ ምሕረቱ ላይ በታላቅ መንፈሳዊ ደስታና ድምቀት አክብረዋል። በዕለቱ የካቴድራሉ የመጻሕፍት ትርጓሜ መምህር ሊቀ ማዕምራን ተርቢኖስ ቶለሳ እነሆ፥ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት» (ማቴ. 17፥5) በሚል ኃይለ ቃል መነሻነት ትምህርተ ወንጌል አስተላልፈዋል። መምህሩ በትምህርታቸው የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አብራርተዋል፦ «በእርሱ ደስ የሚለኝ» ያለው ለምንድን ነው? «ልጄ» ብሎ መጥራቱ ለምን አስፈለገ? የክብሩ መገለጥ ለምን በተራራ ላይ ሆነ? በመቀጠል የካቴድራሉ ዋና አስተዳዳሪ መልአከ ብርሃናት ቆሞስ አባ ማርቆስ ብርሃኑ «በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው» በሚለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል ላይ ተመስርተው ባአስተላለፉት መልእክት፤ ምሥጢረ ሥላሴና ምሥጢረ ሥጋዌ በሚነገርባት፣ ፍጹማን ምእመናን በሚሰበሰቡባት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዘወትር መገኘት እንደሚገባን አሳስበዋል። መልአከ ብርሃናት አባ ማርቆስ አክለውም ጸሎተ ወንጌል ካደረሱ በኋላ፣ የብርሃነ መለኮቱ ምሳሌ የሆነውን ችቦ አብርተው ሕዝበ ክርስቲያኑን ባርከዋል፤ በዚህም የዕለቱ መንፈሳዊ መርሐ ግብር በጸሎትና በበረከት ተጠናቋል። ለዚህ ቀን ላደረሰን ለአምላካችን ክብርና ምስጋና ይሁን! #Dabra_Tsahaay_Media #ኪዳነምህረትእናቴ #የአዳማ_ደብረ_ፀሐይ_ቅድስት_ማርያም_ካቴድራል_ሚዲያ #ኪዳነምህረት_ከክፉ_ነገር_ሁሉ_ትጠብቃላችሁ #ደብረፀሐይሚዲያ
ደብረ ፀሐይ ሚዲያ
Region: ET
Tuesday 18 August 2026 18:37:55 GMT
Music
Download
Comments
Rahel Rich :
እኔ ያልገባኝ ለምንድ ነው ደብረ ፀሀይ ብቻ በ12 የሚከበረው?
2026-08-19 13:51:47
0
lili192104 :
በረከታቹሁ ይደርብን
2026-08-19 13:24:43
0
hereg 🥰 :
🥰🥰🥰
2026-08-19 06:56:47
0
John Oro....koo :
🥰🥰🥰
2026-08-19 05:58:12
0
𝙚𝙮𝙤𝙧🦋 :
🙏🥰
2026-08-19 05:53:01
0
sifuukoo :
🥰🥰🙏
2026-08-19 05:34:37
0
@haset :
🙏🙏🙏
2026-08-19 03:10:17
0
Firii Live Official💠✅ :
❤️🥰
2026-08-18 19:39:45
0
mera21 :
🙏🙏
2026-08-18 19:33:24
0
Sr.Weduu kinfe..........21 :
🙏🙏🙏
2026-08-18 19:04:45
0
Kalkidan :
🥰🥰🥰🥰
2026-08-18 18:59:48
0
Fira :
🔥🙏
2026-08-18 18:58:07
0
(ያልተኖረው➴ ልጅነት) :
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-08-18 18:47:00
0
marti 💒🙏🏻12 :
😍🙏
2026-08-18 18:45:58
0
Debelo :
🥰🥰🥰
2026-08-18 18:45:33
0
fenet 27✨ :
🥰
2026-08-18 18:41:49
0
Henok :
🥰🥰🥰
2026-08-18 18:39:58
0
Hasset@shewit :
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-08-19 07:03:35
0
To see more videos from user @debretsehaymedia, please go to the Tikwm
homepage.