@tatek.media27: ነገሩ እንዲህ ነው፤ እህታችን ተሚማ እተፋ ትባላለች። በሳዑዲ ዓረቢያ ለአሥር ዓመታት ያህል በማዳም ቤት በሞግዚትነት ሥራ ላይ ተሰማርታ ስታገለግል የኖረችው በፍቅርና በታላቅ መከባበር ነበር። የቤተሰቡ አባላት ሁለት መንትያ ልጆች ነበሯቸው፤ ልጆቹም የኦቲዝም (Autism) ሁኔታ ይገኝባቸው ነበር። እህታችን ተሚማ እነዚህን ህፃናት ለ10 ዓመታት ያህል ልዩ በሆነ የእናትነት ፍቅርና እንክብካቤ ስታሳድጋቸው ቆየች። ጊዜው ደርሶ የገዛ ሀገሯ ተመልሳ ኑሮዋን ለመቀጠል ወደ ኢትዮጵያ ስትመለስ፣ ፍቅራቸው ግን በሐገር ርቀት አልተገደበም። ስልክ ይደዋወሉ ነበር፤ ነገር ግን የስልክ ድምፅ ብቻ የህፃናቱን ናፍቆት ሊወጣው አልቻለም። የልጆቹ ወላጆች «ተሚማ እኛም ናፈቅሽን፤ ልጆቻችንም ቀን ከሌሊት እያለቀሱ 'እናት እናታችን ናፈቀችን' እያሉ አስቸገሩን» በማለት በፍቅር ታስረው ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ወሰኑ። እናም ከሁለት ሳምንት በፊት ህፃናቱን አስከተው ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መጡ። እሷም በክብራቸው ልክ በፍቅርና በደስታ ተቀበለቻቸው። እነሱም ቀን ቀን ተሚማ ቤት እየወጡና ከእሷ ጋር ከተማዋን እየጎበኙ፣ ማታ ማታ ደግሞ ወደ ማደሪያ ሆቴላቸው እየተመለሱ ለአንድ ሳምንት ያህል በፍቅር አብረው አሳለፉ። በመጨረሻም የናፍቆት እራባቸውን ተወጥተው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ። ይህን ልብ የሚነካ እውነተኛ ታሪክ ያነሳሁበት ምክንያት፣ ሰሞኑን የሀገራችን ስም በሳዑዲ ዓረቢያ ወንድሞቻችን ዘንድ በመጥፎ እየተነሳ ባለበት ወቅት፣ የእውነትና የእውነተኛ ፍቅር መገለጫ የሆነውን የኢትዮጵያውያንን ደግነትና መልካም ስብዕና ለማስታወስ ነው። Via Mame Yasin 🙏🙏🙏

ታጠቅ Media ✅
ታጠቅ Media ✅
Open In TikTok:
Region: GR
Wednesday 19 August 2026 06:35:51 GMT
165543
6922
442
517

Music

Download

Comments

h.wolloyewa
❥︎አምሀራዊት༆🧕🩷 :
ጨርሷ ያነበበ🥺
2026-08-19 08:21:11
485
lemlem.tameru
lemlem tameru :
fetarey yebarekachew nachew yewenet🥰🥰🥰🥰💕💕💕💕💕💕
2026-08-19 17:53:39
0
foziya7341
foziya🌹حسبي لله :
እንደኔ ሙሉዉን ያነበበ ላይክ🥰🥺
2026-08-19 11:31:52
252
sawed150
Typing... :
30አመትም ብሰራ አይወዱኝ የኔስ😁
2026-08-19 12:45:30
121
feti2455
feti🧕🦋👸🏻 :
እኔ እድሌ ሁኖ ፎቶና ሰው አይወጣልኝም😂
2026-08-19 16:26:46
57
tsionl87legese
ፂዬ21 5000kብቻ🇦🇪 &❤️⛪️💒🙏 :
እስከ መጨረሻዉ የነበበ😥
2026-08-19 09:13:42
74
mesaqnwamele
Güzel.💫 :
like አርጉኝ እንዳነበው መዳም ተራችኝ 🙌🏻
2026-08-19 12:59:09
45
ethio.3608
ሺአمት ላيኖر ሺماሠب ሞኝنት🤗 :
እነዚህን ጥሩ የሚባሉ ሠወችን የት ነው የሚያገኟቸው🥺
2026-08-19 14:07:42
14
madinaalii475
✝️ፍቅር የማርያም ልጂ✝️❤ :
ምን ዋጋ አለወ አሁን ለይ ግን ሀገሬ 😭😭😭😭😭 በደም ተጨማልቃለች 😭😭😭
2026-08-19 16:50:03
12
foziyaashawaa12
Fozii Mahammad :
maalidhaa
2026-08-19 14:02:04
5
asiya.mohamed75
Asiya Mohamed :
ቅመሞች ጀግና ናቸው ሁሉን ችለው ሀገርን አስከብረው ነው በሰው ሀገር የሚኖሩት
2026-08-19 11:41:27
30
sada.ahmed537
<<ሱሱ "ነኝ" የድኔ ተማሪ >> :
ከመጣሁ አመቴ ሶስት ልጆች አሉኝ እኔ ከለለሁ እሪ ነዉ የሚሉት እኔ ራሱ ስወዳቸዉ ቀጣይ ወዴ ኢትዮ ልንሄድ ነዉ ጉብኝት ,ኢንሻ አላህ ወላሂ ከአላህ በታች የሰዉ ፍቅር የተሰጠን ሰዎች ምንኛ የታደል ነን 🌺🌺🌺🌺
2026-08-19 14:36:02
9
user5094549934181
ዜድ ፀጉር ቤት ጅዳ💇🌸🐝 :
አገራችን ሰላም አርግልን ያራብ 🥰🥰🥰 እኛም ወደቀልባችን መልስን
2026-08-19 12:26:25
10
m6479965
መኖርስ በናት ሆድ 🦅❤️ :
እስከመጨረሻዉ ያነበበ🥰
2026-08-19 16:13:44
8
ruta04857
Ruta :
መታደል ነው ፈጣሪ እንዴቸት ሲወዳት ነው በፈጣሪ ፉቅር እንዴት ባረከች ኡፉፉፉፉፉ
2026-08-19 11:08:57
7
alhamdulillah61188
alhamdulillah :
የኔ ማሮች አላህ የሰዉ ፍቅር ይስጠን እንደኔ እስከመጨረሻዉ ያነበበ🥰🥰🥰🥰🥰
2026-08-19 10:09:51
9
hawa.hawa478
🅗 𝙬𝙤𝙡𝙡𝙤𝙮𝙚𝙬𝙖🇪🇹 :
🥰🥰🥰🥰ደግነት ለራስ ነው
2026-08-19 11:07:04
6
hadyamohamed8
Hነኝ የሀይቋ ወሎየ 🇵🇸🇵🇸🇪🇹🇪🇹 :
ማሻአላ 🥰🥰🥰ለሰው በላወችም አላህ ሂዳይስጣቸው
2026-08-19 06:47:49
7
ttttttt19997
የማይሆን ወግ :
ሥት መልካም አለ
2026-08-19 15:21:43
1
asdd1539
𝑻𝒊ያ᭄💎 𝐐𝐮𝐞𝐞𝐧👸᭄ያ𝑩𝒂ቷ᭄ :
🥺ጨርሽ አነበብኩት ደስይላል
2026-08-19 15:38:36
1
ese39b
𝓸𝓷𝓮 𝓭𝓪𝔂🧕 :
😥😥ንፁህ ልብ🥰🥰🥰
2026-08-19 14:08:25
1
tsaga2178
tsaga :
እንድ አይናት ፊቅሪም አሌ🥰🥰🥰
2026-08-19 11:15:13
3
dameintalbadiyaa
🌳🦅ام خالد🌏 :
Afaan Oromootii nuufii hikaa mee namii bekkataanii darbuufii garaan naa daadhabee😭
2026-08-19 15:41:25
3
To see more videos from user @tatek.media27, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About