@fuadmuna9: ቀን 6 ሳላወራሽ .... (ፉአድ ሙና) . አበባየሆሽ ለምለም፣ አድርሰናል እንደመባል ‘ሚቀፍ የለም። ሆ ብዬ መጣሁ ሆ ብዬ .... ፍቅሬ ካለሽ ብዬ፣ ሆ ብዬ መጣሁ ሆ ብዬ!! በእንቁጣጣሹ ጭፈራው ሲደምቅ፣ ሰማይ ሳትጠራ፣ ሆ ብሎ መምጣት አሰብኩኝና፣ ስስ ልቤ ፈራ። ፈሪ ነኝ እኮ .... ፈሪ ነኝ በጣም ያንቺ ፍቅር ነው፣ ስሱ ብልቴ፣ ላግባሽ ለማለት እንደምን ልድፈር፣ አልቆመም ቤቴ። በእኩለ ለሊት ገና ሳልጨርስ፣ እንጨት ሰበራ፣ አይመጥንሽም ነይ ግቢ መባል፣ ቤት ሳይሰራ። ፍቅርሽ ተራራው እያሳነሰው፣ በእጄ ያለን ሁሉ፣ ብትገዝፊብኝ .... ወላዋይ ብለሽ፣ አማሽኝ አሉ። ቆራጥ ነበርኩኝ .... ፍቅርሽ ነው እንጂ ያስደፋኝ አንገት፣ ነበርኩኝ ዋና፣ እጄን የማልሰጥ የማልሰፈር፣ በቆንጆ ቁና። ግን ተበለጥኩኝ .... አልገባሁሽም ታየ እንደሽንፈት፣ ስስት ፍቅሬ፣ አነስኩሽና ሌላ ሰው መርጠሽ፣ ቃል ሰጠሽ ማሬ። ቀልዴን ነው በይኝ!! አበባየሆሽ ለምለም፣ አድርሰናል እንደመባል፣ ‘ሚቀፍ የለም። ቀልድሽን ነው አውቅሻለሁ፣ አትጨክኚም በመውደዴ፣ ከቶ አልችልም አንቺን ማጣት፣ ለአፍታ ለአንዴ። ቀልድሽን ነው!! አሁን አሁን አይኔ ሲራብ፣ ፊትሽን ለምዶ፣ ፅልመት ሞላኝ ድምፅሽ ሲጎ‘ል፣ ከጆሮዬ ተዋህዶ። አዲስ አመት ሳላወራሽ ሳንተያይ፣ አበሰሩ፣ ያላንቺ ሳቅ መድመቅ ሽተው፣ ችቦ አበሩ። ኪሳራ!! እኔ ጋር ግን የፅልመት ጎርፍ፣ ይታየኛል ተጥለቅልቆ፣ ያላንቺ ድምፅ ያለሳቅሽ፣ ምሎልኛል ላይሄድ ለቅቆ። ልሰምጥ ነው!! ሲያዩኝ ብመስል፣ ያካበበኝ ድሎት ሞልቶ፣ ትንኝ ታክል፣ ልቤ አያውቅም ደስታ አይቶ፣ ራሪልኝ፣ ውስጤ አይንደድ አንቺን አጥቶ። ናፍቀሽኛል .... ደሙን ትቶ፣ ልቤ እንባ እስኪዘራ፣ አይኖቼ ላይ በስምሽ ቅርፅ፣ የደም መስመር እስኪሰራ። ንፍቅፍቅ ብለሽኛል። አበባየሆሽ ለምለም፣ አድርሰናል እንደመባል፣ ‘ሚቀፍ የለም። ናፍቀሽኛል!!! 20 ቀን እኮ ብዙ ነው!!! ያ ረብ ኢኒ ፈቂር!!!
Fuad Muna
Region: ET
Wednesday 19 August 2026 09:21:27 GMT
Music
Download
Comments
𝐌𝐞𝐛𝐫𝐢𝐧𝐚 🦋 :
አበባይሆሽ
ለምለም
አድርሰናል እንደመባል ሚቀፍ የለም 🥹🥹
2026-08-19 09:30:25
12
Emhale🧕 :
ፉአዴ ወረቀቷ ብትቀር ወንድሙ ግሬሱን ይቀንስብሀል አሂ ትኩረታችን ድምፅህ ላይ ሆኖ ስንኞቹን እንደመምባቸው ወንድሙ ብዙ አቅም አለህ 🤗❤
2026-08-19 09:59:21
14
jennah :
ሳላወራሽ😔
7 inshallah
2026-08-19 11:52:51
2
Sëbrï🦋_hïñā :
dimtsikin eskisema kenun yemikotir ene 😊
2026-08-19 09:38:45
1
حنان🇹🇷🍫 :
salafekr un getim yemradaw ene🥰
2026-08-19 19:05:00
1
strong women💪 :
ende fuad wellahi diro be telegram neber yamawuk wede tiktok mender enedemetah alawekum neber🥰🥰🥰
2026-08-19 13:17:50
1
𝑒𝑠𝑚𝑖𝑙𝑒 𝑠𝑢𝑙𝑡𝑎ን :
እየሞከር ነው ወላሂ
2026-08-20 04:08:07
1
H :
ሳላወራሺ 6
2026-08-19 09:27:58
1
muba its me🎇 :
beb eare 6 tu kenat eko adekemugne🥰🥰
2026-08-19 09:30:03
2
🤑🤬😎 :
kelden nw🥺
2026-08-19 16:33:47
1
ربي لا تذرني فردا🤲 :
era yh yanta gtm wellahi yilayal
2026-08-19 13:06:51
1
s̶i̶🦋 :
ፈሪ ነኝ እኮ ❤️🩹
2026-08-19 15:13:40
1
ጤናዳም 🌿 :
ፉአድ 💚
2026-08-19 09:26:28
1
Abudi Al-menan :
Endehulgize wendeme andegna 🫡
2026-08-20 11:31:09
2
Sude@ :
ኪሳራ🥺
2026-08-19 11:08:53
1
siiyy💫 :
Another one👏
2026-08-19 09:31:26
1
🦋🦋🦋 :
ቆራጥ ነበርኩኝ.......✌🥰✌🥰
2026-08-19 17:04:36
1
hurelin :
yarebi ine fekit 🥰🥰
fkre dichemer arekewu😓😓
2026-08-19 09:44:28
1
sumi :
💞
2026-08-19 09:35:02
2
Muzekir :
አድርሰናል እንደመባል ሚቀፍ የለም!
2026-08-19 17:11:30
1
nunu :
ፉሀድ ይህ የተቆራረጠ ወረቀት ሀሳቤንም ቆራረጠው እኮ እና ወጥ ነገር ቢሆን ጥሩ ነው!!!
2026-08-19 14:45:17
1
To see more videos from user @fuadmuna9, please go to the Tikwm
homepage.