@axumawi214: "መለስ" ሆይ እስቲ ጉዳችንን ስማን ልንገርህ እኛን አትጠይቀኝ በቁም ሞተናል እስቲ ትንሽ ላጫውትህ ግን አደራ እንዳትጨነቅ አሁን ከዚህ በታች የምትሰማው ሁሉ ኑሯችን ነው እንዳትደነግጥ! .**** አንተ ከሄድክበት ዓለም ሆኖ የልጆችን የልብ ምት መስማት ቢቻል ኖሮ፣ ይሄኔ የዚህች ምድር ጩኸትና የጦቢያ የልጆቿ የደከመ ትንፋሽ እረፍት ይነሳህ ነበር። እነሆ ዛሬ አንተ ከዚህች ምድር ከተለየኸን ሙሉ ዐሥራ አራት ዓመታት ተቆጠሩ። .**** ጊዜው እንዴት ይሮጣል? ግን ለአንተ ዓመታቱ ቢሮጡም፣ ለእኛ ግን እያንዳንዱ ቀን እንደ ሺህ ዓመት የከበደ፣ በፈተና እና በብቸኝነት የተሞላ ረጅም ጉዞ ነበር። ልክ አባቱን በድንገት ሳያስብ እንደተነጠቀና ሜዳ ላይ እንደቀረ ምስኪን ልጅ የገባንበትን አውሎ ንፋስና የገጠመንን የሕይወት ውጣ ውረድ ብታየው፣ ልብህ በሐዘን ይሰበር ነበር። እንኳንም አያለህን! .**** አባታችን መለስ ሆይ አንተ እኮ ለእኛ መሪ ብቻ አልነበርክም፤ የሀገሪቱ የቤቱ ዋልታ፣ የአዕምሮው ማዕበል፣ በማዕበል የተናወጠችውን መርከብ ወደ ወደብ የምታሻግር ብልህ መሪ ነበርክ። ደግሞም አሻግረሀን ብዙ አሳይተህን ነበር እኔም ሌላውም ስራህም ህያው ምስክር ነን! .**** ዓለም ያደነቀው አንደበተ ርቱዕነትህ፣ በዓለም መድረኮች ላይ እንደ ሻማ የምታበራው ጥልቅ ዕውቀትህ፣ ማንኛውንም ውስብስብ ችግር በአንድ ፅንሰ ሐሳብ ፈትተህ የምታስቀምጥበት ያ ድንቅ ብቃትህ ዛሬ እንዴት እንደናፈቀን ብታውቅ! ምኞቴ ነበር። .***** በዓለም ዙሪያ ያሉ ኃያላን አንተ ስትናገር ጆሮ ሰጥተው በመፍዘዝ የሚያዳምጡበት፣ የአፍሪካን ክብር በጫንቃህ ተሸክመህ ድምፅ የሌላቸውን ድምፅ የሆንክበት ያ ታላቅ ግርማ ሞገስህ የት ደረሰ? ብዪ ለመጠየቅ አስብ እና ለካስ እረፍት ላይ ነህ ብዪ ሳስብ ላለማስጨነቅ ዝም እላለሁ። .**** መለስ ሆይ አንተ ትተኸን ከሄድክ በኋላ… .**** እየውልህ አባቴ፤ አንተ ከሄድክ በኋላ እኛ ስንት ጦርነት፣ ስንት ስቃይ፣ ስንት በደል አሳለፍን መሰለህ? አንተ የገነባኸው የአንድነት ድልድይ ሲናድ፣ ወንድም በወንድሙ ላይ ሲነሳ፣ እናቶች የልጆቻቸውን አስከሬን ማቀፍ የዕለት ተዕለት ኑሯቸው ሲሆን በአይናችን አየን። .**** ትናንት በልማትና በዕድገት እናሸንፋለን ያልከን ድህነት ዛሬ መልኩን ቀይሮ መጣ፤ የሰው ልጅ ሕይወት እንደ ቅጠል ረገፈ። ወጣቶች ልክ እንደ ደርግ ዘመን በፍርሀት ድባብ ተከበዋል ዛሬ አንድ ወጣት ከኑሮ ውድነቱ ባሻገር እታፈስ ይሆን? የሚለው ስጋት እረፍት ነስቶታል! .**** የወጣቱ ተስፋ አልባነት ያስፈራል ያ ለነገው ተስፋ ታጭቶ የነበረው ወጣት ዛሬ ፊቱ በባዶነት ተሞልቷል። ሥራ አጥነቱ፣ የነገው ፍርሃትና የህልም አልባነቱ ገደል ውስጥ ከቶታል፤ ሀገሩን ጥሎ በየበረሃውና በየባሕሩ ለመሰደድ ይማስናል። .***** የኑሮው አላነሳብህም! ብዪ ነበር ግን አልቻልኩም! ዛሬ በየቤቱ ያለው የኑሮ ውድነት ቃላት አይገልጹትም። አንድ አባት ለልጆቹ የዕለት እንጀራ ማቅረብ አቅቶት አንገቱን ደፍቶ ሲያለቅስ ማየት የተለመደ ሆኗል። የድሃው ዕሮሮ ጣሪያ ሰማይ ነክቷል፤ የሕዝቡ ትዕግሥት ተሟጧል። .***** ዛሬ ህዝቡ በቤት ኪራይ ተማሯል አንዳንዱ ልጆቹን በትኖ ጎዳና ወጥቷል። አንዳንዶች የማያውቁት ሰፈር ሄደው ለምነው ሲመሽ ወደ ሰፈራቸው ይመለሳሉ። እንዲህ የምልህ ስራ ያላቸው የመንግስት መስሪያቤት የሚሰሩ ናቸው ከስራ በኋላ የማያውቁት ሰፈር ሄደው የሚለምኑት። .***** ይቺን ልጨምርልህ ደግሞ የማኅበራዊና ሃይማኖታዊ እሴቶቻችን ተደረማምሰዋል ቅጥ አጥተዋል ፡ አንተ አጥብቀህ የምትጠብቀው የሕዝቦች መከባበር፣ ያ የዘመናት አብሮነት እና የሃይማኖቶች መቻቻል ፈተና ላይ ወድቋል። በደምና በአጥንት የተገነባው ማኅበራዊ ማሰሪያችን ሲላላ፣ “አባት አልባ ሆንን” እያልን በየማዕዘኑ ህዝቡ ያነባል። .***** ስለ ፊንፊኔ ትንሽ ልንገርህ እና ልጨርስ ዛሬ አዲስ አበባን ብታያት በመንገዶቿና በሕንፃዎቿ ብልጭልጭ ነገሮች ተሞልታለች። የማነች የሚለው ጥያቄ እንዳለ ሆኖ ማለት ነው። መብራቶቹ ይበራሉ፣ አዳዲስ አስፋልቶች ተነጥፈዋል፤ ግን ያ አንተ ትፈራው የነበረው እውነት ዛሬ ገሃድ ሆኖ ቁጭ ብሏል።“ውበቱና ብልጭልጩ ቢበዛም፣ ሰው በገዛ ሀገሩና በመንደሩ ባይተዋር ሆኗል!” .**** የአዲስ አበባ ሕዝብ በዚያ ብልጭልጭ ገፅታ ውስጥ ሆኖ ውስጡ ግን በስቃይና በዋይታ ይቃጠላል። የፈረሰው ቤቱ፣ የተነጠቀው ትውስታው፣ በአካባቢው ላይ ያለው የባለቤትነት ስሜት መጥፋት ልቡን አድምቶታል። .***** ውጫዊው ግርማ ሞገስ የውስጡን የደስታ ማጣት ሊደብቀው አልቻለም። ሰው በገዛ ሀገሩ እንደ እንግዳ፣ በገዛ አፈሩ ላይ እንደ ባይተዋር ሆኖ አንገቱን ደፍቶ ይራመዳል፤ ፈገግታው የይስሙላ፣ ውስጡ ግን በለቅሶ የታጨቀ ነው። .**** መለስ ሆይ ዛሬ እኮ እውነተኛ መካሪ፣ በማዕበል መሀል ኮምፓስ ሆኖ አቅጣጫ የሚያሳይ አርቆ አሳቢ መሪ አጥተናል። ያ የአንተ የተረጋጋ፣ ጥልቅና አሳማኝ አመክንዮ ዛሬ በፉከራና በውዥንብር በግርግር ተተክቷል። ልክ ድንገት ጨለማ ውስጥ የቀረ ልጅ “አባቴ የት ነህ?” ብሎ እንደሚጣራ ሁሉ፣ ዛሬም ይህች ሀገርና ልጆቿ ያንተን ጥልቅ ዕውቀት፣ ያንተን ቆራጥነት እና የዳበረ የመሪነት ስብዕናህን በብርቱ ይናፍቃሉ። .***** ዐሥራ አራት ዓመታት አለፉ በዚህ ጊዜም በአንተ መሞት የሚደሰቱ ጮቤ የሚገርጡ መኖራቸውን ሳልነግርህ አላልፍም ነገር ግን እኛ ወዳጆችህ አሁን ድረስ በልባችን የፈጠርከው ክፍተት አልተሞላም፤ ያንተ ባዶነት ዛሬም እንደ ትኩስ ቁስል ያማል። .**** ነፍስህ በሰላም ትረፍ አባታችን፤ ስምህና ያ ድንቅ አሻራህ በታሪክ ማኅደር ውስጥ ለዘላለም ሲነበብ ይኖራል! #ትግራይ_ንዘለኣለም_ትነብር🙏🇻🇳 #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #eirtrean_tiktok🇪🇷🇪🇷🇪🇷eirtrean #አማራዬ💚💛❤አማራዬ💚💛❤ #oromotiktok

ኮድ 11💊🖤🤍
ኮድ 11💊🖤🤍
Open In TikTok:
Region: KR
Wednesday 19 August 2026 15:31:45 GMT
4284
373
18
44

Music

Download

Comments

samireby
alem :
we missed you my dear brother.
2026-08-19 19:51:18
0
helen.tesfiy
Helen Tesfiy :
ነብስህ በሰላም ትረፈ ጀግናው😭😭😭
2026-08-19 19:37:09
0
t.g111111
ምቅናይ ኩሉ ንምርኣይ :
ምልስ ኢልኻ ኣይትርኦዮ ዓድኻን ህዝብኻን😭💔😭
2026-08-19 19:37:33
0
yareda777eagle
Yare sisay :
ነብስህ በሰላም ትረፍ 🥹🥰
2026-08-19 17:03:14
0
rona111220
rona111220 :
2026-08-19 15:41:17
0
user8181111593097
user8181111593097 :
አይ መሪ አይ ግርማ ሞገስ
2026-08-19 16:48:54
0
ebenareb
የጌታ ልጅ :
2026-08-19 16:39:23
0
kimbeki257
THANKS GOD. 72 :
አባቴ ድሕርየኻ አይኸርናይ
2026-08-19 17:51:43
1
user9444713655282
🙏ብተስፋ ተሓጎስ ኣብ ፀበባ ተዓገስ🙏 :
ብድሕሬኻ ኢትዮጵያ ፀልሚቱዋ😌
2026-08-19 16:36:03
2
dinno.noah
ቀቀቀቀቀቀ :
እናሓደረ ዝደምቕ ስብአና❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
2026-08-19 15:52:41
1
fuhygbh965h
fuhygbh965h :
❤️❤️❤️
2026-08-19 16:00:31
1
ejrye.ejrye
Ejrye Ejrye :
😭😭😭🥰🥰🥰
2026-08-19 15:56:28
1
samialex9515
CReator.search.insight :
❤️❤️❤️
2026-08-19 16:11:38
1
tsge.mizan
ከም ፍቃድካ ይኩን ኣምላከይ :
😭😭😭
2026-08-19 19:24:36
0
melashu.fasam
mahlati :
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭
2026-08-19 19:35:24
0
joury20193
user2370580585009wayn :
😳😳😳
2026-08-19 19:40:43
0
organicadisabeba
ፍቁረ እግዚ :: ዬሐንስ ስፈሪ :
🥰🥰🥰
2026-08-19 19:03:40
0
abebeberhehailu
Abel :
no one live for ever tarik gin nahasasat kewagie tekoyine baalege ,Tigray gin tiyik dimocracy soon terebeza gun free
2026-08-19 15:36:37
0
To see more videos from user @axumawi214, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About