@natanimzerfu2: #ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ለ418 አገልጋዮች ሥልጣነት ሰጡ ነሐሴ ፲፫ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የቅዱስ ዜናማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ መሥራችና የበላይ ሓላፊ በዛሬው ዕለት ለ399 የአብነት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለነበሩ ደቀ መዛሙርት ዲቁናን እና ለ19 ዲያቆናት ደግሞ ቅስናን በወልቂጤ ደብረ ታቦር እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ሰጥተዋል። ሁሉም ሥልጣነ ክህነት የተቀበሉት በደብራቸው በአብነት መምህራኖቻቸው፣ በወረዳ ቤተ ክህነትና በሀገረ ስብከቱ የመመዘኛ ፈተና ተፈትነው ያለፉ መሆናቸው ታውቆአል። በሀገረ ስብከት ደረጃ በብፁዕነታቸው መመሪያ መሠረት ጥራት ያላቸው ካህናትን ለማፍራት ጥረቶች እየተደረጉ ሲሆን ይህ በየ እረከኑ የሚደረገው ፈተና ማሳያ ነው። ብፁዕነታቸው በጥልቅ መንፈሳዊ አደራና መመሪያ የተሞላ አባታዊ ምክር ያስተላለፉ ሲሆን በጸሎትና በጾም የጸናችሁ ሁኑ፣ በእውቀት ትበስሉና የቤተ ክርስቲያንን ክብርና የክህነትን አርአያነት በጽናት የምትጠብቁ መሆን ይገባችኋል ብለዋል። ብፁዕነታቸው ሲቀጥሉ ዘመኑ የሚጠይቀውን አገልግሎት ለመስጠትና እውነትን በበሰለ መንገድ ለማስተማር እንድትችሉ መንፈሳዊ ትምህርታችሁን ማሳደግ አለባችሁ፤ ከፍ ወዳለው የእውቀት ደረጃ ለመድረስ ጠንክራችሁ ተማሩ፤ ራሳችሁንም ሁልጊዜ በጥበብ ማነጽ ይኖርባችኋል በማለት በአጽንኦት ተናግረዋል። ብፁዕነታቸው ሲያጠቃልሉ በንግግራችሁ፣ በጠባያችሁ፣ በአለባበሳችሁ፣ በአኗኗራችሁና በምግባራችሁ ለምእመናን መልካም አብነት በመሆን የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓትና ታሪክ የመጠበቅና የማስጠበቅ ግዴታ አለባችሁ በማለት አባታዊ መመሪያቸውን ሰጥተዋል።

ኤማ ሚዲያ Emma Media
ኤማ ሚዲያ Emma Media
Open In TikTok:
Region: ET
Wednesday 19 August 2026 17:30:45 GMT
487
145
0
7

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @natanimzerfu2, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About