@wasumohammed: የአዲስ አበባ ጉዳይ...‼ በአገራዊ የምክክር ጉባዔ የአዲስ አበባና የድሬዳዋ የወደፊት ህጋዊ ማዕቀፍ ምክረ-ሀሳብ ይፋ ሆነ‼ ለ35 ቀናት ሲካሄድ የቆየው ዋናው አገራዊ የምክክር ጉባዔ የስምንቱን አጀንዳዎች አንድ ወጥ ምክረ-ሀሳብና ቃለ-ጉባዔ ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ የበርካታ ህዝብ ትኩረት የሆነው የአዲስ አበባ ጉዳይም እልባት የሚያገኙበት አማራጮች ተቀምጠውለታል። ስለ አዲስ አበባ የቀረቡ ዋና ዋና ምክረ-ሀሳቦች፡ 📌ተጠሪነት፡ አዲስ አበባ ተጠሪነቷ ለፌዴራል መንግስት እንዲሆን በተመካካሪዎች ሙሉ ስምምነት ተደርሷል። 📌የጋራ ጥቅም፡ ቀደም ሲል የነበረው "ልዩ ጥቅም" የሚለው አባባል "የጋራ ጥቅም" በሚል ተተክቶ እንዲካተት ተደርጓል። 📌የኦሮሚያ ክልል መቀመጫነት፡ ከተማዋ የክልሉ ዋና መቀመጫ እንድትሆን በቀረበው ሀሳብ ላይ ሁለት አማራጮች ተቀምጠዋል፤ ሁሉም ክልሎች ርዕሰ ከተማቸውን በነጻነት መምረጥ እንደሚችሉ በሕግ እንዲደነገግ። በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 49(5) መሰረት በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል መካከል ያለው ግንኙነት በሕግ እንዲወሰን። 📌ድሬዳዋ፡ ድሬዳዋ በሕገ-መንግስቱ እውቅና በተሰጠው ቻርተር እየተዳደረች ተጠሪነቷ ለፌዴራል መንግስት እንዲሆን ተመክሯል። ይህ በአዘጋጅ ቡድኑ ተዘጋጅቶ የቀረበው ቃለ-ጉባዔ በነገው ዕለት በ4 ሺህ የጉባዔው ተሳታፊዎች ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል ሲል ቲክቫህ አጋርቷል።። video 👇Like + Follow👇 https://www.facebook.com/share/18ZGvgBVhp/?mibextid=wwXIfr ==================== ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 #WasuMohammed #breakingnews #tiktok #foryou #foryoupage
Wasu Mohammed 📌
Region: ET
Wednesday 19 August 2026 20:11:58 GMT
Music
Download
Comments
madina :
ewent new mnm terribly yelewm
2026-08-21 04:28:30
0
የናግራው ገብርኤል ❤19 :
ስላሴ አንድም ሶስትም ናችው 🙏🙏
2026-08-19 20:33:51
34
United for Peace :
Nothing givez any sense!
2026-08-20 08:24:47
2
ለበጎ ነው :
የኔ ጀግና መንግስት የሚሆነውን ጠንቅቆ ያውቃል
ጥሩ ውሳኔ ነው
2026-08-19 20:23:15
7
John Abate :
yihe nw tikikil
2026-08-20 04:49:16
0
name :
ህውሀት ሊጀራደሩ ነው የሚለው ዘገባ የተሳሳተ ነው ከየት አመጣሀው
2026-08-20 07:53:12
2
Football Fan :
ahun new bitibit
2026-08-20 06:22:10
4
🎧 Safari_Com☑️ :
እኛ ሰላም ነው የምንፈልገው መጀመሪያ
2026-08-20 11:58:43
0
user2334175039021 :
ከተሞች በጠቅላላ በፌደራል መንግስት ቢተዳደሩ ጥሩ ነበር
2026-08-20 12:47:19
2
Chali Petros :
ላለፉት 35 ቀናት በአዲስ አበባ/ፊንፊኔ ሲካሄድ የቆየው ሀገራዊ ምክክር ዛሬ የውሳኔ ሀሳቦችን በማቅረብ አጠናቋል።
ከውሳኔ ሀሳቦቹ መካከልም አዲስ አበባ/ፊንፊኔ የኦሮሚያ ዋና ከተማ መሆኗ ሕገ መንግሥታዊ እውቅና እንዲያገኝ የሚለው ይገኝበታል።
2026-08-21 20:01:50
0
ሰው ነኝ jemal :
የሚያጣላን ሌላ አጀንዳቸው ሌላ
2026-08-19 20:34:03
5
Abiy Tegegn :
አሁንስ ይሄ ወሬ እንደኔ የሰለቸው ላይክ
2026-08-20 12:51:40
2
it :
🇪🇹 ዝናብ የለም ወይ ዘንድሮ
2026-08-20 18:11:04
1
Meskerem Takele :
ስሙ። ምክክር ቢኖር። ሀገሬ የት በደረሰች
2026-08-20 04:25:47
2
endalebezabih0 :
ሀሉም የኔ ማለት የራስህንም ሊያሳጣህ የችላል........
2026-08-20 14:53:03
0
💫💥Hassuu AD🇪🇹💥🌙 :
❤️❤️❤️
2026-08-19 20:17:46
0
محمد عخمد :
አድስ አበባ የፌድራል ከሆነ ሀሪፍ ነው
2026-08-20 22:15:46
0
አስተውል :
ተወው ሞኙ እኔ ነኝ ይሔንን "የሴራ ምክክር" መሆኑን አለማወቄ
2026-08-20 10:29:35
0
ጀማል ፈንታው :
እንደፈለጋችሁ አርጉት
2026-08-21 12:12:56
0
user3325449955708 :
ሀገሬእየመከረችነዉእዉነትም
2026-08-19 20:30:11
0
one day 2 :
በጣም ጥሩ ዉሳኔ
2026-08-20 07:58:30
1
hawww :
ዉሉምክልል።መቃመጨ።ፍንፍኔይሁንበቃ።
2026-08-20 00:25:07
3
To see more videos from user @wasumohammed, please go to the Tikwm
homepage.