@behajanews: የመንግስት ጥብቅ የተፈጥሮ ደን ዛፍ ቆርጠው ተሸክመው ሲሄዱ እጅ ከፍንጅ የተያዙ አካላት በእስራትና በገንዘብ ተቀጡ አርባምንጭ ፣ነሐሴ 13/2018 ዓ፣ም(አርባ ምንጭ ከተማ መ/ኮሚዩኒኬሽን) የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት በአርባምንጭ ከተማ በመንግስት ይዞታ ጥብቅ የተፈጥሮ ደን ውስጥ የደን ዛፍ ቆርጠው ተሸክመው ሲሄዱ እጅ ከፍንጅ የተያዙ አካላት ላይ የእስራትና የገንዘብ ቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል። የአርባምንጭ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተከሳሾች የኢ.ፌ.ድ.ሪ.ወ.ህግ አንቀጽ 32(1)(ሀ) እና የደን ልማት ጥበቃ እና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 1065/2010 አንቀጽ 25(4) (ሀ) እና (ሠ ) 26(1) የተደነገገዉን በመተላለፋቸው አንድ ዓመት ከስድስት ወር እስራት እና በ10,000 ( አስር ሺ ) ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል ። ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በቀን ዐ8/12/2018 ዓ/ም በግምት ከምሽቱ 1፡30 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ ያለፈቃድ በህገወጥ መንገድ ወደ አርባምንጭ ጥብቅ ደን ውስጥ በመግባት ተጠብቆና ተከልሎ ካለው ደን የማገዶ እንጨት በመቁረጥ እያንዳንዳቸው አንዳንድ ሸክም በድምሩ 12 ሸክም በጀርባቸው እንደተሸከሙ እጅ ፍንጅ በመያዛቸው በፈጸሙት የደን ውጤት የሆነውን እንጨት ይዞ በመገኘት ወንጀል ተከሰዋል። ወንጀሉን የፈጸሙት ግለሰቦቹ 1ኛ አልማዝ ድርሳ፣ 2ኛ/ ማርታ ማዣ፣3ኛ ዓይናለም ባቤና፣ 4ኛ/ ገነት አባ ፣5ኛ/ ገነት ኡፎ ፣ 6ኛ/ መቅደስ ጠጆ፣ 7ኛ/ ዓለም አበበ ፣ 8ኛ/ ኩንታሬ ኩካ ፣ 9ኛ/ ሴጌቴ ሳቦ ፣ 10ኛ/ አማረች ዝዳ ፣ 11ኛ/ ትዕግስት ሹርካ እና 12ኛ/ አንዷለም አብይ እንደሆኑ የክሱ መዝገብ ያሳያል። የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ውሳኔው የኢ.ፌ.ድ.ሪ.ወ.ህግ አንቀጽ 32(1)(ሀ) እና የደን ልማት ጥበቃ እና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 1065/2010 አንቀጽ 25(4) ሠ) እና 26(1) የተደነገገዉን ድንጋጌ በመተላለፍ የቀረበ መሆኑን የገለፀ ሲሆን ሌሎችን ከመሰል የወንጀል ድርጊቶች ለማስተማር የተላለፈ ውሳኔ እንደሆነም አመላክቷል። የአርባምንጭ ከተማ ፍትህ መምሪያ በበኩሉ ውሳኔው በተደጋጋሚ እየተፈፀመ የሚገኘውን ወንጀል ለማስቆም ፈጣንና ፍትሃዊ መሆኑን ገልፆ በተለይም የበርካታ ብዝኃ ሕይወት መገኛና ውድ ሥነ-ምህዳርን በታቀፈው ነጭ ሳር ብሔራዊ ፓርክና የአርባምንጭ የተፈጥሮ ደን ላይ የሚደርስ ጉዳትን ለማስቀረት የሚያግዝ እንደሆነም አስታውቋል። በአሰፋ ጪሻ #behajanews #ethiopiannews #እናቶች #ችግኝ #አርባምንጭ

BEHAJA NEWS
BEHAJA NEWS
Open In TikTok:
Region: ET
Thursday 20 August 2026 04:24:35 GMT
35633
2521
228
549

Music

Download

Comments

sahlemareyam21
ኢዮራም :
ህግ ድሀ ላይ የሚበረታው ለምንድን ነው
2026-08-20 07:34:27
141
abdurehim56
abdurehim56 :
ከቲባው ይታሰርልን
2026-08-20 04:38:57
172
mikiyasbezabih2127
miko bezabih21 27 :
yemote hager west new yenew
2026-08-20 05:10:21
0
raya22685
Raya :
የፈረሰ መግስት
2026-08-20 04:31:17
146
mesaybekele
ናታኔም&አምነን :
are tewun begeta sew yenurebet
2026-08-20 10:15:21
0
hnn5550
habtìsh :
ሀንግ የሰራው በ3ወር ሲፈታ እናቶችን 1አመት ከ 6 ወር
2026-08-20 07:06:26
58
abhunehara
ብርሀኑ :
የክልሉ መንግስት እራሱ መታሰር አለበት
2026-08-20 07:47:47
18
geez3000
Geez🇪🇹🇪🇹🇪🇹 :
asafary!!!
2026-08-20 08:13:20
1
user5692919807423
Gashu :
😭😭😭😭😭😭😭😭😭 yet ager new
2026-08-20 09:41:59
0
abysis06
siab :
እንደው እንደ ብልፅግና አይነት ጉድ እርግማን ነው
2026-08-20 05:21:50
21
rohobot_media
Rohobot Media :
1 አመት🙄🙄ይሁን 10,000 ይሄ ቢኖር ይሸከሙ ነበር 🤔🤔🤔
2026-08-20 05:59:38
5
mustefaebado
@Mustafi :
አይ ሀገሬ ድሆች እንዳይበሉ ሚከለከልባት ሀገር 😥😥😥😥😥
2026-08-20 04:34:28
32
soliethiopia612
lôlĩťâ :
መንግስት ድህነትን ሳይሆን ድሀን ለማትፋት ቆርጦ ተነስቷል
2026-08-20 10:37:26
16
nuruseid12
nuru seid :
ጉድ በል ጎንዴር ኑሮአቸው እንደመቀየር እስር እና ገንዘብ ቅጣት
2026-08-20 05:47:04
15
_daviloa_
dawit :
eeeeee
2026-08-20 08:50:35
0
joshwa1400
josh :
ከአውሬ ለይቼ ማላየው መንግስት
2026-08-20 05:33:11
13
user22372387935666
mame :
እናቶች ናቸው መታሰር የለባቸውም
2026-08-20 04:37:08
16
tek.stgonder
አባዝምታ :
ኡኡኡኡኡኡኡ እረ ይሄን መንግስት አንድ እንበለው ጎበዝ
2026-08-20 04:33:24
8
zihdkrh
zinash :
እናት ባትራብ እጨት አትለቅምም አይ እናት ሀገሬ ያሳዝናል
2026-08-20 05:24:30
5
me.my.son
1 SOl :
ህግ ድሀ ላይ ነው የሚሰራው 😏
2026-08-20 09:36:16
2
a968259655
Arsenal / win :
ere mengist tew
2026-08-20 07:56:00
3
ferhandicor
dicor ዲኮር ferhan :
መቼስ እርጥብ አይቆርጡ .. ለማገዶ .. የደረቀ ጭራሮ የረገፈ ቅጠል ጠርገው ኑሮን በታገሉ...😭😭😭😭
2026-08-20 14:30:33
1
yirgalemminale
YirgaNafu@4321 :
አይ ሀገር
2026-08-20 06:17:21
2
jorga106
jorga :
ምን ማለት ነው አልገባኝም ቀልድ ነወ በለኝ
2026-08-20 07:35:08
3
n432217t
natanem :
አይ አገሬ ያሳዝናል
2026-08-20 04:34:11
5
To see more videos from user @behajanews, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About