@abdulfetahou1: የዑመር ኢብኑል ኸጧብ🤎 አገልጋይ የነበረው አስለም እንዲህ ሲል ይተርካል: በአንድ ሌሊት ከዑመር ኢብኑ አል-ኸጣብ🤎 ጋር የሕዝባቸውን ሁኔታ ለመቃኘት ከመዲና ወጥተን ጋር ወደ ሐረቱ-ዋቂም ወደተባለ ስፍራ አመራን። ሱራር በተባለ ቦታ ስንደርስ በሩቅ እሳት ታየን። ዑመርም «አስለም ሆይ! ብርዱና ሌሊቱ ያስቆማቸው መንገደኞች ይታዩኛል፤ ወደ እነሱ እንሂድ» አሉኝ። በፍጥነት ስንቀርብ አንዲትን እናት ከሕፃናት ልጆቿ ጋር አገኘን፤ እሳቱ ላይ ድስት ተጥዷል፣ ልጆቿም ያለቅሳሉ። ዑመርም🤎 «አሠላሙ ዐለይኩም ያ አሥሐበድ-ደውእ (የብርሃኑ ባለቤቶች)» አሉ — «የእሳቱ ባለቤቶች» ማለትን ጠልተው ነው። እሷም «ወዐለይኩም አሠላም» አለች። ዑመር🤎 «ወደ እናንተ ልቅረብ (ልጠጋ)?» ሲሉ ጠየቁ። ሴቲቱም «በበጎ ከሆነ ቅረብ፣ ካልሆነ ግን ተወን» አለች። ቀረብ ብለውም «ምን አጋጠማችሁ?» አሏት። እሷም «ሌሊቱና ብርዱ ጉዟችንን አሰናከለን» አለች። ዑመር «እነዚህ ሕፃናት ለምን ያለቅሳሉ?» አሏት። «በረሃብ ምክንያት ነው» አለች። «በዚህ ድስት ውስጥ ያለው ምንድን ነው?» ሲሉ ጠየቋት። «ልጆቹ እስኪተኙ እያፈላሁ የማታልልበት ውኃ ነው፤ አላህ በእኛና በዑመር መካከል ይፍረድ!» አለች። ዑመርም «አላህ ይዘንልሽ! ዑመር የእናንተን ሁኔታ እንዴት ሊያውቅ ይችላል?» አሏት። እሷም «የእኛን ጉዳይ ተረክቦ ከዚያ በእኛ ይዘናጋል?» ብላ መለሰች። በንግግሯ የደነገጡት ዑመር 🤎 «ተከተለኝ እንሂድ!» አሉኝ። በፍጥነት ወደ ዱቄት ማከማቻ ቤት (ዳሩድ-ደቂቅ) ሄድን። አንድ የዱቄት ከረጢትና የስጋ ስብ አውጥተው «በጀርባዬ ላይ ጫንልኝ» አሉኝ። እኔም «እኔ ልሸከምልዎ?» ብላቸው «በቂያማ ቀን ወንጀሌን ትሸከምልኛለህ?» አሉኝ በቁጣ። በጀርባቸው ላይ ጫንኩላቸውና በፍጥነት ወደ እናትየው ተመለስን። ዑመር🤎 የዱቄቱንና የሥቡን ጥቂት ክፍል ድስቱ ውስጥ አድርገው «እኔ አማስልልሻለሁ፤ አንቺ ዱቄቱን ነስንሺልኝ» አሏት። ከድስቱም ሥር እሳቱን እየነፉ ያቀጣጥሉ ጀመር፤ ከዚያም ድስቱን አወረዱት። ቀጥሎም፡ «የሚበሉበት እቃ አምጪልኝ» አሏት፤ ሰፊ እቃ (ሳህን) አቀበለቻችውና ምግቡን አደረጉላት። ከዚያም ለሴቲቱ፡ «አንቺ መግቢያቸው፤ እኔ ደግሞ አቀዝቅዝላቸዋለሁ» አሏት። እስኪጠግቡ ድረስ ማብላታቸውን አላቆሙም፤ የቀረውንም ምግብ እሷ ዘንድ ትተውላት ተነሱ፤ እኔም አብሬ ተነሣሁ። ሴቲቱም፡ «አላህ መልካም ምንዳህን ይክፈልህ! ከምእመናን መሪ (ከዑመር) ይልቅ ለዚህ ሥልጣን የተገባኸው አንተ ነበርክ» አለች። እርሳቸውም፡ «ወደ ምእመናን መሪ ዘንድ በመጣሽ ጊዜ መልካም ነገርን ተናገሪ፤ አላህ ካለ እዚያ ታገኚኛለሽ» አሏት። ከዚያም ከእሷ ዘወር ብለው ፈቀቅ አሉና በርከክ ብለው ተቀመጡ። እኔም፡ «ከዚህ ሌላ የምናከናውነው ጉዳይ አለንኮ» አልኳቸው፤ እርሳቸው ግን ምንም አልመለሱልኝም። ህፃናቱ ሲጫወቱና ሲስቁ፣ ከዚያም ተኝተው እስኪረጉ ድረስ ይመለከቷቸው ነበር። ከዚያም፡ «አስለም ሆይ! ረሀብ አሳድሯቸውና አስለቅሷቸው ነበር፤ ስለዚህ ያየሁትን ደስታና እርጋታ ሳላይ መመለስ አልፈለግኩም ነበር» አሉኝ።» ይለናል አስለም። በንጋታው እናትየው ወደ መዲና ሄዳ የዑመርን ማረፊያ ጠይቃ ገባች። ያ ማታ የረዳት ሰው አሚሩል ሙእሚኒን ተብሎ ከሶሐቦች መካከል ተቀምጦ ባየች ጊዜ ዑመር መሆኑን አውቃ ስጋት ያዛት። ዑመርም 🤎 «አንቺ እናት ሆይ! ምንም ስጋት አይግባሽ፤ በደልሽን ከአንቺ ልገዛሽ እንጂ ሌላ አይደለም፣ በስንት ልግዛሽ?» አሏት። በአርባ ድርሃም ከተስማሙ በኋላ ለፀሐፊያቸው «በርግጥም ዑመር ከዚች እናት በደሏን በአርባ ድርሃም ገዝቷል» ብለው እንዲጽፍ አዘዙ። ዐሊይንና ዑሥማንን (ረ.ዐ) ምስክር አድርገው ደብዳቤውን ለሶሐቦች በመስጠት « በሞትኩ ጊዜ ይህን ደብዳቤ ከከፈኔ መካከል አድርጋችሁ ቅበሩኝ፤ አላህን በእሱ እንድገናኘው» አሉ።
عبدالفتاح🖋️ Abdulfetah
Region: ET
Thursday 20 August 2026 04:51:10 GMT
Music
Download
Comments
Meقሙ 🌍 :
እኛ ግን ሰዎችን ስንበድል ልበችን ለምነ አይደነግጥም አለህ ይዛንልን
2026-08-20 06:56:36
7
( )حا :
mashaallah gobez tsehafi neh allah ytebkh
2026-08-20 05:32:50
7
A' b d :
Abdu🔥
2026-08-20 05:53:46
3
seadi the first :
wendmachn Allah ytebkh ☺️☺️☺️☺️
2026-08-20 05:00:24
1
🎀ነብያት🎀 :
ማሻ አላህ🌷🔥
2026-08-20 06:25:47
2
•ೋ°❀بنت مُحمّد❀°ೋ•|ɾιɱ :
mashallah jezakelah heyran 🥰
2026-08-20 10:46:03
1
hidaya👒 :
first🙌🙌
2026-08-20 04:57:36
1
نعيمه :
ማሻ አላህ አላህ ይጠብቅህ ወንድሜችን
2026-08-20 10:13:33
1
ለይቤዥ እለቦዥ😌🦋💝 :
ማሻ አላህ አላህ እውቀት ይጨምርልህ በርታ🦁
2026-08-20 10:01:11
1
𝓗𝓐𝓑𝓲𝓑𝓐💗🎧 :
🥰🥰🥰👌
2026-08-20 05:31:49
0
راحة نفسية 🎧🤍 :
mash allah
mash allah
2026-08-21 11:52:55
0
Fa فضيله እትዮጵያን :
መሸአለህ
2026-08-26 07:29:34
0
هيت بنت بابا 🧕🕌🕋 :
ማሻ አላህ አላህ ይጠብቅህ
2026-08-22 09:04:32
0
ሙና🦋 :
ኢንሻላህ🥰🥰🥰
2026-08-20 05:32:38
0
Rmn Muslim girl 🧕🌙 :
sübhanallah 🥺🥰
2026-09-23 08:57:18
0
ይታደሉታል እንጂ አይታገሉትም :
2026-08-20 21:01:52
0
እሙ ኢብራሂም የልጅዎ ናፋቂ :
🥰🥰🥰
2026-09-16 17:42:19
0
𝐋𝐞𝐲𝐥𝐚🦋 :
🥰🥰🥰
2026-08-20 16:29:41
0
𝖒𝖊𝖐𝖋𝖎𝖗𝖆🌱ماكفيرا🧕 :
ማሻአላህ🥰🥰
2026-08-20 11:43:23
0
ربي زدني علما 🇪🇹 🍂Léña :
ማሻ አላህ
2026-08-20 13:35:21
0
ልዩሰጦታለጀማውበሙሉ :
2026-10-03 08:58:21
0
ኢላሀም :
ማሻ አላህ
2026-08-20 16:14:38
0
✍️Hayu🦅📚ወሎየዋ🌺 :
ማሻአላህ ወድሜአላህይጨምርልህ🥰🥰
2026-08-20 15:42:22
1
L̺j̺l̺ A̺j̺s̺h̺a̺..,🧕 :
ማሻ አላህ🥰
2026-08-20 14:37:06
0
Munna Munna :
ማሻአላህ
2026-08-20 05:52:34
0
To see more videos from user @abdulfetahou1, please go to the Tikwm
homepage.