@natanimzerfu2: በዮንበር መንበረ ብርሃን አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም አጥቢያ ያሉ ከ200 በላይ ምእመናን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀበሉ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጉራጌ ሀገረ ስብከት በእዣ ወረዳ ቤተ ክህነት የሚገኘው በዮንበር መንበረ ብርሃን አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም አጥቢያ የሚኖሩ ከ200 በላይ ምእመናን፣ በበዓለ ደብረ ታቦር በኅብረት ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀብለዋል። ይህም በገዳሙ ዙሪያ የሚኖሩ አጠቃላይ የአካባቢው ምእመናን ቁጥር ጥቂት ቢሆንም እንኳን ሁሉም ምእመናን ለዚህ ታላቅ ክብር መብቃታቸው ልዩ ያደርገዋል። ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ለወንጌል አገልግሎት እና ምእመናን ንስሐ ገብተው ሥጋ ወደሙን እንዲቀበሉ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው የማስተማራቸው ውጤት ነው። ምእመናን ለዚህ ክብር መብቃታቸው የብፁዕነታቸው መመሪያዎች ሲሆኑ የገዳሙ የበላይ ጠባቂ የሆኑት ሊቀ ብርሃናት ኃይሉ ወ/ኢየሱስም ከፍተኛ የሆነ ጥረት መሆኑ ተገልጿል። ምእመናኑ ለዚህ ታላቅ የምስጢር ተሳታፊ እንዲሆኑ በሦስት የንስሐ አባቶች አማካኝነት ተከታታይ የሃይማኖት ትምህርት ሲማሩና የንስሐ ሕይወታቸውን ሲያስተካክሉ ቆይተዋል። የአካባቢው ተወላጅ የሆኑ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ምእመናኑን በማስተማርና በማበረታታት በኩል ከፍተኛ እገዛና በጎ አስተዋጽኦ አድርገዋል። ሙሉውን ምእመን አስተምሮ ለቅዱስ ቍርባን ማብቃት ብርቱ ጥረትና ድካም የሚጠይቅ ቢሆንም፣ የጥንካሬቸው ውጤት የሆነው ይህ የወንጌል ፍሬ በመበቀሉ ምእመናኑና ካህናቱ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቷቸዋል። ይህ መርሐ ግብር የተከናወነው በገዳሙ ጠንካራ መንፈሳዊ አገልግሎት በንስሐ አባቶች ብርቱ ጥረትና በመላው የገዳሙ ተወላጆች የተቀናጀ፣የተናበበ በፍቅር የተሞላ አሠራር መሠረት ነው። ሥጋ ወደሙ የክርስትና ሕይወት ዋና መድረሻና ግብ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ የዮንበር መንበረ ብርሃን አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም ምእመናን ያሳዩት ይህ የህብረት መንፈስ ለሌሎች አብያተ ክርስቲያናትና አካባቢዎች ታላቅ አርአያና አብነት የሚሆን መልካም መንፈሳዊ አገልግሎት ነው ተብሏል። ሳሌም
ኤማ ሚዲያ Emma Media
Region: ET
Thursday 20 August 2026 12:28:08 GMT
Music
Download
Comments
እሙ የኪዲዬ ልጅ(16) :
እግዚአብሔር ይመስገን 🙏🙏🙏
2026-08-20 12:33:01
1
@ sokem ✝️ 💪 :
🥰🥰🥰
2026-09-02 10:21:36
0
ክንፈ ሚካኤል (ቡሩክ) :
🥰🥰🥰
2026-08-20 17:20:33
0
የኔ ዓለም ሲራክ :
❤️❤️❤️
2026-08-20 13:23:41
0
yeshi_.77 :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-09-14 19:59:10
0
To see more videos from user @natanimzerfu2, please go to the Tikwm
homepage.