@jomom90: በወልቃይት ጠገዴ መዘጋ ወልቃይት የሚገኘው የስኳር ፋብሪካ፡ የህዝብ እንባ፣ ሀገራዊ ቁጭት እና ተጠያቂነትን የሚጠይቅ ድምፅ! በወልቃይት ወረዳ መዘጋ አካባቢ የሚገኘው ይህ ግዙፍ የስኳር ልማት ፕሮጀክት 85% አልቆ ለምረቃ 15% ብቻ ሲቀረው ስራ መቆሙ ያነሰ ይመስል፤ ዛሬ የሌቦችና የዘራፊዎች መጫወቻ ሲሆን ዝም ብሎ ማየት የታሪክም የሕሊናም ተጠያቂነት ያመጣል! ይህንን ሀቅ የዛሬ ሁለትና ሶስት ዓመትም ቢሆን በቁጭት ስናገር፣ ስሞግትና ድምፅ ስጮህ ነበር። ዛሬም ቢሆን አልደክምም! ምክንያቱም ይህ ፕሮጀክት በህዝብ ሀብት፣ በህዝብ ላብና ጉልበት የተገነባ እንጂ የጥቂት ግለሰቦች ወይም ቡድኖች የግል ንብረት አይደለም! 1. ይህ ፕሮጀክት ቢጠናቀቅ ኖሮ ምን ይዞልን ይመጣ ነበር? ለወጣቶች ስራ እድል፡ በሺዎች የሚቆጠሩ የአካባቢውና የሀገራችን ወጣቶች የቋሚ ስራ ባለቤት ይሆኑ ነበር። ወጣቱ ተስፋ ቆርቆሮ ሀገሩንና ቀዬውን ጠልቶ ከሚሰደድ፣ በባህርና በበረሃ ከመቅረት ይታደገው ነበር። ሀገራዊ የኢኮኖሚ አቅም፡ የሀገር ውስጥ የስኳር ፍላጎትን በማሟላት በቢሊዮን የሚቆጠር የውጭ ምንዛሬን ያድን ነበር። 2. የደረሰው ጉዳትና የዛሬው እውነታ፡ በወቅቱ ህወሓት በፈፀመው ጥቃት በቦታው ጥበቃ ያደርጉ የነበሩ የፌደራል ፖሊስ አባላትን ገድሎ ስለሄደ፣ በዛ ምክንያት በተፈጠረው የጥበቃና የደህንነት ክፍተት (በገባው ንፋስ) ሳቢያ ፋብሪካው ለጉዳት ተዳረገ። ያ አልበቃ ብሎ እስካሁንም ድረስ "ስርቆትን እንደ ዋና ስራ ተያይዘውታል" በሚባሉ፣ ከታች እስከ ላይ ባሉና ህዝቡ በግልፅ የሚያውቃቸው አካላት የአሉሚኒየም፣ የበራ ብረትና የማሽነሪ ክፍሎች የዘረፋ ሲሳይ እየሆኑ ይገኛሉ። 3. ለኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽንና ለሚመለከታቸው አካላት የቀረበ ሀገራዊ ጥያቄ፦ ፕሮጀክቱ እዚህ ደረጃ ደርሶ መቆም አለበት ወይ? 85% ያለቀን ፕሮጀክት በ15% ምክንያት ወድቆ እንዲቀር ማድረግ የታሪክ ስህተት ነው! በክብር ተጠብቆ ለምን አይቆይም? ስራውን መቀጠል እንኳን ባይቻል፣ ሁኔታዎች እስኪስተካከሉ ድረስ ይህ የህዝብ ሀብት በፀጥታ አካላትና በኮርፖሬሽኑ ተጠብቆ ለምን አይቆይም? ተጠያቂነት የት አለ? ህዝቡ በግልፅ የሚያውቃቸው ዘራፊዎች እያሉ በመንግስት አካላት በኩል ለምን እርምጃ አይወሰድባቸውም? ጥሪያችን፦ ለኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን፣ ለፌደራልና ለአካባቢው አስተዳደር አካላት! ይህ ሀብት የደሃው ህዝብ ላብና እንባ አለበት። በአስቸኳይ፡ የፋብሪካው መሰረተ ልማትና ማሽነሪዎች ጥበቃ ተደርጎላቸው ዘረፋው በጽኑ ይቁም! በዘረፋው ላይ የተሰማሩት ከታች እስከ ላይ ያሉ አካላት በህግ ፊት ይቅረቡ! የቀረው 15% ስራ የሚጠናቀቅበትና ወጣቶች ወደ ስራ የሚገቡበት መንገድ በፍጥነት ይመቻች! እኛ አዲስ ልማትና ሀብት ልናፈራ እየተጋን ባለንበት ወቅት፣ በእጃችን ያለውንና ያለቀውን ሀብት በዚህ መልክ ማጣታችን ያመማል! የተጀመረ ነገር "ተጀምሮ ቀረ" ተብሎ አይተውም። የህዝብ ሀብት አይዘረፍም፤ የልማት ተስፋችን አይዘጋም! በዚህ ሁለተኛ ግዜ ስመጣ ግን በከፋ መልኩ ነው #ethiopian_tik_tok #Amharatiktok #tigraytiktok🇻🇳🇻🇳tigraytiktok #eritreantiktok🇪🇷🇪🇷habesha @Ashete Demlew @kbrab welkayt @helen hafte @ታዘባቸዉ ዘ ወልቃይት ጠገዴ 8ቱ ማይቤት ◊🔹 @Haftu Dejen Alemayoh @yonas welkayt
ያዳሙ ልጅ✅ 👑☠️
Region: GB
Thursday 20 August 2026 18:44:09 GMT
Music
Download
Comments
ጥቁር ሞሳድ :
ስፈልጋት የነበረችው ቪድዮ ነው ያነሳሀው tanxx bro
2026-08-20 23:04:26
1
ያዳሙ ልጅ✅ 👑☠️ :
ቢያንስ Sher Riposte ብታረጉት 😔
2026-08-20 19:04:41
1
Alexo +23ነኝ :
ከተዘረፈ ካለቀ በኋላ ብንነጋገር ምን ይበጃል?
2026-08-21 05:16:15
0
user2829419037 :
ወደ ኢትዮ ጦርነት ፎብሪካ መቀየሩ ኣታቅም ያኣገሬ ልጅ😳😳😏🤔
2026-08-21 05:05:02
0
To see more videos from user @jomom90, please go to the Tikwm
homepage.