@www.fikadu1.com: #✍️ በእሱ ፊት እኔ ማነኝ ተወዳጆች ! እግዚአብሔር ግን እኔን በምን ያውቀኛል ብላችሁ ታስባላችሁ? እኔን ስል ጣታችሁን አሻግራችሁ ወደ እኔ አትቀስሩ 🤭 ይልቁንስ የሌባ ጣታችሁን ወደ ራሳችሁ መልሷትና ለየራሳችሁ እኔ በሉ እሽ!? ድንገት ከእግዚአብሔር ፊት ብንቆም እኔ፣አንተ፣አንች በእሱ ፊት ማን እንደሆን ይነግረን ይሆን? ብዙ ጊዜ እኛ ለሰዎች ራሳችንን የምናስተዋውቀውም ሆነ ሰዎች በራሳቸው ዕውቀት ተደግፈው የሚያውቁን ሰባ አምስት በመቶው የሚሆነው ፐርሰንት ባልሆነው ነው።" መኑ ብእሲ ዘየአምር ዘውስተ ልበ ሰብእ ዘእንበለ መንፈሱ ለሰብእ ዘላዕሌሁ=በሰው ልቡና ያለውን የሚያውቅ ሰው ማን ነው? በእርሱ ያለችው ነፍሱ ወይም መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ "እንዲል 1ኛ ቆሮ 2፥11 ለምሳሌ ፦ተጠራጣሪዎች ሁነን ሳለን ለሰዎች ግን አማኞች መሰለን ራሳችንን ልንገልጽ እንችላለን ። እንዲሁም ደግሞ እኛ ኃጢአተኞች ሁነን ሳለን ጻድቅ አድርገው የሚቆጥሩን ሰዎችም አይጠፋም። እግዚአብሔር ግን እኛን የሚያውቀን ራሳችንን በገለጽነው ልክ ወይም ሰዎች እንዲህ ይሆናል ብለው በሰጡት ግምት ሳይሆን እሱ የሚያውቀን በሆነው እና በሆነው ብቻ ነው። እግዚአብሔር ትናንት የነበርነውን፤ ዛሬም የሆነውን እና ነገም የምንሆነውን ሁሉ ያውቃል ። እሱን ጊዜያት አይጉድቡትም፣ቦታዎችም አይወስኑትም፣ጨለማም አይጋርደውም "ኩሉ ክሱት ወስጡህ በኀቤሁ= በእርሱ ዘንድ የተሰወረ ምንም ምን የለም ሁሉ በፊቱ ግልጥ ነው። " እንዲል ጳውሎስ ታዲያ እኛን ❶እንደ ሳምራዊቷ ◈" ባል የለኝም በማለትሽ መልካም ተናገርሽ ቀድሞ አምስት ባሎች ነበሩሽ ፤ ዛሬ አብሮሽ ያለው ግን ባልሽ አይደለም ። " ይለን ይሆን ? ወይስ ➋ እንደ ማርታ ◈"በብዙ ነገር ትደክሚያለሽ ፥ ትቸገሪያለሽም ፤ ታዘጋጃለሽም፤ጥቂት ይበቃል፤ያም ባይሆን አንድ ይበቃል ።" ይለን ይሆን? ነው ወይስ ➌እንደ ማርያም ◈" ማርያምስ የማይቀሟትን መልካም ዕድል መረጠች" ይለን ይሆን? ➍እንደ ይሁዳ ◈" ከእኔ ጋራ እጁን ወደ ወጭቱ የሚያገባ አሳልፎ የሚሰጠኝ ይሁዳ እርሱ ነው " ይለን ይሆን? ወይሰ ➎ እንደ ጥጦስ ◈"እነሆ ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ነህ " ይለን ይሆን? ➏እንደ መቶ አለቃው ◈"እውነት እላችኋለሁ በሀገሪቱ ሁሉ እንዲህ ያለ እምነት ያለው ሰው አላገኘሁም " ይለን ይሆን? ➐እንደ ሐዋርያት ◈ " እናንተ እምነት የጎደላችሁ ስለምን ይህን ማድረግ ተሳናችሁ " ይለን ይሆን? ነው ወይስ ➑ እንደ ናትናኤል ◈ " እነሆ በልቡ ተንኮል የሌለበት እውነተኛ ሰው ይህ ነው። ይለን ይሆን?...በእሱ ፊት እኛማነን?በሰዎች ዘንድ ባልሆነው ብዙ ተብለናል ፥ ተወቅሰናል ፣ ተተችተናል ፣ ተነቅፈናል ፣ ታምተናል ፣ ተወንጅለናል እልፍ ሲልም ታስረናል ፣ ብዙ መከራዎችን ተቀብለናል ። ይህን ሁሉ ተውትና በሆነው ግን እኛ ማነን ??? ሁሉን በሚያውቅ በእሱ ፊት እኔ፣አንተ፣ አንች ማነን? በእሱ ፊት እኔ ማነኝ😥??? ወስብሐት ለእግዚአብሔር !!🙏🙏 #creatorsearchinsights #ethiopianviraltiktok #fyp

@fikadu ▸01
@fikadu ▸01
Open In TikTok:
Region: ET
Friday 21 August 2026 03:35:41 GMT
1670
283
4
12

Music

Download

Comments

getu_sale
ቅንነት ለራስነው 🦅🦅🦅 :
አቤቱ እግዘመያብሔር ሆይ በደላችን ይቅር በለን🥰🥰🥰
2026-08-21 07:00:12
1
getachew_zerie
GETACHEW_ZERIE_ADMASIE :
🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲
2026-08-21 10:42:47
0
ziriyawcr7
"የበረሀው"cR7🇮🇱🇮🇱🇮🇱🇮🇱 :
🙏🙏🙏
2026-08-21 04:27:19
0
ztomi64
ZTOMI :
🙏🙏🙏🙏🙏
2026-08-21 16:15:47
0
To see more videos from user @www.fikadu1.com, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About