@viewer_1221: ውድ "የእኔ እይታ" ቤተሰቦች፣ አንዳንድ ጊዜ ለምንወዳቸው ሰዎች በልባችን ያለውን ፍቅር ለመናገር እንዘገያለን። ፍቅር ግን በልብ ብቻ ተቀምጦ መኖር የለበትም። የምታፈቅሯትን ፣ ከእሷ ጋር ስትሆኑ ልባችሁ የሚረጋጋውን፣ ሰላም ለሚሰማችሁ: እሷን መምረጣችሁ የሕይወታችሁ ውብ ውሳኔ ነው ብላችሁ ምታምኑባት ከሆነ፣ ዛሬ እንዲህ በሏት፦ “ልቤን ለአንቺ መስጠቴ ትክክለኛ ውሳኔዬ ነበር።" በሕይወቴ ውስጥ ብዙ ሰዎችን ልገናኝ እችላለሁ፤ ብዙ ፊቶችንም ላይ እችላለሁ። ነገር ግን ልቤ የሚረጋጋበት፣ ነፍሴ የምታርፍበት አንድ ሰው ብቻ አለ። እሱም አንቺ ነሽ። አንቺን መምረጤ የአንድ ቀን ስሜት አልነበረም። እያወቅኩሽ የበለጠ የምወድሽ፣ እያወቅኩሽም የበለጠ እንደማከብርሽ የተረዳሁት ትልቁ ውሳኔዬ ነው። ከአንቺ ጋር ሆኜ ፍቅር ማለት በአንድ ሰው ፊት መደሰት ብቻ እንዳልሆነ ተማርኩ። ፍቅር አንዱ ሲደክም ሌላው መደገፍ፣ አንዱ ሲያዝን ሌላው መቅረብ፣ በደስታም ሆነ በፈተና እጅ ለእጅ መያዝ መሆኑን ተረዳሁ። አንቺን ካገኘሁ በኋላ የወደፊት ሕይወቴን ስለማስብ ብቻዬን አላየውም። አንቺን አያለሁ። የደስታዬን ቀናት ከአንቺ ጋር፣ የከበዱኝን ቀናትም ከአንቺ ጋር ማለፍ እፈልጋለሁ። ስለዚህ አንድ ቀን ራሴን ወደኋላ ተመልሼ ብጠይቅ፣ ‘ከሁሉም ውሳኔዎችህ የትኛውን ነው በፍጹም የማትጸጸትበት?’ ብሎ ልቤ ቢጠይቀኝ፣ መልሴ አንድ ብቻ ነው። አንቺን መምረጤ። ልቤን ለአንቺ መስጠቴ። ከአንቺ ጋር ሕይወቴን ማጋራቴ። እና ዛሬ ይህን ስልሽ አልፈራም፦ አንቺን ማግኘቴ ዕድሌ ነው፤ አንቺን መምረጤ ደግሞ ውሳኔዬ ነው። እናም ያንን ውሳኔ ዳግመኛ ብመርጥ እንኳን አንቺን እመርጣለሁ❤️" በላት። እናም ውድ "የእኔ እይታ" ቤተሰቦች ወይም ወንድ ላይ ልባችሁ በትክክለኛዋ ሴት ላይ ካረፈ፣ እሷን/እሱን ማግኘታችሁ የሕይወታችሁ ትክክለኛ ውሳኔ ነው ብላችሁ ካመናችሁ፣ ይህን ጽሑፍ ለእሷ/ሱ በመላክ ቀናችሁን አሳምሩት። አንዳንድ ቃላት ዛሬ ቢነገሩ ትዝታ ይሆናሉ፤ ነገ ቢቀሩ ግን ጸጸት ሊሆኑ ይችላሉ። ❤️ ይህ የእኔ እይታ ነው✍️ፍቅር የተሞላበት ቀን ይሁንላችሁ🙏 ቀጣይ ሌሎች እይታዎች እንዲደርስዎት የእኔ እይታን ፔጅ follow, like and share በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ! #foryou #fyp #viral #fypシ #viralvideo
የእኔ እይታ
Region: SO
Friday 21 August 2026 10:35:39 GMT
Music
Download
Comments
🔥MY❤Orthodox👑🙏 :
በትክክል እናመሰግናል እይታህ ድንቅ ነዉ🙏🙏 እዉነተኛ ሰዉ የልብ ማረፊያ ማስመሰል የለለበት የሰላም መስፈኛ የሚወዱት ሰዉ ነዉ🙏እዉነተኛ ፍቅር የእግዚአብሄር ስጦታ ነዉ በሁለት ሰወች መካከል በአንድልብ ቋንቋ አለምን ማየት መቻል ነዉ
2026-08-21 13:39:54
2
እንደልቧ🇪🇹💞☪ :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰ትለያለህ
2026-08-21 23:12:46
1
Tegst Lakwu :
ተባረክ አቦ🙏🙏🙏🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-08-21 10:54:14
1
Seged Dessie :
wow
2026-08-21 10:46:28
1
liliy1267 :
አይ አንተ🙏🙏🥰🥰🥰🥰🥰🥰የአንተ እይታ ግን የተለየ ነዉ 🙏🙏🙏🙏በርታልን
2026-08-21 10:54:51
1
Leyu Ta'em :
የሚባለውን ሰው መሆንና የሚባል ሰው መጥፋቱ ነው እንጅ ድንቅ ነበር
2026-08-21 16:54:42
1
💫ከዋክብት✈💒 :
🥰🥰🥰
2026-08-21 10:45:04
1
የማይወጣ እጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል :
❤️❤️❤️❤️
2026-08-22 15:10:48
1
Tegegne Mulu :
🙏🙏🙏
2026-08-22 09:06:15
1
ይማም :
🥰🥰🥰
2026-08-22 18:37:27
1
ብርዝናዬ :
🥰🥰🥰
2026-08-22 19:28:38
0
መንደዱ ላይቀር ጭሱ ገደለኝ :
🥰🥰🥰
2026-08-21 13:53:24
1
Yeruqi sew aykifaw🥹🇪🇹💞 :
🥰🥰🥰❤️
2026-08-23 19:07:22
0
To see more videos from user @viewer_1221, please go to the Tikwm
homepage.