@sr36377378: “ሴት በማጀት” ዘመን ሲያበቃ.. {ኖህ ዳንኤል} መቼስ ሰሞኑን አየሩን ሁሉ የቃቄ ውርድዎት ሴቶች ልጆች ተቆጣጥረውታል አይደል? (ቃቄ ውርድዎትን ለማታውቁ ከዛሬ 188 አመታት በፊት የነበረች የጉራጌ የሴቶች መብት ተሟጋች ነበረች) አስቡት እሷ ያኔ ለሴቶች በምትሟገትበት በዚያው ዘመን አፍሪካን ተዉትና አሜሪካ የሚኖሩ ሴቶች እንኳን በአስገራሚው የ English Common Law ስር ይተዳደሩ ነበር። ለምሳሌ በዚያን ግዜ አሜሪካ ውስጥ ሴት ልጅ የወረሰችውም ሆነ ሰርታ ያገኘችው ንብረት ባል ካገባች በኋላ የባሏ ይሆን ነበር። ደሞዟ ራሱ የባሏ ነበር። 🙂 ምን እሱ ብቻ አስገራሚው ህግ እንዲህም ይል ነበር.... “ባልና ሚስት አንድ አካል ናቸው ያም አንድ አካል ባል ነው" 🤣 በዚህ ህግ መሰረት የሴቷ ህልውና ራሱ በባሏ ውስጥ ይዋጣል ማለት ነው። ከዚህ በተጨማሪም ሴት ምንም አይነት ውል መዋዋል አትችልም፣ መምረጥ መመረጥም አትችልም። እሱ ብቻ ሳይሆን ባል ሚስቱን ለማረም በሚል ምክኒያት እንደፈለገ እንዲደበድባት ሁሉ በህግ ተፈቅዶለት ነበር። ይህ ሁሉ እንግዲህ የቃቄ ውርድዎት የእድሜ እኩዮቿን ሰብስባ ጉራጌ ውስጥ ከፍተኛ አቢዮት ባስነሳችበት በዚያን ወቅት አሜሪካ ውስጥ ይፈፀም የነበረ ግፍ ነው! እናማ የቃቄ ውርድዎት ልጆች ሰሞኑን ሚዲያውን ሲያንቀጠቅጡት እኔም ትንሽ ወደኋላ ተመልሼ አንዳንድ ነገር ገረፍ ገረፍ እያደረኩ ነበር። ብራዘር ራስህን upgrade ካላደረግክ እንደድሮ “ሴት በማጀት፣ ወንድ በችሎት” እያልክ አብረህ የምታኖራት ሴት ዘንድሮ የለችም። እንደሌኒን ሃውልት አንድ ቦታ አትተከል። ተንቀሳቀስ። ስዊዘርላንድ እስከ 1971 ድረስ ለሴቶች ድምፅ የመስጠት መብትን አልፈቀደችም ነበር። እንደውም ወንዶች ፖለቲከኞች ፓርላማ ውስጥ በግልፅ “ሴቶች ድምፅ ከሰጡ ቤታችን ምግብ አይሰራም” የሚል ስጋት ያቀርቡ ነበር። (መቼስ የሆዳችን ነገር አይሆንልንም) 😀 የስዊዝ ሴቶች ታዲያ ይህንን የወንዶች ስጋት ከሰሙ በኋላ በጣም ተበሳጭተው አንድ ነገር አደረጉ.... ፓርላማ ስብሰባ በነበረበት በአንዱ ቀን ፓርላማው ፊት ለፊት ትላልቅ ድስቶችና ምጣዶችን ይዘው በመውጣት ወንዶቹ የምግብ አሰራር አዘገጃጀት መመሪያ (Recipe Books) እንዲያነቡ በሃይለኛ ድምፅ መጮህ ጀመሩ። 😀 በዚያን ግዜ ስሎጋኖቻቸው ላይ ፅፈዋቸው ከወጡ መፈክሮች አንዱ እንዲህ የሚል ነበር... “የምግብ አሰራር የማያውቅ ወንድ ሐገር መምራት አይችልም” ሃሃሃሃ እህታለም አንቺ ዛሬ ዩኒቨርስቲ እንድትሄጂ ሴት አያቶችሽ ያልሰሩት ነገር የለም። ለምሳሌ በ1913 የእንግሊዝ ሴቶች መንግስት ትኩረት እንዲሰጣቸው ለማድረግ በወቅቱ ይሰራጭ የነበረውን የንጉሥ ጆርጅ አምስተኛ ምስል ያለበትን የነሀስ ሳንቲም (Pennies) በሙሉ ከገበያው ሰብስበው ልዩ የብረት ማህተም በመቅረጽ በንጉሡ ፊት ላይ «Votes for Women» የሚል ፅሁፍ እያተሙ መልሰው ወደ ገበያ ለቀቁት 😀 መንግስት ሳንቲሞቹን በሙሉ ሰብስቦ ለማስወገድ ኢኮኖሚያዊ አቅም ስለሌለው ዝም ብሎ በነዚያው ሳንቲሞች ለመገበያየት ተገደደ። በሴቶች የመብት እንቅስቃሴ ውስጥ አቢዮተኛ ሴቶች መብታቸውን ለማስከበር ያልሰሩት ስራ የለም ስልሽ! አሜሪካ ውስጥ "አስቀያሚ ስለሆናችሁ ነው ፌሚኒስት የሆናችሁት" ሲሏቸው የተዋቡ ሴቶችን ከፊት አሰልፈው ሰልፍ ሲወጡ፣ የዊኒስተን ቸርችልን ስብሰባ ደውልና ድመቶች ይዘው ገብተው ሲረብሹ፣ ምን ያልሰሩት አለ? ፈረንሳይ ውስጥ በ1925 ሴቶች መመረጥ አይችሉም ሲባል ምርጫ አጭበርብረው ለ30 ሰከንድ ሴት ከንቲባ ሁሉ አስመርጠዋል 😀 ከሁሉም ግን የገረሙኝ 1909 የነበሩ የእንግሊዝ ሴቶች ናቸው። ነገሩ እንዲህ ነው.... ሴቶቹ በእንግሊዝ የፖስታ ህግ መሰረት “ማንኛውንም ህጋዊ ነገር በፖስታ መልእክት መላክ ይቻላል” የሚል የህግ ክፍተት መኖሩን ደረሱበት። እንግሊዝ ውስጥ ደግሞ ህግ ህግ ነው ይተገበራል! ይህንን የተረዱት ኤልሲ ማቲዎስ እና ቪክቶሪያ ራይን የተባሉ ሁለት አማፂ ሴቶች ራሳቸውን እንደ «ሰውኛ ፖስታ» (Human letters) በማስመዝገብና ፖስታው የሚደርስበትን አድራሻ ደግሞ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ አድርገው በማስመዝገብ በፖስታ ሰራተኛ ታጅበው እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደጃፍ ድረስ ተላኩ። 😀በዚህ የተነሳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥበቃዎች "ደብዳቤውን አንቀበልም" ብለው ለማባረር ትልቅ ውዝግብ ውስጥ ገብተው እንደነበር ታሪክ ይናገራል 😀 ለማንኛውም ሴቶች ሳትሽኮረመሙ የሚሰማችሁን ተናገሩ! ጠይቁ! ጩሁ! ናንሲ አስቶር የተባለች የመጀመሪያዋ በብሪታንያ የፓርላማ ሴት አባል እንዲህ ትላለች.... “እኔ ሁልጊዜም የምናገረው ዝም ብዬ ብቀመጥ ወንዶቹ እኔን ወክለው የተሳሳተ ነገር ይናገራሉ ብዬ ስለምሰጋ ነው።” ትላለች 😀 አይ እኛ! 🙂

Noah Daniel
Noah Daniel
Open In TikTok:
Region: ET
Friday 21 August 2026 15:27:12 GMT
10663
1182
59
178

Music

Download

Comments

bobmar0913
@ 🔥 🔥 :
አመፀኛ ሴት ስወድ🥰🥰🥰
2026-08-21 21:15:12
35
bbccddee123
virgo :
that's why eko be Haymanot ena behl etir adrgew yeyazun
2026-08-21 20:28:05
39
ashlienanss_
Ashely :
እንዲ ብንግባባ ዛሬ ላይ ስለ መብት ከመከራከር ይልቅ ስንት ታሪክ በሰራን ነበር:: ትችላለህ
2026-08-21 15:56:49
79
cinnamongirl436
Cinnamon girl :
This's what we call "የተማረ ይግደለኝ",and the last one, I couldn't agree more lol
2026-08-21 22:44:19
16
joosssyyy1
Alemtsehay Negus :
መቼም እኔ የማምነው ሃይማኖት መሰረቱ የተፈጥሮና የአፈጣጠር ልዩነት እግዚአብሄር የሰጠንና እንደተሰጠን ተፈጥሮ መስራትና መኖር በተለይ መውለድን አስመልክቶ ቢኖርብንም""ምድርን ግዙ አስተዳድሩ የተባልንው በጋራ እነጂ አዳም አንተ ግዛ ሄዋን ትመልከት አይልም አላለም በተውራትም ቀጥታ የተቀበሑት ቃል ነው ዮህ እናቶቻችን ያለፉበት ዛሬም ያልጠፋው ጭቅና ሰው ሰራሽ ነው!!
2026-08-22 07:28:08
9
patrafranko
Papi kiya :
getan tigist norogn emanebew yanten stehufe new thank you
2026-08-21 18:09:22
11
pheebs71921
pheobe :
ሰው የለም እንዳንል ሰው አለ ቀን የለም እንዳንል ቀን አለ የተባለው ለካ ላንተ ነው ወዳጄ🙏❤
2026-08-22 15:19:06
14
jerry.nani
jerry Nani :
If only they are willing to actually try and understand the cause and try to make a difference 🤦🏾‍♀️
2026-08-21 18:16:58
6
meti.chuchu
Meti chuchu :
wow ሚገርም ፅሁፍ
2026-08-22 14:03:54
7
lid16ya
🩺Dr Lidiya Ab 👩‍⚕️ :
👏👏👏ትፅፈዉ የለ እንዴ🤔
2026-08-22 11:50:17
5
bezaye1992
bee perfumes :
thank you!
2026-08-21 17:11:16
4
vaticanoptics
👓 hiwi :
We call it a civilized thought 👌🤝
2026-08-22 08:56:01
3
suemeorsuethem
Zeee :
as always Noah
2026-08-24 07:56:36
1
ydidiya.k
Edu k 🎀 :
እዚማ የሉም🤌🥰
2026-08-21 23:58:40
2
meron3528
Meron :
Brk bel TEBAREK🙏
2026-08-21 21:24:55
0
taytu.molaw
Marta Hayat🦋🍓 :
ዋዉ
2026-08-23 18:20:08
1
brookearaya
Brooke :
Thank you 🥺
2026-08-21 20:12:23
8
set12_3
ብርቅርቅታ... :
thank you!!!
2026-08-21 17:27:53
2
survivorchildhoodtrauma1
shalom :
Healthy Ethiopian food based meal plan
2026-08-22 16:16:09
0
mediti12
@sif ase :
thank you🥹🥹
2026-08-22 16:29:27
0
tsion0287
tsion :
why we don't have atleast one chapter about this things on history books in school gn alakm
2026-08-25 03:00:12
1
mekdimekdina
Mekdi Maki♋️🌀♾️ :
Thank You🥺🥰
2026-08-22 23:51:21
0
drzehara
Dr Zehara gynecologist :
2026-08-23 18:45:14
1
jerrydimple1995
jerrydimple :
🔥🔥🔥
2026-09-24 06:16:29
0
mercymekonen
Mercy Habesha 16 :
endante yabzaln👌🥰
2026-08-21 22:20:43
0
To see more videos from user @sr36377378, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About