@girma.yimer_official: ✅ ለጥያቄወቹ የተሰጡ መልሶች፦❤❤❤❤❤ ​1ኛ. ንስሐ ለመግባት ወይም የንስሐ አባት ለመያዝ እንዴት ብለን ነው የምንጠይቀው? ​✅ የንስሐ አባት መያዝ ማለት መንፈሳዊ ሕክምና ማግኘት፣ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የሚመራንን መሪ ማዘጋጀትና ነፍሳችንን ለሐኪም ማሳየት ማለት ነው። ​✅ የአጠያየቅ ስርዓቱ ፦ ወደ ቤተ ክርስቲያን ቀርቦ ፀሎት አድርጎ በመንፈሳዊ ትሕትናና በፍርሃተ እግዚአብሔር፡ "አባቴ እኔ ሀጢያተኛ ልጅ ነኝ ነፍሴን የምንከባከብበት በየጊዜዉ ኃጢአቴን ተናዝዤ ከእግዚአብሔር ጋር የምታረቅበት ንስሐ አባት ስለሚያስፈልገኝ የንስሀ አባት እንዲሆኑኝ እፈልጋለሁ ብሎ መጠየቅ። ​✅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ንስሐ አባት ሲናገር፡ "ካህናት በምድር ላይ የሚፈቱትና የሚያስሩት በሰማይ የተፈታና የታሰረ ይሆናል። ካህናት የነፍስ ሐኪሞች ናቸው፤ ደዌህን ለሐኪም ሳታሳይ ፈውስን አታገኝም" ይላል። ​✅ በመጽሐፈ ምሳሌ 11፥14 ላይ ምክር ከሌለ ሕዝብ ይወድቃል በመካሪዎች ብዛት ግን ደኅንነት ይሆናል እንደሚል. የንስሐ አባት ደግሞ ወደ መንግሥተ ሰማያት የሚመራን የመንፈስ ቅዱስ መሪ ነው፦ ​2ኛ. ንስሐ ስንገባ ኃጢአታችንን እንዳንረሳ እንዴት ነው ማድረግ ያለብን? ​✅ ኃጢአትን ማስታወስና ለንስሐ መዘጋጀት ለብቻ በመሆን ንፁህ ወረቀትና እስክብሪቶ ይዞ  የሕሊናን መዝገብ መመርመርን ይጠይቃል። ​✅ በጽሑፍ መያዝ ፦ ንስሐ ከመግባታችን በፊት  ከሕፃንነታችን ጀምሮ  የሠራናቸውን በሐሳብ ወይም በምኞት ፣ በቃል ወይም በንግግር ፣ በሥራ ወይም በተግባር ፣ በሕዋሳት (በዓይን፣ በጆሮ፣ በምላስ...) የፈጸምናቸውን ሀጢያቶች ሁሉ ማንም ሊያየዉ በማይችለዉ ጊዜአዊ ወረቀት  ላይ  መጻፍ አስፈላጊ ነው። ​✅ ከዚህ በመቀጠል "አምላኬ ሆይ! የረሳሁትን ኃጢአቴን ግለጽልኝ" ብሎ መንፈስ ቅዱስን በፀሎት መማጸን። ​✅ በገድላትና በስንክሳር እንደሚነገረው፦  ቅዱሳን አባቶች ወደ ንስሐ አባታቸው ከመሄዳቸው በፊት ሌሊቱን ሙሉ በጸሎትና በዕንባ ሕሊናቸውን ይመረምሩ ነበር። ​✅ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ በሃይማኖተ አበው ላይ፡ "ኃጢአትህን ብትረሳው እንኳ እግዚአብሔር አይረሳውም አንተ ግን ብታስበውና ብትናዘዘው እግዚአብሔር ይረሳልሃል" ብሏል። ስለዚህ በጽሑፍ ይዞ መቅረብ ትልቅ መንፈሳዊ ብልህነት ነው። ​3ኛ. የረሳነውን ኃጢአት ድጋሜ ተመልሰን እንገባለን? ወይስ ምን ማድረግ አለብን? ​✅ አዎ  ልባችንን መርምረን ንስሐ ከገባን በኋላ ላይ የታወሰን ወይም የረሳነው ኃጢአት ካለ በሚቀጥለው የንስሐ ቀጠሯችን ላይ ለንስሐ አባታችን፦ "አባቴ ባለፈው ንስሐ ስገባ የረሳሁት ይህ ኃጢአት ትዝ ብሎኛል" ብለን እንናዘዛለን። ​✅ እግዚአብሔር አምላክ የልብን ቅንነት ያያል። አውቀን የደበቅነው ካልሆነ በስተቀር ባለመገንዘብ ወይም በመርሳት የቀረውን ኃጢአት አምላክ በካህኑ ጸሎተ ፍትሐት (በፍትሐት ጸሎት) ይቅር ይላል። ነገር ግን ትዝ ሲለን ድጋሜ መናዘዛችን ፍጹም ትሕትናንና የነፍስ ጥንቃቄን ያሳያል ለህሊና ነጻነትም ይሰጣል። ​4ኛ. የንስሐ አባት አንዴ ከተያዘ መቀየር አይቻልም? ወይስ ይቻላል? (ለምሳሌ ካልተመቸን) ​✅ መቀየር ይቻላል  ነገር ግን በምክንያትና በስርዓት መሆን አለበት። ​✅ የንስሐ አባቱ በሞት ሲለዩ፣ ከአገር ወደ አገር ሲሄዱ/ሲርቁ፣ ወይም መንፈሳዊ መመሪያቸው ትምህርታቸዉ ቀኖና አሰጣጣቸዉ  ለነፍስ ዕድገት ካልረዳን፣ እንዲሁም በሃይማኖት አስተምህሮአቸዉ የሚሳሳቱ ከሆኑ ወይም ገንዘብ ወዳጅ ከሆኑ መቀየር ይቻላል። ​✅ ለመቀየር  ግን ሥርዓቱን ማወቅ አስፈላጊ ነዉ ፦ ​✅ በስሜት ወይም በጥቅም ምክንያት ዝም ብሎ አባት መቀየር አይገባም። ​✅ ከተቻለ ለቀደሙት የንስሐ አባት በጥሩ ሁኔታ ማስረዳትና "አባቴ በቦታ/በሁኔታ ምክንያት ስላልተመቸኝ ሌላ የንስሀ አባት ልይዝ ስለሆነ ይፍቀዱልኝ" ብሎ ፀሎተ ቡራኬ ተቀብሎ መቀየር። ​✅ ቅዱሳን አባቶቻችን በዚህ ጉዳይ ላይ ፦ ማር ይስሐቅ እንደሚለው፡ "መንፈሳዊ ሐኪምህን ስትመርጥ የነፍስህን ደዌ የሚረዳ ይሁን፤ ነገር ግን ያለ በቂ ምክንያት አባትህን አትቀያይር፤ ተክሉ በተከታታይ ቦታው ከተቀየረ ፍሬ ማፍራት አይችልምና።" ​5ኛ. በስደት ሆነን እንዴት ነው ንስሐ የምንገባው? በስልክ ደውለን ከንስሐ አባታችን ጋር ንስሐ መግባት እንችላለን? ​✅ በስደት ሀገር ለምንኖር ወንድሞችና እህቶች ዘመኑ የተለያዩ ፈተናወች የበዙበት አስቸጋሪ ስለሆነ ንስሐ ብንገባ እግዚአብሔር ይረዳናል የቤተክርስቲያናችን አስተምህሮም ይፈቅድልናል። ​✅ በስልክ ንስሐ መግባት ይቻላል? ​✅ አዎ ይቻላል። በምትኖሩበት ሀገር ቤተክርስቲያን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህን ከሌለ ሀገር ቤት ወይም በሌላ ቦታ ካሉ የንስሐ አባት ጋር በስልክ ንስሐ መናዘዝ፣ ምክርና ቀኖና መቀበል ይቻላል ቀኖና ስትቀበሉ ካላችሁበት ሀገር ስራ አንጻር የማይመች ቀኖና ከሰጧችሁ ይህንን ለመፈፀም አይመቸንም ብላችሁ ወዲያዉኑ በመናገር ቀኖናችሁን ማስቀየር ትችላላችሁ ቀኖና እንዳታቋርጡ ፣ ንስሀ ገብታችሁ የተሰጣችሁትን ቀኖናችሁን ፈፅማችሁ ሳትጨርሱ በመካከል ፈተና ቢገጥማችሁ ሀጢያት ብትሰሩ ወዲያዉኑ ሳይዉል ሳያድር ለንስሀ አባታችሁ ተናዛችሁ ተጨማሪ ቀኖና ይሰጣችኋል። ንስሀ ስትገቡ እንዳትፈሩ መዉደቅ መነሳት የቅዱሳኖች የህይወት መንገድ ነዉ። እንደወደቁ መቅረት ግን የዳቢሎስ ልጅ መሆን ነዉ። ​✅ አበው አባቶች፦ "እግዚአብሔር የልብን ፍላጎትና መሰጠት ያያል፤ በሰውነትህ በስደት ብትሆንም ነፍስህ በንስሐ ወደ እግዚአብሔር ከቀረበች እርሱ ወደ አንተ ይቀርባል" ይላሉ። ስለዚህ በሁሉም ቦታ እግዚአብሔር ስላለ በፀሎት በርቱ በንስሀ ህይወት ተመላለሱ። ​✅ እንዳጠቃላይ የሰዉ ልጅ ሕይወት አላፊና ጠፊ ነው። የዚህ ዓለም ጭንቅና ድካም ያልፋል። የሰው ልጅ በምድር ላይ የሚኖረው ለጥቂት ዘመን ነው፤ የነፍስ መኖሪያ ግን የዘላለም አምላክ መንግሥት የሆነችው መንግሥተ ሰማያት ናት። ​✅ መጽሐፈ ሲራክ 5፥7 ላይ፦ "ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ አትዘግይ ከቀን ወደ ቀንም አታስተላልፍ" ይላል። ​✅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፦ "ትናንት አልፏል፤ ነገ ደግሞ የአንተ ለመሆኑ ዋስትና የለህም፤ ያለችህ ሰዓት ዛሬ ብቻ ናትና አሁኑኑ ንስሐ ግባ" ይላል። ​✅ በስደት ሀገር ያላችሁ እህቶችና ወንድሞች የእግዚአብሔር የምህረት በር ሳይዘጋ፣  የንስሐን በር እንንኳካ። ንስሐ የሁለተኛ ጥምቀት ያህል ነፍስን ያጥባል፤ ከእግዚአብሔር ጋር ያታርቃል። የንስሐ አባት በመያዝ፣ ኃጢአትን በግልጽ በመናዘዝ ንስሐ እንግባ ማለት እፈልጋለሁ ጠያቂዋ እህቴ አመሰግናለሁ። ​#ኦርቶዶክስ #ተዋሕዶ #ንስሐ #መንፈሳዊ #ቲቪ_ኦርቶዶክስ

ነገ መሞት አለ 🕯️ትጉና ፀልዩ ማቴ 26፥41
ነገ መሞት አለ 🕯️ትጉና ፀልዩ ማቴ 26፥41
Open In TikTok:
Region: AE
Friday 21 August 2026 17:46:50 GMT
7921
517
60
526

Music

Download

Comments

tiktokvillage44
maregngeta@kiya :
You’re good bro
2026-08-26 22:24:27
0
cikarang153
♥️ :
እግዚአብሔር ይስጣቹ በጣም ጭንቀት ውስጥ ነበርኩ 🥹🤲4ኛው ግራ አጋብቶኝ ነበር 🥹
2026-08-25 08:53:37
2
kidist5093
kidist :
እሚገርም ምላሽ ከነ ማብራሪያው 🙏
2026-08-23 07:44:37
5
haniiii1319
haniiiiተዋህዶእምነቴ.ማርያምእናቴ :
የሁላችንምጥያቄነበርበስደትያለኖችእኔማጭንቀትሊደፍኝነው🙏🙏በጣምእናመሠግናለን🙏🙏
2026-08-23 20:34:38
1
ft456427
𝄞❥ፍቅርተ ማርያም✞᭄༄ :
በእዉነት ቃለህወት ያሰማልን ወንዲማችን ሁሉም የኔ ጥያቄ ነበረ🙏🙏🙏🙏
2026-08-22 02:39:06
0
belaqahtan
ወሎ ብለህ ጥራኝ :
ቃለ ሒወት ያሠማልን
2026-08-22 06:45:53
0
mam329237
mam :
እግዚአብሔር ይባረክ ለብዙ ጥያቄዎች መልስ አጊቻለው
2026-08-22 19:34:28
0
sara700106
ወድሜ😭ስብራቴ💔😭 :
ቃለሂወት ያሰማልን ወድማችን🥰🥰🥰
2026-08-22 06:49:20
0
user1243947651341
እግዚአብሔር እረኛየ ነው 🙏 🇪🇹@🇰🇼 :
በእውነት ቃለኽይወትን ያሰማልን🙏🙏🙏
2026-08-22 09:47:23
0
tit32221
ሚካኤል አባቴ ✝️❤ :
ቃለ ሒወት ያሰማልን ወድማችን🙏🙏🙏
2026-08-22 13:10:56
0
user71735766815286
Demsie sete :
አስተማሪነዉለንስሀያብቃን
2026-08-22 07:56:13
3
userjdhxzxoiq9
eyerus :
እግዚያብሔር ይባርካችሁ የብዙ ጥያቅየ ነበር
2026-08-22 04:22:01
1
maya.queen2561
@ማያ የአባቱዋ Ⓜ😘 :
ቃለ ህይወት ያሰማልን😥😥ለንስሐ ሞት ያብቃን🙏🙏🙏
2026-08-24 13:34:34
0
user9817971391136s
ጎጃም ነው ሀገሬ :
ቃለ ህይወት ያሰማልን በስደት አገር ያሎችንም የይጠብቀን
2026-08-26 11:45:22
0
ergbe63
Tseada lemaryam :
እግዚአብሔር ይባርካችሁ በ እውነት ጥሩ ጥያቄ እና መልስ ነው
2026-08-24 19:54:26
2
user9376850283979
ማራናታጌታሆይቶለና :
ቃለወትያሰማልን🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-08-25 15:39:36
0
fhf7fadey
Fhf7fAdey :
እግዚአብሄር ፀጋዬን ያብዛልህ🥰🥰🥰
2026-08-25 00:26:31
0
tadewossekltew
ያየ አለ ወይ ጭቄን።።።። :
ይቻላሉ ሁሉም ጥያቄወች እዉነታ ናቸዉ
2026-08-23 00:03:00
1
aklilu.haftay2
Aklilu Haftay@618870421088 :
ናመሰግናለን መምህር ቃለሂወት ያሰማልን
2026-08-26 06:12:59
0
user19885418
ወይኩን ፈቃድኬ⛪️💚💛❤️ :
ቃል ህይወት ያሰማልን ለንሳ ሞት ያብቃን🤲😢😢
2026-08-25 20:07:35
0
b219377
🅱️ዩየእግዛብሄርባራ🤲🤲😭😭ዋነፍሴ :
ቃልህይወትያሰማልን🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-08-24 20:06:24
0
user6783670438856
እማ በፆለትሽ😘🙏 :
ቃለ ህይወት ያሠማልን ጸጋውን ያብዛልህ ወንድሜ👏🙏🙏🙏
2026-08-24 13:13:20
0
thut4722
thut :
ቃለህይወት ያሰማልን🙏🙏🙏
2026-08-24 18:27:05
0
user7480178379796
ተስፋየ በእግዛብሔር ነው 💝 ⛪ 🎂 :
😢ቃልሂወት ያሰማልን🥺
2026-08-24 15:28:36
0
my71243
🕊☦️ ናዲያ ☦️🕊 :
2026-08-21 22:07:18
0
To see more videos from user @girma.yimer_official, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About