@seid_959: #በእውነት እና #በዝምታ መካከል ያለ ስንብት.... #አንዳንዴ ሰዎችን ለመተው መራራ ቃል መነጋገር አያስፈልግም፤ ዝምታ በራሱ ትልቅ ስንብት ነው። በሕይወት መንገድ ላይ፣ አብረውን ይጓዙ የነበሩ ሰዎች[ወዳጆች] በወዳጅነት ሚዛን ላይ አስቀምጠናቸው ክብደታቸው ሲቀል፣ በመካከላችን ያለው ያ ጥንታዊ እምነት ሲሰበር፣ የነበረን ቦታ እና የገነባነው አብሮነት መፍረሱን ስንረዳ፣ መጀመሪያ ላይ ድንጋጤ ይሰማናል። ከዛ ግን፣ በፈተና መለኪያችን ሲለኩ፣ የቆሙበት ቦታ እንደማይመጥነን፣ የገቡት ቃል እንደቀለለ እና በጠበቅናቸው ልክ እንዳልተገኙ ስናረጋግጥ....."እንዴት መኖር እንደሌለብን" እና "ለማን ቦታ መስጠት እንደሌለብን" እንማራለን። #ያ ያልጠበቅከው የሰዎች መለወጥ መጀመሪያ ላይ በጣም ደባሪ እና የውስጥህን ሰላም የሚነሳ ቢመስልም፣ በአንተ ቀጣይ ጉዞ ውስጥ ግን ትልቅ ጥቅም አለው። አንዳንዴ ክፉ አጋጣሚ ይመጣል፤ የምትወደውን ውድ ነገርህን ይወስድብሃል፣ የገነባኸውን ተስፋ ያፈርስብሃል። ነገር ግን በዚያ ፍርስራሽ ውስጥ ራስህን ታገኘዋለህ። በዙሪያህ ያሉት ሰዎች ሲሸሹ፣ በራስህ እግር ላይ መቆምህን ትማራለህ። በጣም የምትተማመንባቸው ሰዎች ሲሄዱ፣ እራስህን ለራስህ እንደ ምርጥ ጓደኛ ታገኘዋለህ። በዙሪያህ ላሉ ሰዎች ያለህን እምነት በትክክለኛው መጠን ትማራለህ። ክፉ አጋጣሚ መጥቶ ባይሆን ኖሮ፣ ያንን "ጭንብል" ለብሰው በዙሪያህ የሚኖሩትን ሰዎች ማንነት መቼም አታውቅም ነበር። አንዳንድ ሰዎችን የምንተዋቸው ስለምንጠላቸው ብቻ ሳይሆን፣ ስለተማርንባቸው ነው። ለካ አንዳንዴ ሰውን ለመሰናበት፣ ከእነርሱ ጋር ተነጋግረህ መለያየት አይጠበቅም ፤ በውስጥህ ከእነርሱ ጋር ያለህን ግንኙነት በዝምታ መፍታት ብቻ በቂ ነው። ምክንያቱም አንዳንድ እውነቶች መነገር አያስፈልጋቸውም ፤ መተው ብቻ ይበቃቸዋል። ዝም የምትለው ምንም የምትናገረው ነገር ስለሌለህ ሳይሆን፣ የምትናገረው እውነት ከእነሱ ጭምብል በላይ ከባድ ስለሚሆን ነው። ለዚህም ነው አንዳንድ የቅርብ ሰዎቻችን በቃላቸው እና በማንነታቸው ምን ያህል እንደተራራቁ ስናይ ታዝበን የተውነው። በእርግጥ እነሱ አሁንም በአጠገባቸው እንዳለህ ሊሰማቸው ይችላል፣ ነገር ግን በእውነቱ፣ አንተ ከእነርሱ ጋር ያለህን የልብ ወዳጅነት በሆነ ጊዜ/አጋጣሚ ምክንያት ቆርጠሃል። አንዳንድ ጊዜ ከአንዳንድ ሰዎች ጋር physically አብረን የምንኖረው በውዴታ ወይም በአክብሮት ሳይሆን፣ በይሉኝታ እና በለዘብተኝነት 'መጥፎ ሰው' ተብለን እንዳንፈረጅ በሚሰማን ስጋት ብቻ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ 'መጥፎ' ላለመባል በሚል ካባ ውስጥ ተሸሽገን፣ በአንድ ላይ እየኖርን ነገር ግን በውስጣችን የልብ ስንብት በመፈፀም ከእነርሱ እጅግ የራቅን፣ በዝምታ የተገነባ የርቀት ግድግዳ ሰርተናል። አሁን የምንኖረው በጋራ መኖር ውስጥ ሳይሆን፣ በራስ የውስጥ ነጻነት ውስጥ ነው። አዎ! ዛሬ በዝምታ አብረናቸው የምንቆየው እነርሱ ለውጥ እንደሚያመጡ በማሰብ አይደለም፤ የራሳችንን ስብዕና እና የውስጥ ሰላም ለመጠበቅ ነው። ከእንደዚህ አይነት ሰዎች ጋር በውስጥህ ተለይተህ በውጫዊው መልክ በዝምታ በመኖር፣ በሕይወትህ ውስጥ ያለህን መረጋጋት ለመጠበቅ የብልህ እርምጃ ትወስዳለህ። ምክንያቱም አንዳንዴ እውነትን ተናግሮ ጦርነት ከመቀስቀስ ይልቅ፣ እውነትን በልብ ቀብሮ ዝም ማለት ለራስ ክብር ሲባል የሚከፈል የመጨረሻው ዋጋ ነው። ሰላምን ከክርክር፣ ክብርን ከቂም በላይ ስትቆጥር ዝምታን ትመርጣለህ። ያ የዝምታ መጋረጃ እነርሱን ለመከላከል ሳይሆን፣ በአንተ እና በአስተሳሰባቸው ዝቅጠት መካከል የተቀመጠ ቅዱስ ድንበር ነው። ሰዎች ማንነታቸውን በድርጊታቸው ሲያሳዩን፣ በቃላት መልሰን መብከንከን አያስፈልግም። #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🚵♀️ 𝐌𝐄𝐊𝐀𝐍𝐈𝐊𝐔 //🫶🤌/
Region: SA
Friday 21 August 2026 18:04:50 GMT
Music
Download
Comments
@Tት ያገጠሯ Ⓐ💘Ⓣ :
እንደኔ ጨሪሶ ያነበበ ብቻ
2026-08-23 19:06:52
45
😒°ንቢቷ°😜 :
🥺🥺🥺🥺ወላሂ በዚህ ምድርላይ እደኔ ሰዉ የሚወድ የለም አሁላይ ሠዉ አስጠላኝ ቢህድ ቢመጣ ምንም አይሞቀኝ አይበርደኝ ተጣልቸ እኳን ማስረዳት አልፈልግም በዝምታየ እተዋቸዋለሁ😔😔🤥🤥
2026-09-03 08:51:23
7
Eliyana :
ምናልባትም ያፈቅርነውን ሠው እስከመጨረሻው አብረነው ላንኖር እንችላለን ግን ከልባችን አይጠፋም😥 ልቤን ማድከም ብቻ እንዳታደርግብኝ አደራህን ፈጣሪ🙏
2026-08-26 11:06:57
12
ህመሜን በውስጤ 🎼🎶🎵 :
ሰውግንእኮ ለደዚህ አይነትነገር ትኩረትሰተው አያነቡትም እደኔ ጨርሶያነበበ ያውም እያለቀስኩ ሰውግን ደጋጋግመህ አብበህው የማገባህ ፍጥረትነው እኔበጣምነው ከብዙሰወች ብዙነገር የተማርኩት
2026-09-11 13:04:37
1
my every family my LOVE,,❤❤ :
እህ ያለሁበት ሁኔታ ወላሂ አይይይ ሠዉ ሠዉ ማለት ያልተነበበ ወረቀት ማለት ነዉ ይሁን ለበጎነዉ
2026-09-05 08:19:43
2
የየዋህሤትን ልብሠባሪዉነኝ😥 :
ማነዉ እደኔ የሚሥቱን ሥም እያቀማጠለ በዉሥጡ እየተቃጠለ ያለፈዉ ማታ የፈታ 😢😢😢😢😢😢😢😢😢
2026-09-12 15:03:36
1
shemes :
አይ ሁሉም ታማሚ ነዉ ለካ ጤነኛዉ ትንሺ ነዉ
2026-09-06 18:57:03
2
ልጅ ማሜ :
ማንለ ክፉ አለመናገግ ቤኖር
2026-09-08 19:34:13
2
ሸዋ💚🤌 ነው ሀገሬ❤️🩹👑🫶 :
ያለሁበት ሆኔታ........... 🥺
2026-08-21 23:26:55
11
የእናቴ ቀበጥ :
አኔ ያለሁበት ሁኔታ
2026-08-24 02:44:40
12
👉አልሀምዱሊላህ አላህ ሁሊም ከኒጋነዉ💫✨🕋 :
እኒ ያለሁበት ሁኒታ አየእድሊ 😥😥💔
2026-09-09 09:00:35
1
🦋𝑎𝑓𝑛𝑎𝑛 ➽🇹🇷💎🧕 :
"አላህየ በእኔ በልሆነ ሰው አትፈትነኝ😭😭😭😭እህህ"አሁንሰ ድክም አለኝ🥺😥
2026-08-28 20:31:40
5
ልጁ ነኝ የሚካኤል12😘 :
አይ ሁሉም ታማሚ ነው ለካ 😭😭😭😭😭
2026-08-28 11:24:44
5
𝙎𝗲𝘣𝑙𝘪 (ሙሉ ሸዋ) :
መራር እውነታ😭😭😭😭
2026-09-03 14:48:48
0
ልጂ ዳጊ🛐ባለ ማህተቡ☦️ :
በለቅሶ ያነበብኩት እዉነታ💔💔💔
2026-09-03 17:58:04
4
Money is power✅🍋💊 :
እንቧዬን ዋጥ እያረኩት ጨረስኩት😭😭
2026-09-13 18:03:34
1
Z𝑢𝑧𝑢💘 :
አይይይ ያለሁበት ሁኒታ😥😥😥😥😥😥😥😥😥😥💔💔💔💔💔💔
2026-08-22 07:09:18
8
J 👑 🥀👬 የኔ ንጉሶች 👑🥀 R :
ህመሙን የደረሰበት ወላሂ ምንምነገር አያድነውም ግንበቃዝም💔💔💔💔💔😥😥😥😥😥
2026-08-27 20:15:18
2
Ahmed Aminu :
በትክክል ዝምታ ትልቁ መሳሪያ ነው
2026-08-23 00:06:41
3
የFaዘሯ💞💞👸 :
የኔዉዶች ላይክ አረጉኝ መጣሁ🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-08-25 22:40:01
2
Semira :
የደረሰበት ያውቀዋል😭😭
2026-09-11 15:42:56
1
ሴትልይ ለማክበር እናትን ማየት በቂነው :
እርሜና ጤና ሠጥቶን ያለቀሡንን አላህ ያሣየን
2026-08-23 08:14:50
2
ልባም ❤️ሴት 👧አድርገኝ 🥺🙏 :
አይ አለመታደሌ አንዳንድ ቃላቶች የመጨረሻ ስንብት ናቸው አስባችኋል እንደ ቀልድ ተኮራርፋች በዛው ወደ ማይቀረው አለም ሲሄድ የዘላለም ፀፀት
2026-08-30 20:05:28
1
john :
እኔ "የነፃነት ማህተም" እንደማስቀመጥ እቆጥረዋለሁ
2026-08-25 09:16:20
1
የገጠር አራዳ የከተማ እብድ ነው🫣 :
የአለሁበት ሁኔታ🥺
2026-08-28 00:28:50
1
To see more videos from user @seid_959, please go to the Tikwm
homepage.