@musictube369: ንገሪኝ ምነው 😮💨 ✍️ሀገራችን በርካታ የኢትዮጵያ የግጥም እና ዜማ ደራሲዎችን አፍርታለች በርካታ የቅኔ ገበሬዎች ይሁን እንጂ ብዙዎቹ እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ ያላንዳች እውቅናና ክብር እንደተረሱ ከዚህ አለም እረፍት አተናቸዋል😥 በቅረቡ በሚያሳዝን ሁኔታ ከተለየን ያየህራድ አላምረውን ጨምሮ ሻምበል አፈወርቅ ዮሐንስ፣ ኮሎኔል ሳህሌ ደጋጎ፣ ተስፋዬ ለሜሳ፣ ተዘራ ኃይለ ሚካኤል፣ አየለ ማሞ ፣ ሙልጌታ ተስፋዬ (አያሙሌ) ፣ የሸዋሉል መንግስቱ፣ ሱራፌል አበበ፣ ተመስገን ተካ ወዘተ.... በአፋን ኦሮሞ ብዙ ቋንቋም ቢሆን እነ አቡበከር ሙሳ እና አብዲ ቆጴም ቢሆኑ አሁን በሕይወት የሉም ነፍስ ይማር🙏 በኔ ግምት አሁን በህይወት ያሉትም እነ አበበ ብርሀኔ፣ ጸጋዬ ደቦጭ ፣ ሙሐመድ ቆጴ፣ ይልማ ገ/አብ፣ ዓለምፀሐይ ወዳጆ፣ የአበበ መለሰ ፣ አለማየሁ ደመቀ፣ ሞገስ ተካ፣ ታምራት አበበ፣ ቢንያምር አህመድ፣ ሀብታሙ ቦጋለ፣ ታመነ መኮንን ወዘተም.. ቢሆን በተገቢው ልክ ምስጋናና ክብር ያልተሰጣቸው ጉምቱ የዜማ እና ግጥም ደራሲዎች ናቸው ብዬ አምናለሁ🙌 እርግጥ ነው አሁንም ቢሆን እጅግ ተስፋ የሚሰጡ ግሩም ሙዚቃዎች ይቺ ሀገር ማፍራቷን አላቆመችም እንደነ ናትናኤል ግርማቸው፣ ያምሉ ሙሉ፣ ፍሬዘር ታዬ፣ ቢንያም እሸቱ፣ አቡዲ ወዘተ... አይነት ባለተስፋዎች🙏 ✨ውድ ቤተሰቦቼ ታዲያ ዛሬ ብዙአየሁ ድንቅ አርጎ ከዲጄ ፋትሱ እና ሁንአንተ ሙሉ ጋር remix አርጎ በ2000ዓ.ም ከህዝብ ጋር በወዋወቀበት አነጋጋሪ በነበረው አልበሙ ላይ ያካተተውን አስገድሞ በዘመናዊው ዋልያስ ባንድ አጃቢነት በ1971 ዓ.ም ነፍሱን ይማረውና🙏 ሙሉቀን መለሰ በስሙ በሰየመው ውብ አልበም ላይ ነፍሱን ይማረውና ግጥም እና ዜማው በታላቁ ተስፋዬ ለሜሳ የተደረሰውን "ንገሪኝ ምነው" ን ስጋብዛቹ ያለምክንያት አይደለም ይልቁንም አንጋፋውን ድምፃዊ፣ ግጥምና ዜማ ደራሲ፣ ቀማሪ ተስፋዬ ለሜሳን እንድናታውስስ እንድናከብር ስለወደድኩኝ ነው🙌🥰 አንጋፋው ጥበበኛ ጋሽ ተስፋዬ ለሜሳ የምድር ጦር ሙዚቃ ክፍልን ገና በላጋ ዕድሜው ተቀላቅሎ በድምፃዊነት ሙያ ጀመረ፤ ተስፋዬ በጣም የሚያምርና ቀጭን ድምፅ ነበረው ምድር ጦር እያለ ስለ ሙዚቃ፣ ስለ እንቁጣጣሽ፣ ስለ ሀገር የራሱን ድርሰቶች ተጫውቷል... ~ውቢት ኢትዮጵያ በማለት ስለ ኢትዮጵያ በአድናቆት አዚሟል ~ ስለ ሙዚቃ * ፍጥረት የሚወድሽ ሙዚቃ በዚህ ዓለም ላይ ሙዚቃ ውብ እንደ ጨረቃ ድንቅ እንደ ፀሐይ ምነው ባላየሁሽ በቀረብኝ ኖሮ ነፍሴ ሳትወጣ አትቀርም ዘንድሮ...በማለት ለሙዚቃ አዚሟል ~ስለ እንቁጣጣሽ *እንቁጣጣሽ እንኳን ደህና መጣሽ በአበቦቹ በወፎች ታጅበሽ....በማለት አዚሟል... ጋሽ ተስፋዬ ለሜሳ በአዲስ አበባ ብዙም ሳይቆይ ድምፃዊነቱን ባልታወቀ ሁኔታ አቁሞ ወደ ሐረር ተዘዋውሮ በምሥራቅ ዕዝ አሰልጣኝነት ሲሰራ ቆይቶ። ከዚያም ወደ አዲስ አበባ ተምልሶ ውስጡ የነበረውን የሙዚቃ ፍቅር ለበርካታና ታዋቂ ድምፃውያን ድርሰቶቹን መስጠት ጀመረ፤ ከድምፃዊያኑ በጥቂቱ ለክብር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ፣ ለክብር አርቲስት መሐሙድ አህመድ፣ ለአስቴር አወቀ፣ ለኤፍሬም ታምሩ፣ ለሙሉቀን መለሰ፣ ለነፃነትን መለሰና ለበርካታ አርቲስቶች ሰጥቷል... 📌ከነዚህም ውስጥ በጥቂቱ እንመለከት.. ለጋሽ ጥላሁን *ያቺ ቆንጆ ጥርሰ በረዶ ናት *አካል አይንሽን ጣል አርጊብኝ *ፈልጌ አስፈልጌ *እቱ ገላ እቱ ገላ ገላ *የምወድሽ ፍቅሬ የአላንቺ ማን አለኝ *አስታውስሻለሁ *ሕብረት *ያስብኩት ተሳካ *የህይወቴን ተስፋ ፍቅሬን አጣዋት *ምኞት እኮ ሕልም ነው *ፍቅር ቤቷን ሰርታ *ከአንቺ ጋር ካልሆነ *ብዙ ጊዜ አለፈ *ካሰኘሽ *አጉል ነው ለጋሽ መሐሙድ አህመድ *ጉብል የሀገሬ ልጅ ውብ አይናማ *የድሬ ልጅ ነች የከዚራ *ንሽቴ *ማሬ ገላ *ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን ደም ለሙሉቀን መለሰ *ምነው *እንደምነሽልኝ እንደምነሽዋ አልማዜዋ ለንግስቷ አስቴር አወቀ *አማላጅ ሳይቀረኝ መላዕክተኛ ላኩኝ *ሙናዬ ሙናዬ ለኤፍሬም ታምሩ *በፍቅርሽ መያዜን በአንቺ መቸገሬን *አንቺ ልጅ ነይልኝ በሞቴ መውደድ አካላቴ ለነፃነት መለሰ *ይላል ዶጁ ይላል ዶጆ ፏፏ ይላል ዶጁ *አይናማዬ መውደድ ከተማዬ አይናማ ሰው ልቤን አትመልሰው.... *ለኤልያስ ተባባል የመጀመሪያ ሥራዎቹ የሆኑትን እቱ ምን ጠፍቶ ሀገራችን ፍቅርሽ ይዞኛል ምን ይሻለኛል። ከተስፋዬ ለሜሳ ሥራዎች እጅግ ጥቂቶቹ ናቸው፤ ጋሽ ተስፋዬ በደርግ ጊዜ ፈልጌ አስፈልጌን ግጥምና ዜማ ለጋሽ ጥላሁን በሠጠበት ወቅት... "ልዝናና ስወጣ ብቅ ብል በማታ የለችም ካሣንችስ እሷ መች ተገኝታ" የሚለውን ግጥም በሶሻሊዝም ርዕዮተ ዓለም የምን አለ ሥራ መንገላወድ ነው አንድ ሴት ፍለጋ በሚል በሳንሱር ምክንያት ግጥሙን እንዲህ ቀይሮታል... "ከሥራ ስወጣ ብቅ ብል ባማታ የለችም ካሣንችስ እሷ መች ተገኝታ...በሚል 📌በተጨማሪም ጋሽ ተስፋዬ ለሜሳ ድንቅ የሙዚቃ ሰው ነበር ለጥላሁን ገሠሠ አንድ ሙሉ ካሴት በግጥምና ዜማ ድርሰት በሙዚቃ ቀማሪ(ቅንብር) ሰርቶለታል። ጋሽ ተስፋዬ አንተ ብታልፍም ሥራዎችህን እያዳመጥን ስናስታውስህ እንኖራለን። "ነፍስ ይማር"🙌 🗣️ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡 Musictube #fyp #ብዙአየሁደምሴ #ንገሪኝምነው #ethiopianmusic #musictube369
🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
Region: ET
Friday 21 August 2026 20:02:02 GMT
Music
Download
Comments
EyUeL🪽 :
best music of all time buzayew demise negerigh menew ❤🙌🥂
2026-08-22 05:35:22
5
Sammy :
❤❤
2026-08-21 20:07:06
1
wenda :
❤️❤️❤️❤️
2026-08-22 04:44:55
1
Ermiyas_t :
🥰🥰🥰
2026-08-21 20:29:04
1
Mickey Mak :
🔥🤌🏼🎧😎🤙🏼
2026-08-21 20:19:41
1
Ermiyas_t :
👍👍👍
2026-08-21 20:29:07
1
@chapter one :
🥰🥰🥰
2026-08-22 04:57:12
0
ms olds :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-08-22 05:37:58
0
ተክለab :
✌️✌️
2026-08-22 04:43:03
0
Kiduse old Music🎧 :
👌
2026-08-21 20:50:03
0
Luna🌙✨ :
🥰🥰🥰🥰
2026-08-22 10:06:56
0
To see more videos from user @musictube369, please go to the Tikwm
homepage.