@user611745600037: አድስ አበባ የሁሉም ኢትዮጲያዊ የጋራ ህልውናችን ናት። አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ መዲና እና የኢኮኖሚ ማዕከል እንጅ የከተማዋን ስነ-ሕዝባዊ ስብጥር ወይም አስተዳደራዊ ወሰን በአንድ ወገን ፍላጎት ብቻ ለመቀየር የሚደረግ እንቅስቃሴ የሀገር ህልውናን የሚያናጋ ተግባር ነው። ስለሆነም መላው የአድስ አበባ ወጣት ህልውናህን ለመታደግ ከአማራ ፋኖ ጎን የምትቆምበት ጊዜው አሁን ነው። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ቅናቄ ሃገርን ከመፍረስ እና ህዝብን ከመፍለስ ለመታደግ የጀመረው መራራ ተጋድሎ ለድል እስኪበቃ ድረስ የህልውና ትግሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል። ሃገር አፍራሹ ወንበደ ቡድን በአድስ አበባ ከተማ እና በኑዋሪው ላይ እያደረገ ያለው ዘመቻ የሃገሪቱን ማህበራዊ ውል የሚያፈርስ እኩይ ደባ በቀላሉ የሚለወጥ አይደለም!! አማራጩ ጉልበት ነው። በይስሙላው ምክክር ኮሚሺን አማካኝነት በአድስ አበባ ከተማ ይዞታነት ላይ ተፅዕኖ ለመፍጠር የሚደረጉ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች መነሻቸው የታቀደ ደረቅ ወንጀል ነው። አደገኛ የፖለቲካ ማጭበርበር እና ማህበራዊ ኢኮኖሚን ለመንጠቅ የሚደረግ ጥቃት ነው። መፍትሔው ከማልቀስ እና እለታዊ ብስጭት ወጥቶ የፀረ -ብልፅግና ትግሉን መቀላቀል ብቻ ነው። ድርጊቱ ስግብግቡ የብልፅግና ሃይል የህዝቦችን አብሮ የመኖር እሴት በመሸርሸር ሀገርን ለብተና የሚዳረግ እኩይ ተግባር ነው። ስግብግቡን የኦህደድ ብልፅግና በጋራ መታገል የሁሉም ዜጎች ትልቅ ኃላፊነት ነው ። የብልፅግናው አገዛዝ የጠቅላይነት አባዜ የህዝቡን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሕይወት ሙሉ በሙሉ 100% ለመቆጣጠርና ለመግዛት ያለው ከፍተኛ ፍላጎት የአገዛዙን ስግብግብነት ያረጋግጣል። በነጻነት ማሰብን፣ የተለየ ሃሳብ ማቅረብንና ተቃውሞን በፍጹም ማስተናገድ የማይችለው የአብይ አህመድ አገዛዝ አሁን ደግሞ በምክክር ኮሚሺን ስም አድስ አበባን ለመዋጥ እና ለመሰልቀጥ ተግቶ እየሰራ ነው። የብልፅግና መንግስት ፀረ-ሰው አገዛዝ እርምጃዎች ለሰብአዊ መብቶች፣ ለሰው ልጅ ክብር፣ ሕይወትና ደህንነት ምንም አይነት ግድ የሌለው የሰውን ልጅ እንደ መሣሪያ ብቻ የሚጠቀም መሆኑን ላለፉት 8 ስምንት ዓመታት አስመስክሯል። ብልፅግና ጦርነትን እንደ ፖለቲካ ስልት እየተጠቀመ ቀጥሏል። የጠይቅላይነት አባዜ የተጠናወተው ፀረ-ሰው አገዛዙ ብልፅግና የሰዎችን ነጻነትና ስልጣን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሩ ስር ለማዋል በሚያደርገው እብደት፣ የሰዎችን ሕይወት፣ ክብር፣ ሰብአዊ መብት የሚረግጥና የሚያጠፋ ጭካኔ የተሞላበት የፈላጭ ቆራጭ አስተዳደር ነው። ስለዚህ መላው የኢትዮጲያ ህዝብ እና አድስ አበቤ ከፋኖ እና ከትብብር ሃይሎች ጋር ልትቆሙ ይገባል!! ዝንታለም አማራ ወይራው አማራ
የፈራ ይመለስ የፀና ያሸንፋል 🐯
Region: DE
Saturday 22 August 2026 14:28:17 GMT
Music
Download
Comments
ዝምተኘዉ :
💪💪💪
2026-08-22 20:39:37
0
/Semira/ :
🥰🥰🥰
2026-08-22 16:50:40
0
ኤደን ቤተ አማራ 21 🦁 :
🥰🥰
2026-08-22 17:49:14
0
user52907667572 :
❤️❤️❤️
2026-08-22 14:44:11
0
እየበ ሠጨኝ🇨🇬👌 :
💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪💪
2026-08-22 14:33:32
0
ቤተ - አማራ :
💪💪
2026-08-22 15:07:44
0
To see more videos from user @user611745600037, please go to the Tikwm
homepage.