@awokederb: ✍️ አንድ ጊዜ መውደቅ... የሕይወት መጨረሻ አይደለም። መሰናከል... የድክመት ምልክት አይደለም። መሸነፍም... ለዘላለም ተሸናፊ ሆናችኋል ማለት አይደለም። ምክንያቱም... ከወደቀበት የማይነሳው ዛፍ ብቻ ነው። ሰው ግን... ይወድቃል። ይደክማል። ያለቅሳል። አንዳንዴም... "ከዚህ በኋላ አልችልም!" ብሎ ይቆማል። ነገር ግን... የሰው ታላቅነት በመውደቁ ሳይሆን፣ ከወደቀበት ዳግመኛ በመነሳቱ ይለካል። ሕፃን መራመድ የተማረው... ብዙ ጊዜ ከወደቀ በኋላ ነው። ወርቅ... በእሳት ካልተፈተነ አያበራም። አልማዝ... ከፍተኛ ጫና ካላለፈ ውበቱን አያሳይም። ሰውም...ከፈተና በኋላ የበለጠ ይጠነክራል። ስለዚህ...ዛሬ ከወደቃችሁ... ራሳችሁን ላይ አትፍረዱ። ዛሬ ከተሳሳታችሁ... ሕልማችሁን አትቅበሩ። ዛሬ በሰዎች ብትተዉ... ራሳችሁን አትተዉ። አስታውሱ... ከመሬት ላይ የምትነሱበት ቦታ... ወደ ከፍታ የሚወስዳችሁ የመጀመሪያ ደረጃ ሊሆን ይችላል። ዛሬ የሚያሳዝናችሁ ጉዳት... ነገ የሚያኮራችሁ ታሪክ ይሆናል። ሰዎች የሚያስታውሱት... ፈጽሞ ያልወደቀውን ሳይሆን፣ ብዙ ጊዜ ወድቆም ደጋግሞ የተነሳውን ነው። ስለዚህ... አትፍሩ። አትቆሙ። አትተዉ። ምክንያቱም... መውደቅ ዕድልን አይገድልም፤ ተስፋ መቁረጥ ግን ይገድላል። የሚነሳ ሰው... ሁልጊዜ ከወደቀበት ከፍ ብሎ ይታያል። ከወደቀበት የማይነሳው ዛፍ ብቻ ነው፤ እናንተ ግን ዛፍ አይደላችሁም። ተነሱ፣ እንደገና ሞክሩ፣ እንደገናም አሸንፉ። Follow, Like, Share, Repost እና Copy Link በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!

Awoke12
Awoke12
Open In TikTok:
Region: ET
Saturday 22 August 2026 19:47:52 GMT
292
8
0
2

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @awokederb, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About