@habashaourchannel: ዛሬ በአዲስ አበባ መገናኛ አደባባይ ላይ የታየው ክስተት የሀገሪቱን ወቅታዊ የፖለቲካ ምህዳር ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ማሳያ ነው። አንድ ዜጋ በሰላማዊ መንገድ የበላዮቹን የአስተዳደር አካላት መቃወም፣ መፈክር ማንገብና ድምፁን ማሰማት ሕገ-መንግስታዊ መብቱ ነው። በኢፌድሪ ሕገ-መንግስት ላይ የመናገር፣ የመሰብሰብ እና ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቶች በግልጽ ቢሰፍሩም፣ በተግባር ግን መብቶቹ የሚሰሩት ለአንደበት ማስዋቢያ ብቻ እየሆኑ መጥተዋል። ይህ ዜጋ “አምባገነኑ ከሥልጣን ይውረድ” የሚል የራሱን የፖለቲካ አቋም በወረቀት ላይ ይዞ አደባባይ በመውጣቱ ብቻ፣ በጸጥታ አካላት ተከቦ በአሁኑ ሰዓት ወደማይታወቅ ቦታ ታፍኖ ተወስዷል። መብትን በተግባር መተርጎም ወንጀል በሆነባት ሀገር፣ የሕግ የበላይነት ሳይሆን የኃይል የበላይነት እየነገሰ መሆኑን ይህ ድርጊት በድጋሚ ያረጋግጣል። የሃሳብ ልዩነትን በጠመንጃ እና በማፈን ለማፈን መሞከር የትኛውንም ሥርዓት ዘላቂ አያደርገውም። የታፈነው ዜጋ በአስቸኳይ ያለበት ታውቆ ለሕግ እንዲቀርብ ወይም እንዲፈታ እንጠይቃለን! Addis AbabaThe event that unfolded today at Megenagna square in Addis Ababa is a stark reflection of the current political reality in Ethiopia. A citizen exercising his fundamental right to peaceful protest was surrounded by security forces and has now been abducted and taken to an undisclosed location, simply for holding signs that criticized the ruling administration.While the FDRE Constitution explicitly guarantees the rights to freedom of speech, assembly, and peaceful demonstration, these provisions remain a mockery in practice. They exist only as lip service for international rhetoric, while the reality on the ground is ruthless suppression. Expressing a dissenting political view is treated as a capital offense.Attempting to silence peaceful dissent through state-sponsored abductions and intimidation will never foster stability or peace. We demand to know the whereabouts of this citizen and call for his immediate and unconditional release!