@silentwarrior_et: እራሴን የማሰቃይበት ነገር ነገር ያጣሁ ይመስል ልቤ የሚያርፍበትን ሰው እንኳን እንደማልፈልግ እያወቅሁ አንቺን አፈቀርኩሽ። ከሁሉም በላይ የሚያስቀጣኝ ነገርግን የወደድኩሽ መሆኔ ሳይሆን በልቤ ውስጥ ቦታ ሰጥቼሽ ከዚያ በኋላ ያንን ቦታ ባዶ ሆኖ ማየቴ ነው፡፡ አንቺን ከማግኘቴ በፊት ልቤን ለማንም እንዳልሰጥ ተምዬ ነበር። ነገር ግን አንቺ መጣሽና ያልኩትን ሁሉ አስረሳሽኝ፡፡ በአንቺ ውስጥ የሆነ ነገር አገኘሁ እኔም ሳላስበው ልቤን ሰጠሁ፡፡ ከዚያ በኋላ አንቺ ተራ ሰው አልነበርሽም የቀኔ ሀሳብ የሌሊቴ ትዝታ የነገ እቅዴ አንቺን አፈቀርኩሽ" እኔ ግን ያንን ሁሉ እንደሚቀጥል አስቤ ነበር። አንቺ ግን ተለየሽኝ፡፡ እኔ አንቺን እያሰብኩ የነገን ህይወት ስሳል አንቺ ግን ከዚያ ስዕል ውስጥ ወጥተሽ ተውሽኝ፡፡ አሁን እኔ የማሰቃየው ራሴን ነው ምክንያቱም ልቤ የማይረሳውን ነገር አእምሮዬ እንዲረሳ እገደዋለሁ፡፡ አንዳንድ ጊዜ “ለምን አፈቀርኳት?" ብዬ እራሴን እጠይቃለሁ፡፡ መልሱን ግን አላገኘሁም፡፡ ምናልባት ፍቅርመቼ እንደሚመጣ ስለማይጠይቅ ይሆናል፡፡ ምናልባት ልብ ማንን እንደሚመርጥ እኛ ስለማንወስን ይሆናል፡ እንደገና ቢመለስ ጊዜው ልቤን እንደገና እንደምሰጥሽ አላውቅም ግን አንድ ነገር አውቃለሁ—አንቺን በእውነት አፈቅርሽ ነበር፡፡ እና አሁን ከሁሉ በላይ የሚያሳምመኝ ያ ፍቅር ነው አንቺን ማጣቴ ብቻ ሳይሆን እኔ በአንድ ወቅት የነገ ህይወቴ አድርጌ የመረጥኩሽ ሰው አሁን የሚያልፈኝ ትዝታ መሆንሽ ነው፡፡
Silent Warrior ⚔️
Region: ET
Monday 24 August 2026 16:41:03 GMT
Music
Download
Comments
Zinet :
ፍቅር ደስ የሚል ስቃይ እብደት ነው
ማፍቀር መታደል መፈቀር ፀጋ
ፍቅር ያፈቀሩትን ማግኘትም አይደለም
2026-08-31 14:17:28
0
Nanis12 :
ስቃይ ብቻ መኖር እራሱ ያስጠላል እንጂ ግን የመጨረሻክ በደንብ ይሆናል💔
2026-08-31 10:04:12
0
Zinet :
ማፍቀር መታደል መፈቀር ፀጋ ነው
ፍቅርን ይታደሉታል እንጅ አይታገሉትም ወዳጀ
ፍቅር ያፈቀሩት ሰዉ የራስ ማረግ ብቻ አይደለም ያፈቀሩትን ማግኘትም አይደለም
ፍቅር ደስ የሚል ስቃይ እብደት ነው
2026-08-25 02:40:25
1
To see more videos from user @silentwarrior_et, please go to the Tikwm
homepage.