@jajanhemat__:

Yongki sugeha | jajanhemat
Yongki sugeha | jajanhemat
Open In TikTok:
Region: ID
Tuesday 25 August 2026 00:00:22 GMT
219
1
0
0

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @jajanhemat__, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

ሸይኽ ሙሐመድ አሊ አደም አል-ኢትዮቢ፣ የሐበሻው ሙፍቲ የነበሩት ታላቁ ዓሊም ሸይኽ አሊ አደም ልጅ ናቸው። ታላቁ የሐዲስ ሊቅ ሸይኽ ሙሐመድ አሊ አደም በ1366 ዓ.ሂ. በወሎ ክፍለ ሀገር፣ በወርሂመኑ አውራጃ ተወለዱ። ገና በልጅነታቸው ቁርኣንንና የመጀመሪያ ደረጃ የዲን ትምህርታቸውን ከአባታቸው ሸይኽ አሊ አደምና ከአካባቢው ታላላቅ ዑለማዎች ቀሰሙ።  የነሕው፣ የፊቂህ፣ የሐዲስ፣ የበላጋ እና ሌሎች የእውቀት ዘርፎችን አጥንተዋል። እንደ አልፊያቱ ኢብኑ ማሊክ እና አልፊያቱስ-ሱዩጢ ያሉ ግዙፍ የግጥም ኪታቦችንም በቃላቸው ሀፍዘው ነበር። እነዚህን የእውቀት ዘርፎች ከተለያዩ የሀገራችን ዑለማዎች ዘንድ ተምረዋል። ከአባታቸው ሸይኽ አሊ አደም፣ ሸይኽ አብዱልባሲጥ ሙሐመድ ሃሰን አል-ቦርኒይ፣ ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ሙሐመድ ዳኒይ፣ ሸይኽ ሙሐመድ ሰዓድ፣ ሸይኽ ሙሐመድ ራፊዕ እና ከሌሎች ታላላቅ ዑለማዎች ቀስመዋል፤ የብቃት ሰርተፍኬትም አግኝተዋል። እውቀታቸውን ለማስፋፋት ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ በመሄድ በመካ ጥቂት ጊዜ ተማሪ ሆነው ቆዩ። ከዚያም ወደ “ዳሩል ሐዲስ” በመሄድ የተማሪነት ፈተና ተፈተኑ። ከፍተኛ ውጤት በማምጣታቸው ለመማር የሄዱት ሸይኽ ሙሐመድ አሊ አደም ወደ መምህርነት ተሸጋገሩ። በመስጂደል ሐረምና በ“ዳሩል ሐዲስ” ተቋም ውስጥ ለበርካታ ዓመታት በመምህርነት በማገልገል በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን አፍርተዋል። ይህ ጊዜ ለሸይኽ ሙሐመድ አሊ አደም ትልቅ አጋጣሚ ነበር። የተለያዩ ኪታቦችን ለማየት፣ በርካታ ማንበብና ማገላበጥ፣ የሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ እና የሸይኽ ሙሐመድ ቢን አብዱልወሃብን ኪታቦች በሰፊው ማጥናትና መመርመር ቻሉ። ይህ ሁኔታ ግን ቀላል አልነበረም። በሀገራቸው ተምረውት ከመጡት የአሻዒራ ዐቂዳ ጋር ተጋጨባቸው። ይህም በደንብ እንዲያጠኑና ወደ ትክክለኛው የሰለፎች ዐቂዳ እንዲገነዘቡ መንገድ ከፈተላቸው። ከሀገራቸው ያመጡትን የተሳሳተ ዐቂዳም እርግፍ አድርገው ጣሉት። ወደ ሀገራቸው አባታቸውን ለመጠየቅ በመጡ ጊዜ ያጋጠማቸውን ሁኔታ እንዲህ ያስታውሳሉ“አባቴን ለመጠየቅ ሀገሬ በተመለስኩ ጊዜ አንድ ሰው ‘ወሃብይ ሆነሃል’ አለኝ። እኔም ‘የለም፤ መረጃዎች የሚደግፉትን አቋም ነው የምከተለው። ወደ መካ ከመጓዜ በፊትም ትክክለኛ መረጃዎችን እከተል እንጂ ጭፍን ተከታይ እንዳልነበርኩ ታውቃለህ’ አልኩት። እርሱም ‘አዎ፣ አውቃለሁ፤ ነገር ግን ማጥበቅ ላይ ጨምረሃል’ አለኝ።‘እኔም ኢማሙ ሻፍዒይ በሂጃዝና በኢራቅ የነበራቸውን የፊቂህ አቋምና ምልከታዎች ወደ ግብፅ ከተጓዙ በኋላ የተለያዩ መረጃዎችን ሲያገኙ ከነበራቸው አቋም አልተመለሱምን? እኔም ልክ እንደዚያው ከሀገሬ ሰዎች የተሰወሩባቸውን ማስረጃዎች ባገኘሁ ጊዜ ተከተልኩት። ይህን ደግሞ ዕድሜዬን ሙሉ ሳደርገው የነበረ ነው’ አልኩት” ይላሉ። ሸይኽ ሙሐመድ አሊ አደም በወዳጆቻቸውና በሐበሻ ዑለማዎች ዘንድ “ሸይኽ ሙሐመድ ሸይኽ” በመባል ይታወቃሉ።  ልባቸው በሐዲስ እውቀት ፍቅር የተሞላ ሲሆን፣ በዘርፉ ያዘጋጇቸው ኪታቦች ወደር የሌላቸው መሆናቸውን የዘመናችን ታላላቅ ዑለማዎች መስክረዋል።ከፃፏቸው ኪታቦች መካከል “አል-በሕር አል-ሙሒጥ አሥ-ሠጃጅ ፊ ሸርሒ አል-ሙስሊሚል ሃጃጅ” የተሰኘው በ50 ቅጽ የተዘጋጀ የሰሒሕ ሙስሊም ማብራሪያ ነው። እንዲሁም “ዘኺረቱል ዑቅባ” በ42 ቅጽ የተዘጋጀ የሱነን አን-ነሳኢ ማብራሪያ ነው። እነዚህ ድርሳናት የሸይኽ ሙሐመድ ሸይኽ የእውቀት ምጥቀትን ያሳዩ፣ ለትውልድም እውቀታቸውን ያስተላለፉ ዘመን የማይሽራቸው መጻሕፍት ናቸው። ሸይኽ ሙሐመድ አሊ አደም በዐረብኛ ቋንቋና በግጥም እጅግ የላቀ ችሎታ ነበራቸው። በተለያዩ የእስልምና እውቀቶች ዙሪያ በሺዎች የሚቆጠሩ ስንኞች ያላቸውን አልፊያዎች ደርሰዋል። የሐዲስ ኪታቦችን በሙሉ ከነሰንሰለታቸውና ኢስናዳቸው የሸመደዱ ሲሆን፣ ወደ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) የሚደርሱ ከ1,000 በላይ ኢጃዛዎች ነበሯቸው።እጅግ ዝቅተኛና ዙህድ፣ ዱንያን የናቀ ሕይወትን ይመሩ የነበሩ፣ በኢባዳቸውና በትህትናቸው የተመሰገኑ ዓሊም ነበሩ። በሐዲስና በሱና እውቀታቸው በዘመናችን ካሉ ታላላቅ ዓሊሞች አንዱ ነበሩ። ሀገራችንንም በኢልም ያስተዋወቁ ድንቅ የወሎ ዑለማዎች ፍሬ ናቸው። እንደ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ፣ ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን፣ ሸይኽ ፈውዛን እና ሸይኽ ዐብዱልከሪም አል-ኹደይር ያሉ ታላላቅ ዑለማዎች አድናቆታቸውንና ምስክርነታቸውን ሰጥተዋቸዋል። እንደ ሸይኽ አል-አልባኒ፣ ሸይኽ ሙቅቢል አል-ዋዲዒ፣ ሸይኽ ረቢዕ አል-መድኸሊ እና ሌሎች በርካታ የዘመናችን ዓሊሞችም በሐዲስና በኢስናድ እውቀታቸው የላቀ ደረጃ እንደነበራቸው መስክረዋል። ታላቁ ዓሊም እውቀትን ሲያስተላልፉና ሲያገለግሉ ቆይተው፣ በተከበረችው የመካ ከተማ ወደ አኼራ ሂደዋል። ሸይኽ ሙሐመድ አሊ አደም አል-ኢትዮቢ አል-ወሎዊይ رحمه #አፍሪካ_ቲቪ  #የህይወት_ጎዳና

About