@yebichuu: ዛሬ የቀድሞ የአማራ ክልል ፕሬዘዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በአሜሪካን ሃገር ፓርኪንግ እየሰሩ የሚያሳይ አንድ ቪዲዮ ተለቆ በየቦታው መነጋገሪያ ሆኗል ወዳጄ፣ ፖለቲካውን ለጊዜው እንተወውና እንደ ሰው እናስበው። በአንድ ወቅት የክልል ርዕሰ መስተዳድር፣ ሚኒስትር ወይም ሌላ ከፍተኛ ኃላፊ ሆነህ ከሠራህ በኋላ ከሥልጣን ስትወርድ፣ ባለፈ ክብርና ባለፈ ማዕረግ ላይ ተንጠልጥለህ ከመኖር ይልቅ ሥራን በሥራነቱ አክብረህ፣ ዝቅ ብለህ ሠርተህ ቤተሰብህን ማስተዳደር የአስተዋይነት፣ የጽናት፣ የትልቅነትና የራስ መተማመን መገለጫ ነው። ሥራ አያሳፍርም። ሰውን የሚያሳፍረው ሳይሠራ መኖር፣ የሕዝብን ሀብት መዝረፍና በሌሎች ላብ ላይ ተንጠልጥሎ መኖር ነው። በንጹሕ ላብ ሠርቶ፣ ጥሮ ግሮ ማደር የሚሰጠው ውስጣዊ ሰላም ከማዕረግና ከወንበር የሚበልጥ ነው። በዚህ ረገድ እኔ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ሳላደንቅ አላልፍም። በግሌ ከአቶ ገዱ ጋር በፖለቲካ ላንስማማ እንችላለን፤ አንዳንድ አቋማቸውም ላይመቸኝ ይችላል። ይህ ግን ሰው እንደ ሰው የሚያሳየውን ጽናትና ቆራጥነት እንዳላከብር አያደርገኝም። ይህ ለአሁን በሥልጣን ላይ ላሉ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ ኃላፊዎችም ትልቅ ትምህርት ነው። ሥልጣን ዘላለማዊ አይደለም፤ ወንበርም የማንም ቋሚ ንብረት አይደለም። ዛሬ ሚኒስትር የሆነ ነገ ተራ ዜጋ ይሆናል። ስለዚህ ሥልጣን ላይ ሳላችሁ ለነገ የሚቀርላችሁ የሰበሰባችሁት ሀብት ሳይሆን በንጹሕ እጅ ሕዝብን ያገለገላችሁበት ታሪክና ክብር ነው። ከሥልጣን በኋላ በገዛ ላብህ የምትበላበትን ሥራ መሥራት አያሳፍርም፤ የሚያሳፍረው ከሥልጣን ከወረድክ በኋላ ሳትሠራ እንድትኖር የደሃውን ሕዝብ ሀብት ቀድመህ መዝረፍ ነው። ሥራ ክብር ነው። ወንበር ያልፋል፣ ማዕረግ ያልፋል፣ ሥልጣንም ያልፋል፤ ሰውን ተከትሎ የሚቀረው ግን ሥራው፣ ስሙና ሕሊናው ነው። ሰላም ለሀገራችን ይሁን።

Yebichu
Yebichu
Open In TikTok:
Region: ET
Tuesday 25 August 2026 04:46:17 GMT
121673
12147
283
1039

Music

Download

Comments

temesgenbekel
ናትናኤል የመድሀኒት አለም ልጅ :
GoFundMe ተደርጎ ፎ አርገን እናኑረው የምር ::
2026-08-25 06:32:19
502
ethio_canada_agent
. :
1 እንጀራ ለመብላት ሀገር መሸጥ እደሌለብን ያስተማረን ❤️🫡
2026-08-25 07:08:26
968
yohannesbayu0
yohannes bayu :
አማራ ለህሊናው እንጂ ለሆዱ አይሞትም
2026-08-25 08:40:30
227
miftah00000
MIF :
it will aggravate the amhara region politics(Fano fighting)
2026-08-25 08:30:21
1
discovernature_
Discover Nature :
He is rational and a real patriot.
2026-08-25 09:16:13
5
yelibvoice1
yelib voice :
ሙዚቃው ቦታውን ያገኘው አሁን ነው ለእውነት ሰትኖር የህሊና ሰላም ታገኛለህ🥰🥰🥰
2026-08-25 05:01:34
397
danielf07
Daniel :
Gofund me for this Jegna
2026-08-25 06:58:12
11
mike32946
mike :
ንፁ ሕሊና ምቹ ትራስ ነው!
2026-08-25 04:58:40
229
stayhere2116
live life :
ማንም ሰው እዳ ከሌለብህ ሰላም ያለው እንቅልፍ ትልቅ እረፍት ነው ወዳጄ🙏🙏
2026-08-25 06:06:53
171
kebu4677
ሰቆቃዉ :
ሙዚቃዉ ቦታዉን አገኘ
2026-08-25 06:08:19
169
mahletwondmnew24
Mahiii :
am proud of you 💪💪💪💪💪
2026-08-25 07:53:52
1
yosefki8
yosef :
🥰አማራ ማለት እራሱን ገሎ ሀገር ያቆመ ነው
2026-08-25 09:03:50
67
user9027299578509
user9027299578509 :
honest person prode
2026-08-25 08:16:55
1
donotquit2026
እስኪደክምህ ሩጥ :
ለህዝብ ስትቆም ገንዘብ ሳይሆን ህሊናህ ነዉ የሚያሳስብህ 🥰
2026-08-25 08:00:22
73
amanuelsis_16
ዘአማኑኤል :
እንኮራበታለን ሰራ እንጅ አልሰረቀም❤️
2026-08-25 06:45:09
80
1mimi353
Mimi coca :
እውነት ነው👍👍👍👍👍
2026-08-25 09:51:21
11
amha327
Abimael Surgical consultancy :
the truth man
2026-08-25 07:14:49
1
saveasbel24
Bel 24 :
ትክክለኛ ሙዚቃ ለ ትክክለኛ ሰው🥰
2026-08-25 05:34:37
45
sewmhone4
ሰማይ :
ዘፈኑ ቦታውን አገኘ
2026-08-25 07:42:49
12
beba0brook
beßa :
ንፁህ ህሊና ከምቹ ትራስ በላይ ነው !
2026-08-25 09:25:47
8
samson_coder
Samson Belayneh :
ሁሉም ፓለቲከኛ እንደሱ ቢሆን ኖሮ በቂ የሆነ ሀብት ነበር ሀገሪቱ ላይ
2026-08-25 09:13:02
17
ethioriders
EthioRiders :
ክቡር አቶ ገዱ🙏🙏🙏🙏🙏እናመሰግናለን!!! አለመስረቅን ፣ የስራ ክቡርነትን ፅናትን ስላስተማርክ ትውልድ ያመሰግንሃል። 💚💛❤ዓማራ
2026-08-25 12:20:07
11
henok6168
henok :
በስልጣን ዘመኑ አለመዝረፉ ነው የሚያሳይ
2026-08-25 07:04:22
22
hewaneyob
Hewan :
ሃገር ያመሰግንሃል እድሜ ብቻ ይስጥህ
2026-08-25 06:24:27
14
To see more videos from user @yebichuu, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About