@.al.nur.hamas: የቀድሞ የአማራ ክልል አስተዳደር ጀግናው ገዱ ሚኒስትር የነበሩት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በአሜሪካን በሚገኝ ፓርኪንግ ተቀጥረው እየሰሩ የሚያያሳይ ቪዲዮ ተለቋል። ቪዲዮውን እንዳየሁ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን አከበርኳቸው ... የቀበሌ ሊቀመንበር በቢሊዮኖች ብር ዘርፎ ገንዘቡን በዶላር ቀይሮ ወደ ውጭ ሀገራት በማሸሽ ቤት ፣ ሞሎች ገዝቶ በሚንፈላሰስበት .. የእድሜ ልክ ቅንጡ ህይወት እንዲመሩ የሚያደርግ ብር በሚዘረፍበት ሀገር ... አቶ ገዱ ከስልጣን ዘመናቸው በኃላ ፓርኪንግ ሲሰሩ መመልከት ይደንቃል። ርዕሰ መስተዳድር ፣ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ከመሆናቸው በተጨማሪም የኢትዮጵያ ቁልፍ ሁለተኛው ግለሰብ ነበሩ። ያሹትን ቢያደርጉ ሀብት የሚያግበሰብሱበት ፣ ከባለሃብቶች ጋር ተሻርከው የፈለጉትን የውጭ ንግድ የሚሰሩበት እድል ነበራቸው። ሌላው ቢቀር ከስደት በኃላ ዲያስፖራውን አስቸግረው በ go fund me ዶላር ሰብስበው ቤት ተቀምጠው ሳይሰሩ የሚኖሩበትን መላ መፍጠር አይከብዳቸውም ነበር። በስልጣን ዘመናቸው የተዋወቋቸውን ዲፕሎማት ፣ ባለሃብቶችን ጠይቀውም የሚከለከሉም ግለሰብ አይደሉም። ነገር ግን ሁሉንም አማራጭ አልተጠቀሙም። አንድ ሚሊዮን ዶላር ቢኖራቸው እንኳን አሜሪካን ላይ ቅንጡ ህይወት መኖር ያስችላቸው ነበር። ይህም አልሆነም። የሸገር ከተማ ከንቲባ በሁለት አመት ሹመቱ ካናዳ ላይ ቅንጡ ቤት በገዛበት ሀገር ... ከሁለት አስር አመታት በላይ የሀገሪቱ ቁልፍ ሰው ዶክተር ገዱ ከንፅህናቸው ጋር ፓርኪንክ እየሰሩ ህይወታቸውን ይገፋሉ። በስልጣን ዘመናቸው የነበራቸው ego ሳይገድባቸው ፣ ክብራቸው ሳይሸብባቸው ፣ የእድሜ መግፋት ሳይዛቸው ፣ ሰው ምን ይለኝ ይሆን ከሚል ይሉኝታ ወጥተው ... ቆመው የመኪና ጥበቃና የፓርኪንግ አገልግሎት ለመስጠት ደፋ ቀና ይላሉ። ከዚህ በላይ ክብር ... ከዚህ በላይ የሞራል ከፍታ ... ከዚህ በላይ በእራስ መተማመን ከየት ይገኛል ?? ..... ከአቶ ገዱ ጋር የፖለቲካ ልዩነት ሊኖር ይችላል ፣ በስልጣን ዘመናቸው በፈፀሟቸው ስራዎች ጠባሳ ሊኖር ፣ አለመግባባት ሊሰፍን ይችላል .... ይህ ጤናማ ነው። ነገር ግን ምንአልባትም በኢትዮጵያ ታሪክ ለዛውም ዘረፋና ፣ ሌብነት በሚበረታታበት ፣ ተራ የወረዳ ባለስልጣናት ቢሊየነር በሚሆኑበት #የብልፄ ዘመን .... ከነ ንፅህናቸው በመኪና ጥበቃ ስራ ተወጥረው ሲሯሯጡ የታዩ ብቸኛው ግለሰብ ናቸው። ከአምስት አመት በፊት በነጩ ቤተመንግሥት የአሜሪካን ፕሬዚዳንት ድናልድ ትራንፕ በክብር ተቀብሏቸው ከግብፅና ከሱዳን አቻዎቻቸው ጋር ስለ ህዳሴው ግድብ የተወያዩ ባለስልጣን ... ዛሬ ዝቅ ብለው መኪና የሚጠብቁ በሁለቱም የህይወት መንገዳቸው ከፍ ብለው የጎሉ ታላቅ ግለሰብ ናቸው። ከልቤ አከበርኳቸው 🙏🙏 . .
{Feth Nur} የሲቲ ና ኸድጃ ልጅ
Region: DE
Tuesday 25 August 2026 09:30:01 GMT
Music
Download
Comments
meron.hrb :
Respect
2026-08-25 19:56:01
0
shagiz :
አንድ አምራ አስር ብር ብሰጠዉ 80 million x10=800 million challenge yijemerlllet
2026-08-25 15:05:04
25
JA AMITE :
ሀገር በትንንሽ እጆች ገብታ ፍዳችን አየን😓
2026-08-25 11:16:57
7
የተዋህዶ ልጅ 🥰🥰 :
ከሁሉ ነገር በላይ የህሊና ሰላም ይበልጣል በጣም ጀግና ነህ 🥰🥰🥰🥰
2026-08-25 16:55:13
13
Mihret🤘🤘💪 :
አማራ 🤴
2026-08-25 16:17:25
4
God's plan is always perfect :
😂😂😂😂😂
2026-08-25 18:31:29
0
Alex€*! :
ገና ነዉ አልመሸም
2026-08-25 18:39:20
0
user168643 :
እድሜና ጤና ይስጦት የአገር ባለውለታ ኖት እርሶ እግዚአብሔር እድሜና ጤና ይስጦት🙏
2026-08-25 17:24:38
1
Sine :
ለስራ ያላቸው ትጋት የሚደነቅ እና የሚያኮራ ቢሆንም መካድ የማልችለው እውነት ግን የሀገሬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር የነበረ ሰው በሰው ሀገር ተሰዶ ፓርኪንግ ሲሰራ እንደማያት የሚያሳዝን ነገር የለም ።
የተከበሩ ገዱ ኢትዮጵያን ወክለው ስለ አባይ ተደራደረዋል ነጩ ቤተ መንግስት ተገኝተው ትራምኘን ሞግተዋል የተለያዩ የውጭ ዲፕሎማቶችን ተቀብለው አነጋግረዋል ቢያንስ የሚመጥናቸውን ስራ ቢሰሩ በግሌ ደስተኛ ነኝ ቢያንስ አማካሪ መሆን አይችሉም? እንደ ሀይለማሪያም ደሳለኝ የሚመጥናቸው ቦታ አይገኙም ? እንደ ሀገር ልናዝን ነው የሚገባን ሰው አይውጣልሽ ተባላ የተረገመች ሀገር ሆንን እኮ ! እሳቸው ፓርኪንግ በመስራታቸው የህዝብ ብር ስላልበሉ ነው ቢበሉ ኖሮ የተሻለ ነገር ይኖራቸው ነበር የምትሉ አደብ ግዙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሆኖ ያገለገለ ሰው እኮ ሀገር ቢለቅ እንኩዋን ከሀገር ውጭ የሚያርፍበትን የተሻለ ቦታ አያጣም ።
2026-08-25 17:25:26
1
🌸🌸 :
የኛ ጀግና 🙏🙏🙏
2026-08-25 19:18:45
0
awelibo2 :
:ጋሽ ገዱ 🦁👑👑በጣም Respekt 🇪🇷ነኝ ግን የህ ወርቅ ኣባታቹ ለምን ሳርፕራይ ኣታድርጉም 10$ ከ 100.000 ሰው ኣልገኝም በትንሹ ቤት ይገዛል
2026-08-25 19:17:03
0
beladn :
ፓርላማው ጆነሳይድ ነው ይጠይቃል
2026-08-25 17:26:57
0
burra😒🤑 :
ሰላም የትነህ🤔
2026-08-25 17:28:09
0
Yabsira :
ጀግና
2026-08-25 17:43:37
0
Mule Mix🦅🦅 :
በነገራችን ላይ ይህ ለአማራ ፖለቲካ ትልቅ መኢልክምትም አለው
2026-08-25 18:05:40
0
hh :
🥰
2026-08-25 18:01:54
0
soli@ :
Anjeten new yebelaw yene abat🥺
2026-08-25 15:34:08
0
😘nina 😘yoki 😍 :
Yes 🙏
2026-08-25 15:30:49
0
abrham yonas :
2026-08-25 17:26:07
0
user168643 :
ሁሉም ባለ ስልጣን እንደሳቸው ታማኝ ቢሆን አገራችን የት በደረሰች ወጣቱም ስራ በማጣትና ተስፋ በመቁረጥ የሊቢያ በረሀ ላይ ባላለቀ
2026-08-25 17:22:53
0
trap queen :
ጀግና ማርያምን
2026-08-25 17:09:53
0
𝕒𝕡𝕚𝕕𝕦💥 :
ene le Ethiopia be merake alwagam😔
2026-08-25 10:42:29
0
To see more videos from user @.al.nur.hamas, please go to the Tikwm
homepage.