@beimnet19: በኢትዮጵያ ውስጥ ስልጣን የገንዘብ መዝረፊያ መንገድ ነው፤አብዛኛው የመንግስት ሹመኛ ወደ ስልጣን ሲመጣ ታሳቢ የሚያደርገው ከሕዝብ የሚዘርፈውን ገንዘብ ነው። “ሲሾም ያልበላ፣ ሲሻር ይቆጨዋል” የሚል ብሂል በሚናገርበት ሀገር ያደገ ሰው፣ በክብር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ላይ ቢሳለቅ የሚገርም አይደለም። አቶ ገዱ እጃቸው ንጹሕ የሆነ ሰው በመሆናቸው፣ የፓርኪንግ ሥራ እየሠሩ ሕይወታቸውን እየኖሩ ነው። በፓርኪንግ ሥራ ላይ መሰማራታቸው ሊያስከብራቸው የሚችል እንጂ፣ አንገት ሊያደፋ የሚችል አይደለም። የማዝነው ሌብነት በሕዝብ ደረጃ በዚህ ልክ እውቅና ሲሰጠው መመልከቴ ነው። ሕዝቡ ከገዱ አንዳርጋቸው ይልቅ፣ ቢሊዮን ዶላር ዘርፈው በኬንያና ዱባይ ቪላ የገነቡትን ሰዎች ያደንቃል። አቶ ገዱ ፋብሪካና ጀት በሚሰረቅበት ዘመን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነበሩ፤ በአብይ አህመድ የእብደት ዘመንም ከፍተኛ የመንግሥት ሹማኛ ነበሩ። የመዝረፍ ዕድል ቢኖራቸውም አላደረጉትም። ስለሆነም የተከበሩ አቶ ገዱ ሊከበሩ እንጂ፣ ሊሸማቀቁ አይገባም። .......መውጫ..... ትናንት “ለዙፋን ያበቃን ገዱ ነው” ሲሉን የነበሩ ልጆች፣ ዛሬ ገዱ አንዳርጋቸው ላይ ለመሳለቅ ሲሞክሩ ማየት ያስገርማል። ለነገሩ፣ ጅብ ውለታ አያውቅም።

Beimnet
Beimnet
Open In TikTok:
Region: ET
Tuesday 25 August 2026 10:26:46 GMT
1026
55
1
2

Music

Download

Comments

ada230575
ada :
ነገም ስለ አማራ የማወራው ንፁህ ታሪክ አለኝ🙏ተመስገን አምላኬ
2026-08-25 17:03:56
0
To see more videos from user @beimnet19, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About