@emuwolloye: ዶክተር ገዱ አንዳርጋቸው!!! አትዘባበቱ ቀን ጣለው ብላችሁ፤ ከፊታችሁ ቀድሞ ታገኙታላችሁ። ምናልባት አገር ወዳድ መሳይ ጭምብለኞች ለስላሳ ቆዳቸውን ይዘው ጠጋ ጠጋ በማለት በስሙ ሸቅጠውበት ካልሆነ በቀር (ይህንንም ቢሆን እሱ ሳያውቅ) ሰርቆና ዘርፎ ያቆመው ሃውልት እንኳን የለውም። እነዚህ ጭምብለኞች በሴራቸው ቀመር ምናልባት ሃቀኛ የትግል ጓዶቹን ጀርባ እንዲሰጣቸው በማድረግ ጭምር አሳስተውት ካልሆነ በቀር አሁንም ከሌብነት መንደር የለበትም። በያኔው በወሎ ክፍለ ሃገር በዋድላ እና ደላንታ አውራጃ በደላንታ ሃይስኩል ስመጥር ጀግና የቀለም ቀንድ ከሚባሉት ጥቂት ተማሪዎች መሀከል ግንባር ቀደም የነበረው ገዱ አንዳርጋቸው ፖለቲካ የሚባል ጅኒ ባይለክፈው ኖሮ ዛሬ በአውሮፓና አሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች ዘንድ በሊቃውንቱ መንበር ላይ ሲገማሸር ታገኘው ነበር። እኛ የወልዲያ ሃይስኩል ተማሪዎች ሳለን በየጁ ውድመን ተራሮች ወዲያንዲያ ከደላንታ ምድር ዘንድ የጀግኖች ተማሪ ስም ዝርዝር ሲነገረን የገዱ አንዳርጋቸው ስም ከፊት ነበር የሚፃፈው። ገዱ በ1980ዎቹ ወደ ፖለቲካው አለም ሲቀላቀል ያልተቆጨ ሰው አልነበረም። በተለይ ያስተማሩት መምህሮቹ የገዱን የትምህርት ብቃት ደጋግመው በማንሳት የአካዳሚክ መስመሩን ትቶ ወደ ፖለቲካው አለም በመግባቱ ደስ አልተሰኙም ነበር። መቼስ የፖለቲካ ልክፍቱ እንደ ቆላ ዛር በቀላሉ አይለቅምና ገዱ ጭልጥ ብሎ ወደፖለቲካው ገባ እንጅ በጀመረው የጀግና ተማሪነቱ መንገድ ቀጥሎበት ቢሆን ኖሮ ቢያንስ ዛሬ ካገኘነው ስፍራ አናገኘውም ነበር። ገዱ ስለያዘው የፖለቲካ አቋም ሰዎች የፈለገ አስተያየት ቢሰጡ አያገባኝም። ገዱ አንዳርጋቸውን ግን አቅም፤ እውቀትና ችሎታ እንደሌለው አድርገው ሊሞላፈጡና redicule ለማድረግ ለሚከጅሉ ጅላንፎች ግን ዝም ማለት የተራራ ያህል ይከብደኛል። ለማናቸውም ፖለቲካ የሚሉት እከክ ባልተገባ ጊዜ ያልተገባ ቦታ ላይ እንዲገኝ ቢያደርገውም እመነኝ አቧራውን አራግፎ ከፊትህ ቆሞ ታገኘዋለህ። Mark my words!
ቤተ አማራ
Region: AE
Tuesday 25 August 2026 13:01:28 GMT
Music
Download
Comments
Tag_life :
🔥🔥🔥
2026-08-25 13:15:50
0
አርጎባዋ🧕🇪🇹 :
🥰🥰🥰
2026-08-25 18:49:55
0
To see more videos from user @emuwolloye, please go to the Tikwm
homepage.