@cortessatisfatorios4: #asmr #satisfatório #asmrsounds #nostalgia #asmr

Cortes satisfatórios
Cortes satisfatórios
Open In TikTok:
Region: BR
Tuesday 25 August 2026 20:32:43 GMT
17653
475
3
27

Music

Download

Comments

andyshongo331
Andy 👑 king's :
elle est trop nostalgique cette chanson
2026-08-25 22:44:36
0
y_yash1
YASH :
2026-08-25 22:56:08
0
dvibe1702
D.Vibe :
👏👏👏
2026-08-25 20:36:14
0
To see more videos from user @cortessatisfatorios4, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


"በዝሙት እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ፣ ( ይነበብ) 🎋🥀 "ለብዙ ወጣቶች ትምህርት ስለሚሆን አንብቡትና አዛምቱት ሁሉ በአግባቡና በሥርዓት ይሁን #በዚህ_ጊዜ በወንዶችና በሴቶች አደገኛ ፈተና የሆነው ዝሙት ነው። የሰው ልጅ ማለት ሴቷ ወንድ ልጅ የምትፈልግበት ወንዱም ሴት ልጅ የሚፈልግበት የተፈጥሮ ስጦታ አለው። "ነገር ግን ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን" ( 1ኛ ቆሮ 14:40) እንዳለው ቅዱስ ጳውሎስ ማንኛው ሰው ተፈጥራዊ ስሜት ይኑረው እንጂ እንደ እንስሳ ሳይሆን በስርዓት መሄድ ይኖርበታል። እንደ አንበሳና ርግብ ያሉ እንስሳትን እንኳን ብንመለከት ከሕይወት አጋራቸው ውጭ አይሄዱም። እንግዲህ ከእነዚህ እኛ ለምን እናንሳለን??? ነጻነት ሥላለን ከሥርዓት አንውጣ "አንድ ሰው በሕይወቱ ራሱ ኃላፊነት ካልወሰደ በስተቀር ማንም ኃላፊነት ሊወስድለት አይችልም። እግዚአብሔር የሚገዛን በነጻነት እንጂ በአምባገነንነት አይደለምና። ነጻነት ስላለን ከሥርዓት አንውጣ። የሰው ገላ እንደ ፋሽን መቀያየር አይገባም "ወንዱም ይሁን ሴቷ የእግዚአብሔርን ሕግ ከማስቀደም ይልቅ ፋሽን እየተባለ ወንዱ በየቀኑ ሴቶችን እንደ ልብስ እየቀያየረ፣ ሴቷም በየቀኑ ወንዶች እንደ ልብስ እየቀያየረች ወደ ሞት ይነዳሉ። ይህ የዝሙት መንፈስ የተጠናወተበት ሰው በስጋው ይሁን በነፍሱ የረከሰና የዲያቢሎስ መኖርያ ይሆናል። ሰው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነው "አላስተዋልንም እንጂ አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ በዋጋ የገዛን በመሆናችን በራሳችን ላይ ከእግዚአብሔር ሕግና ሥርዓት ውጭ የማድረግ ስልጣን የለንም። ሰለዚህ እኛ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን(1ቆሮ 3:16)። "ታድያ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ናችሁ ከተባልን የእግዚአብሔር መንፈስ መኖሪያ እንሆን ዘንድ ከዝሙት መራቅ አለብን። አለበለዚያ ንስሐ ሳንገባ በዝሙት ተጠምደን የምንኖር ከሆንን ግን ነፍሳችን ከእግዚአብሔር ፀጋ ተራቁታ ወደ ሲኦል ትገባለች። "ዝሙት የነፍስና የሥጋ በሽታ ነው ዝሙት የነፍስና የስጋ በሽታ መሆኑን የአምላክ ቃል እንዲህ ብሎ ያስተምረናል፦ ☞ " ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ " ( 1ኛ ቆሮ 3:17) ። ስለዝሙት የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃዎች እስኪ ከመፅሓፍ ቅዱስ ስለ ዝሙት ምን እንደሚል አብረን እንመልከት፦ " እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ያለ ዝሙት ምክንያት ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ አመንዝራ ያደርጋታል፥ የተፈታችውንም የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል ማቴ 5፥32)። " ከልብ ክፉ አሳብ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት መመስከር፥ ስድብ ይወጣልና" ማቴ 15:19)። " ለጣዖት ከተሠዋ፥ ከደምም፥ ከታነቀም፥ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና፤ ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ። ጤና ይስጣችሁ " ሐዋ.ሥራ 15:28-29)። " በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን ሮሜ 13:13)። " በአጭር ቃል በእናንተ መካከል ዝሙት እንዳለ ይወራል የዚያም ዓይነት ዝሙት በአሕዛብስ እንኳ የማይገኝ ነው፥ የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው ይኖራልና 1ኛ ቆሮ 5:1)። " መብል ለሆድ ነው፥ ሆድም ለመብል ነው፤ እግዚአብሔር ግን ይህንም ያንም ያጠፋቸዋል። ሥጋ ግን ለጌታ ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም፤ ጌታም ለሥጋ ነው " ( 1ኛ ቆሮ 6:13)። " ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚያደርገው ኃጢአት ሁሉ ከሥጋ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚሠራ ግን በገዛ ሥጋው ላይ ኃጢአትን ይሠራል" 1ኛ ቆሮ 6:18)። የሚል እናገኛለን። ታድያ ምን እናድርግ? እስከ ሞት ድረስ መታመን " እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ " ( ራእ.ዮሐ 2:10)። ይህ የሕይወት አክሊል የሚገኘው ደግሞ "በጸሎት፣ "በፊቱ በመሆን "ፈቃዱን መጠይቅ ቅዱስ አምላካችን በማቴ 6:33። ላይ " ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል፣ ስለዚህ እህቴ ሆይ ከላይ በማቴ 6:33 የተጻፈውን ስትፈፅሚ አምላካችን ሌላው ይጨመርላችኋል እንዳለን (ከዝሙት ለመራቅ፣) "ወንድሜ ሆይ ከላይ በማቴ 6:33 ላይ የተጻፈውን ስተፈፅም አምላካችን ሌላው ይጨመርላችኋል እንዳለን ከዝሙት እንድትርቅ፣ የምትረዳህና ዘር ለመተካት በአጠቃላይ ለትዳር የምትሆንህ ሴት ልጅ ላንተ ይሰጠሃል። "እግዚአብሔር እውነተኛ ፍቅር ሰጥቶ ለዚህ ክብር ያብቃን፣ አሜን "በሥርዓት ለመኖር አምላካችን ይርዳን፣☘️🎋

About