@ahimeed.mehameed: እስካሁን የሟቾች ቁጥር 165 የጠፉ 800 አልፏል‼ በኔፓል እና ቻይና (ቲቤት) ወሰን አካባቢ በደረሰ ከፍተኛ የመሬት መንሸራተት እና ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር 165 የደረሰ ሲሆን፣ ከ1,300 በላይ ሰዎች ደግሞ የገቡበት አልታወቀም። 📌 በኔፓል እስካሁን 165 አስከሬኖች የተገኙ ሲሆን፣ ከ800 በላይ ሰዎች ደግሞ ጠፍተዋል። በቲቤት በኩል ደግሞ የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተረጋገጦ ከ558 በላይ ሰዎች መጥፋታቸው ተገልጿል። 📌 በሁለቱም ወገን ከቪየትንና፣ ሕንድ (ከ100 በላይ)፣ አሜሪካ (54)፣ ብሪታንያ (33)፣ ማሌዢያ እና ደቡብ አፍሪካ የመጡ በርካታ ቱሪስቶችና ተጓዦች በጠፉት ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ይገኛሉ። 📌በሬክተር ስኬል 4.4 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥን ተከተሎ የመጣ የበረዶ ግግር መደርመቅ (Glacial collapse) እና የድንጋይ ናዳ ድንገተኛ የውኃና የአፈር ጎርፍ ማስከተሉ ተገልጿል። 📌ጎርፉ በመንገዱ ያገኛቸውን መንደሮች፣ 19 ድልድዮችን፣ 40 ኪሎ ሜትር መንገድን፣ 13 የሃይድሮ ፓወር ፕሮጀክቶችን እና 200 የጭነት መኪኖችን ሙሉ በሙሉ ጠራርጎ ወስዷል። በአካባቢው ባለው አስቸጋሪ መሬታማ አቀማመጥ እና ዝናብ ምክንያት የመታደግ ስራው መወሳሰቡ ተገጿል። #WasuMohammed 👇እዚህ ድምፅ ይስጡ👇 https://yekinlibochaward.org/nominees/wasu-mohammed ==================== ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
Ahimeed m\d🇹🇷🇹🇷🇹🇷
Region: ET
Thursday 27 August 2026 08:21:33 GMT
Music
Download
Comments
Legese✝️🛐🇪🇹🇪🇹🥇 :
😁😁😁
2026-08-27 11:15:23
0
To see more videos from user @ahimeed.mehameed, please go to the Tikwm
homepage.