@daer033: "አደፍርስ" ከዛሬ 56 ዓመት በፊት በሐበሻ የዘመን ቀመር 1962 ዓ.ም እስከዛሬ ድረስ የስነ ጽሑፍ ምሁራን ችለው ሊፈቱት ያልቻሉት አንድ ልብ ወለድ ተወለደ። በሰዓቱ የመጽሐፉን የቋንቋ ክብደትና ጥልቀት መረዳት ያልቻለው አንባቢ ሁሉ መጽሐፉን ለማንበብ አቅም አጣ ብሎም ስለ መጽሐፉ አሉታዊ አስተያዬት ማራመድ ጀመረ። አብዛኞቻችን እንደዚህ ነን ከእኛ እሳቤ ጋር ያልሄደ ሁሉ ስህተት የሚመስለን። ይሄንን ጊዜ ነበር ደራሲው ዳኛቸው ወርቁ መጽሐፉን በውድ እየገዛ መሰብሰብ የጀመረው። "የእኔን መጽሐፍ አንብበው የሚረዱ ትውልዶች ገና አልተፈጠሩም።" በማለት እንደተናገረ በዘመኑ የነበሩ ሰዎች ይናገራሉ። ዳሩ ግን 56 ዓመታትም ተቆጥረው አሁንም ከፊሉን እንጅ ሙሉውን ለመረዳት አዳጋች ሆኗል። “አደፍርስ” ልክ እንደ ስሙ የሰከነውን አእምሮ የሚረብሽ፣ በቃላት ሥዕል የሚሥልና የኢትዮጵያን ማኅበራዊ ሽግግር በረቂቅ ብዕር የከተበ የጥበብ ሥራ ነው። አንድ አደፍርስ የተባለ ንቃተ ህሌናው የተገለጠለት የዩኒቨርስቲው ወጣት ወደ ማህበረሰቡ ገብቶ በባህልና በሐይማኖት ተሸሽጎ ስልጣኔን የሸሸውን ማህበረሰብ ሲያደፈርስ እናያለን። ታዲያ ግን አደፍርስ የዋዛ ሰው አይደለም..."ባህልህን ሳትጥል ሐይማኖትህን ሳትተው ከስልጣኔ ተቀላቀል" ብሎ የሚነግረውን የይፋት ፣የጥሙጋ፣ የጣርማ በር ፣የደብረሲና በአጠቃላይ የሸዋ ሰው በላቀ የአምሮ ብስለት እንጅ እንደ አንዳንድ የፍልስፍና ሰዎች በደፈናው አይደለም። መጽሐፉ ለአንባቢ መልስ አይሰጥም ለመረዳት ከሚከብዱት የቃላት አጠቃቀሞች ጀምሮ እስከ ፍልስፍናዊ እሳቤው ድረስ እኛ አንብበን ከተፃፈው ጀርባ ያልተፃፈውን ነገር እንድንፈልግ በጥያቄ ይሞላናል። በመጽሐፉ ውስጥ ባህል ሐይማኖት፣ ፍልስፍና ፣ስነ ልቦና ፣ፖለቲካ፣ፍቅርና ሌሎችም እንድንመረምራቸው የተተው የደራሲው ድብቅ ሚስጥሮች ናቸው። ባለችኝ ሚጢጢዬ እውቀት መጽሐፉን ደጋግሜ አንብቤ ይህችን እንደ መግቢያ ፃፍኩላችሁ። ሌላውን ለእናንተ ትቻለሁ! መልካም ንባብ! @fb:የጥንት መጽሐፎች ገዢ ✍️ #booklover #ethiopian_tik_tok💚💛❤️

daer33
daer33
Open In TikTok:
Region: ET
Thursday 27 August 2026 18:29:28 GMT
9053
503
6
170

Music

Download

Comments

wendi.tegegn
Wendi Tegegn :
ግማሹን ለማንበብ 2ወር ነው የፈጀብኝ ቋንቋው ከብዶኝ ተውኩት
2026-08-28 03:21:43
4
abiy1486
Abiysolome :
so nice denene telahun
2026-08-30 12:34:48
2
maramawit.mifta
maramawit mifta :
My fvrt book
2026-09-09 01:18:13
0
kasu9317
kasu ሆፓ :
ትችላለህ ብሮ🥰
2026-09-04 20:23:48
0
uma.tessema
Uma Tessema :
"ቁንዲ አንገቷን አስግጋ....?? 😍❤
2026-09-14 15:03:27
0
teda.love94
teda love :
😳
2026-09-12 15:53:09
0
To see more videos from user @daer033, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About