@kosblingdiy2:

kosblingdiy2
kosblingdiy2
Open In TikTok:
Region: US
Friday 28 August 2026 05:47:27 GMT
5576
137
3
10

Music

Download

Comments

alexiaevk
Lhexx25 :
One of my chase. Want him ❤️❤️❤️
2026-08-29 21:41:03
2
wissey_s
Joice_s :
how can I order??
2026-08-30 02:56:44
0
beautybeautiful7705
CraftyFancyItems :
When the glue gets hard how can I make it softer ? I would hate to throw good glue to be wasted.
2026-09-07 06:15:01
1
To see more videos from user @kosblingdiy2, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

በሕይወታችን የምናጣውን ነገር ለመቁጠር በጣም ፈጣኖች ነን። የሌለንን እናስባለን። የሌላውን እናያለን። ያልደረስንበትን እንመኛለን። ያልተሟላልንን እንቆጥራለን። አንዱ ገንዘብ ይፈልጋል። ሌላው ቤት ይፈልጋል። አንዱ መኪና ይፈልጋል። ሌላው ፍቅር ይፈልጋል። ሌላው ደግሞ የሌላውን ሕይወት ለመኖር ይመኛል። በዚህ ሁሉ ፍለጋ ውስጥ ግን በእጃችን ያለውን ሕይወት መመልከት እንረሳለን። ስለዚህ አንድ ቀን ሕይወታችሁን ከልብ ማመስገን ከፈለጋችሁ፣ ሦስት ቦታዎችን ጎብኙ። 1. ሆስፒታልን ጎብኙ ሆስፒታል ውስጥ ስትገቡ በጤና ያለውን ሰው ዋጋ ትረዳላችሁ። ዛሬ በነፃነት እየተነሳችሁ ነው። እየተራመዳችሁ ነው። እየተናገራችሁ ነው። እየተመለከታችሁ ነው። እየተመገባችሁ ነው። እየጠጣችሁ ነው። እየሰራችሁ ነው። እየሳቃችሁ ነው። እየተነፈሳችሁ ነው። እነዚህ ሁሉ ቀላል ነገሮች እንደሆኑ እናስባለን። ግን በሆስፒታል አልጋ ላይ ላለ ሰው አንድ እርምጃ መራመድ ሕልም ሊሆን ይችላል። አንድ ቃል መናገር ምኞት ሊሆን ይችላል። የሚወደውን ሰው በአይኑ ማየት ትልቅ ስጦታ ሊሆን ይችላል። በራሱ እግር መቆም የማይችል ሰው የእኛን ተራ መራመድ ሊመኝ ይችላል። እኛ ግን ጫማችን የተለየ ቀለም ስለሌለው እንከፋለን። ስለዚህ ሆስፒታልን አንድ ጊዜ ጎብኙ። ከዚያ ስትወጡ ምናልባት የምንለው አንድ ቃል ብቻ ይሆናል፦ “ተመስገን!” 2.  እስር ቤትን ጎብኙ እስር ቤት የሰው ነፃነት ምን ያህል ትልቅ ሀብት እንደሆነ ያስተምራል። ዛሬ በፈለጋችሁበት ቦታ መሄድ ትችላላችሁ። በፈለጋችሁት ሰዓት በር መክፈት ትችላላችሁ። የምትወዱትን ሰው መጠየቅ ትችላላችሁ። ወደ ገበያ መውጣት ትችላላችሁ። ወደ ሥራ መሄድ ትችላላችሁ። ቤታችሁን በራሳችሁ ፈቃድ መውጣትና መመለስ ትችላላችሁ። ይህ ነፃነት ነው። ግን ነፃ ሆነን ስንኖር ዋጋውን አንረዳውም። እስር ቤት ውስጥ ያለ ሰው ግን የእኛን  በነጻነት መውጣት መግባት  እንደ ትልቅ ሀብት ያየዋል። እኛ  “ዛሬ ቤት መቀመጥ ሰለቸኝ” የምንለው ነገር፣ ለሌላ ሰው የማይገኝ ነፃነት ሊሆን ይችላል። ስለዚህ የምትችሉትን ሁሉ ማድረግ መቻላችሁን አትናቁ። ነፃነት ራሱ ሀብት ነው። 3.  የመቃብር ስፍራን ጎብኙ ይህ ሦስተኛው ቦታ ከሁሉም የበለጠ ዝምተኛ ነው። በዚያ የትላንት ሕልሞች ተኝተዋል። የትላንት ሀብታሞች አሉ። የትላንት ድሆች አሉ። የትላንት ቆንጆዎች አሉ። የትላንት ታዋቂዎች አሉ። የትላንት ትልልቅ ስልጣን የነበራቸው አሉ። ግን ዛሬ ሁሉም ዝም ብለዋል። ትላንት “ቤቴ” ያለው ሰው ዛሬ በጥቂት ካሬ መሬት ውስጥ ነው። ትላንት “ገንዘቤ” ያለው ሰው ዛሬ አንድ ሳንቲም አይይዝም። ትላንት “ጊዜ የለኝም” ያለው ሰው ዛሬ ጊዜ አይፈልግም። ይህ ማለት ገንዘብ አይጠቅምም ማለት አይደለም። ቤት፣ መኪና፣ ሥራ፣ ሀብትና ስኬት አያስፈልጉም ማለትም አይደለም። ነገር ግን እነዚህ ነገሮች በራሳቸው  ሕይወት  አይደሉም። ለእኛ ሕይወት እየተነፈሱ መኖር ነው። የሚወዱን የምንወዳቸው  ሰዎች ከጎናችን  መኖራቸው ነው። ጤና ነው። ነፃነት ነው። ሰላም ነው። አንድ ቀን በሌላ ቀን ላይ መጨመር መቻል ነው። ስለዚህ ዛሬ ገንዘብ ከሌላችሁ፣ ሕይወት የሌላችሁ አይምሰላችሁ። ቤት ከሌላችሁ፣ ዓለም የተዘጋችባችሁ አትሰማችሁ። መኪና ከሌላችሁ፣ ሕይወት ከእናንተ የራቀች አትምሰላችሁ ። ዛሬ በጤና ካላችሁ፣ እየተነፈሳችሁ ካላችሁ፣ እየተራመዳችሁ ካላችሁ፣ እያያችሁ ካላችሁ፣ እየሰማችሁ ካላችሁ፣ እየተናገራችሁ ካላችሁ፣ የምትወዷቸው ሰዎች አጠገባችሁ ካሏችሁ፤ እናንተ ዛሬ ብዙ ሀብት ያላችሁ ሰዎች ናችሁ።  እናም
በሕይወታችን የምናጣውን ነገር ለመቁጠር በጣም ፈጣኖች ነን። የሌለንን እናስባለን። የሌላውን እናያለን። ያልደረስንበትን እንመኛለን። ያልተሟላልንን እንቆጥራለን። አንዱ ገንዘብ ይፈልጋል። ሌላው ቤት ይፈልጋል። አንዱ መኪና ይፈልጋል። ሌላው ፍቅር ይፈልጋል። ሌላው ደግሞ የሌላውን ሕይወት ለመኖር ይመኛል። በዚህ ሁሉ ፍለጋ ውስጥ ግን በእጃችን ያለውን ሕይወት መመልከት እንረሳለን። ስለዚህ አንድ ቀን ሕይወታችሁን ከልብ ማመስገን ከፈለጋችሁ፣ ሦስት ቦታዎችን ጎብኙ። 1. ሆስፒታልን ጎብኙ ሆስፒታል ውስጥ ስትገቡ በጤና ያለውን ሰው ዋጋ ትረዳላችሁ። ዛሬ በነፃነት እየተነሳችሁ ነው። እየተራመዳችሁ ነው። እየተናገራችሁ ነው። እየተመለከታችሁ ነው። እየተመገባችሁ ነው። እየጠጣችሁ ነው። እየሰራችሁ ነው። እየሳቃችሁ ነው። እየተነፈሳችሁ ነው። እነዚህ ሁሉ ቀላል ነገሮች እንደሆኑ እናስባለን። ግን በሆስፒታል አልጋ ላይ ላለ ሰው አንድ እርምጃ መራመድ ሕልም ሊሆን ይችላል። አንድ ቃል መናገር ምኞት ሊሆን ይችላል። የሚወደውን ሰው በአይኑ ማየት ትልቅ ስጦታ ሊሆን ይችላል። በራሱ እግር መቆም የማይችል ሰው የእኛን ተራ መራመድ ሊመኝ ይችላል። እኛ ግን ጫማችን የተለየ ቀለም ስለሌለው እንከፋለን። ስለዚህ ሆስፒታልን አንድ ጊዜ ጎብኙ። ከዚያ ስትወጡ ምናልባት የምንለው አንድ ቃል ብቻ ይሆናል፦ “ተመስገን!” 2. እስር ቤትን ጎብኙ እስር ቤት የሰው ነፃነት ምን ያህል ትልቅ ሀብት እንደሆነ ያስተምራል። ዛሬ በፈለጋችሁበት ቦታ መሄድ ትችላላችሁ። በፈለጋችሁት ሰዓት በር መክፈት ትችላላችሁ። የምትወዱትን ሰው መጠየቅ ትችላላችሁ። ወደ ገበያ መውጣት ትችላላችሁ። ወደ ሥራ መሄድ ትችላላችሁ። ቤታችሁን በራሳችሁ ፈቃድ መውጣትና መመለስ ትችላላችሁ። ይህ ነፃነት ነው። ግን ነፃ ሆነን ስንኖር ዋጋውን አንረዳውም። እስር ቤት ውስጥ ያለ ሰው ግን የእኛን በነጻነት መውጣት መግባት እንደ ትልቅ ሀብት ያየዋል። እኛ “ዛሬ ቤት መቀመጥ ሰለቸኝ” የምንለው ነገር፣ ለሌላ ሰው የማይገኝ ነፃነት ሊሆን ይችላል። ስለዚህ የምትችሉትን ሁሉ ማድረግ መቻላችሁን አትናቁ። ነፃነት ራሱ ሀብት ነው። 3. የመቃብር ስፍራን ጎብኙ ይህ ሦስተኛው ቦታ ከሁሉም የበለጠ ዝምተኛ ነው። በዚያ የትላንት ሕልሞች ተኝተዋል። የትላንት ሀብታሞች አሉ። የትላንት ድሆች አሉ። የትላንት ቆንጆዎች አሉ። የትላንት ታዋቂዎች አሉ። የትላንት ትልልቅ ስልጣን የነበራቸው አሉ። ግን ዛሬ ሁሉም ዝም ብለዋል። ትላንት “ቤቴ” ያለው ሰው ዛሬ በጥቂት ካሬ መሬት ውስጥ ነው። ትላንት “ገንዘቤ” ያለው ሰው ዛሬ አንድ ሳንቲም አይይዝም። ትላንት “ጊዜ የለኝም” ያለው ሰው ዛሬ ጊዜ አይፈልግም። ይህ ማለት ገንዘብ አይጠቅምም ማለት አይደለም። ቤት፣ መኪና፣ ሥራ፣ ሀብትና ስኬት አያስፈልጉም ማለትም አይደለም። ነገር ግን እነዚህ ነገሮች በራሳቸው ሕይወት አይደሉም። ለእኛ ሕይወት እየተነፈሱ መኖር ነው። የሚወዱን የምንወዳቸው ሰዎች ከጎናችን መኖራቸው ነው። ጤና ነው። ነፃነት ነው። ሰላም ነው። አንድ ቀን በሌላ ቀን ላይ መጨመር መቻል ነው። ስለዚህ ዛሬ ገንዘብ ከሌላችሁ፣ ሕይወት የሌላችሁ አይምሰላችሁ። ቤት ከሌላችሁ፣ ዓለም የተዘጋችባችሁ አትሰማችሁ። መኪና ከሌላችሁ፣ ሕይወት ከእናንተ የራቀች አትምሰላችሁ ። ዛሬ በጤና ካላችሁ፣ እየተነፈሳችሁ ካላችሁ፣ እየተራመዳችሁ ካላችሁ፣ እያያችሁ ካላችሁ፣ እየሰማችሁ ካላችሁ፣ እየተናገራችሁ ካላችሁ፣ የምትወዷቸው ሰዎች አጠገባችሁ ካሏችሁ፤ እናንተ ዛሬ ብዙ ሀብት ያላችሁ ሰዎች ናችሁ። እናም "ተመስገን" በሉ። እኛ ግን ይህንን ሀብት በየቀኑ እንጠቀማለን፤ ስለዚህም ዋጋውን እንረሳዋለን። የምንተነፍሰውን አየር ዋጋ የምንረዳው ሲያጥረን ነው። የእግራችንን ዋጋ የምንረዳው መራመድ ሲያቅተን ነው። የአይናችንን ዋጋ የምንረዳው ብርሃን ሲጠፋብን ነው። የነፃነታችንን ዋጋ የምንረዳው በሩ ሲዘጋብን ነው። የሕይወታችንን ዋጋ ደግሞ ብዙ ጊዜ የምንረዳው ሕይወት ሲያበቃ ነው። እና ነገሮችን ከማጣታችን በፊት ዋጋቸውን እንወቅ። ዛሬ የሌለን ነገ ሊኖረን ይችላል፤ ላይኖረንም ይችላል። ስለዚህ ዛሬን አትናቁ። በተደጋጋሚ እንደምለው... ዛሬ እናት ከጎናችሁ ካለች፣ አመስግኗት። አባት ካለ፣ አክብሩት። ወንድምና እህት ካሉ፣ ዋጋቸውን እወቁ። ጓደኛ ካለ፣ አትናቁት። የምትወዱት ሰው ከጎናችሁ ካለ፣ የዛሬውን ፍቅር ለነገ አታስቀምጡት። ምክንያቱም ሕይወት “ነገ” ብሎ የተፈረመ ውል የለውም። የምንይዘው ዛሬን ነው። የምንኖረው ዛሬን ነው። የምናመሰግነውም ዛሬን መሆን አለበት። ስለዚህ ሕይወት እንደጎደለችን ከመቁጠራችን በፊት፣ እጃችን ያለውን እንቁጠር። የሌለንን ከመመኘታችን በፊት፣ ያለንን እንይ። የሌላውን ሕይወት ከመመልከታችን በፊት፣ የራሳችንን ሕይወት እንደገና እንመልከት። ምናልባት እኛ እንደ ችግር የምንቆጥረው ሕይወት፣ ሌላ ሰው በምኞት የሚጠብቀው ሕይወት ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ዛሬ ትንሽ ቆም ብለን ወደ ራሳችን እንመለስ። “ምንም የለኝም?” ከማለታችን በፊት፣ “ምን አለኝ?” ብለን እንጠይቅ። ከዚያም የልባችንን እጅ ወደ ላይ አንስተን፣ በጸጥታ አንድ ቃል እንበል... “እጅግ ብዙ አለኝ። ተመስገን!” ይህ የእኔ እይታ ነው ✍️ ለወዳጆቻችሁ ሼር እና Repost አድርጉላቸው🙏 ቀጣይ ሌሎች እይታዎች እንዲደርስዎት የእኔ እይታን ፔጅ Follow, Like እና Copy Link በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ! #foryou #fyp #viral #fypシ #viralvideo

About