@ab_quonte: ጠንካራ መስያት ነው ። የምታየው ብቻ መስያት ነው ። ለሷ ያለኝ ቦታ ያሳየኋት እና የነገርኳት ብቻ መስሏት ነው። ሌላም ሰው እኔ ያልኳትን ብሏት ዋሽቷት ስላገኘችው፤ ቃልም፣ ተግባርም ማመን አቁማ ነው ። ስታገኘኝ 'Dead inside' የሚል ፅሁፍ ያለበት ቲሸርት መልበሴን አላስታወሰችውም ።ሳቄ የቲሸርቴን መልዕክት ከልሎት ነበር ። የማያቁኝ፣ ያልሰሙኝ የሰጡአት አስተያየት ልቧን ተጭኖት ነው ። የተሰበረ ሁሉ የሚጠገን መስሏት ነው ። ጊዜ ሁሌ አዳኝ መስሏት ነው ። ከልጅነቴ ጀምሮ የሚራራልኝ አልነበረም!! ልጅ እያለሁ:- አባቴ ይወደኝ ነበር ። አንድ ነገር ሳይዝልኝ ቤት አይገባም ፣ ሳያጫውተኝ አይተኛም። መንገድ ስንሄድ እሽኮኮ ያደርገኝ ነበር ። ላገኘው ሁሉ "ልጄ ነው" ይል ነበር። ዘና ያለ ነው ፣ ሙዚቃ ይወዳል፣ ተጫዋችም፣ ዝምተኛም ፣ ሳቂታም፣ ኮስታራም ነበር ። ከእናቴ ጋር ብዙ ግዜ ቢጨቃጨቁም ፤ ሁለቱም ይወዱኝ ነበር ። ፍቅር አሰጣጣቸው ለየቅል ነው ። ሰው ለሚወደው የሚሰጠው የሚችለውን ሁሉ ነው ። የሆነ ቀን ፀባቸው ከሮ ፍርድቤት ቆሙ ። ይዘውኝ ሄዱ። የሚያወሩት ስለ መለያየት፣ ስለተቆራጭ ምናምን ነበር። አይን አይኔን እያየ "አላምናትም፤ ይሄ ልጅ ራሱ የኔ አይደለም" አለ ። አላመንኩም : ውሸቴን ነው ይላል ብዬ ጠበኩት ህይወት እንደዚ አይነት ቀልድ እንደማታውቅ አላቅም ነበር ። ልጄ አይደለም ካለኝ በኋላ የተወራውን መስማት አልተቻለኝም ። "ይሄ ልጅ ራሱ የኔ አይደለም " ያለው ፊቱ ፣ ሁኔታው ድምፁ ፤ እርግጠኝነቱ ከልቤ አልጠፋ አለ። እናቴ እጄን ይዛ ወደ ቤት ተመለስን ። አደባባይ ላይ "ልጄ አይደለም" ያለኝ ከሰጠኝ ፍቅር ሁላ ስለበለጠብኝ ውስጤ ደነገጠብኝ ። የሚታይ ነው የሚሰማ መታመን ያለበት ?? ለምን ይዘውኝ ሄዱ ? ፣ እማኝ ባለበት ስካድ ማየት እኔን ከማበላሸት ውጪ ምን ይጠቅማል ?? ያን ቀን አባት አልባ ሆኜ ተመለስኩ ። ዘግኖ ባዶ ማግኘት ህይወት ውስጥ አዲስ አይደለም !! © Adhanom Mitiku። #ፍቅር➻ብቻ🖇ፍቅር➻ብቻ❤🥀🔐 #ፍቅር➻ብቻ🖇ፍቅር➻ብቻ❤🥀🔐🦋👑 #ፍቅር #እህቴ_የኔ_ንግስት #ዱባዮች🇦🇪🙏 @سترة🧕 @ኢስማኢል
Abd_Pogba 6🔥
Region: AE
Friday 28 August 2026 10:40:12 GMT
Music
Download
Comments
miki miki :
🥰🥰🥰
2026-08-28 14:57:32
0
Medi 🧕🏻🦋 :
🥰🤝
2026-08-28 12:03:52
0
@_ዩስሪ,,,fiker,,,🍫 :
🥰🥰🥰
2026-08-28 11:00:12
0
Call me qalø :
🤝🥰
2026-08-28 10:59:28
0
Azu :
🥰🥰👌
2026-08-28 15:40:27
0
To see more videos from user @ab_quonte, please go to the Tikwm
homepage.