@mane.shopping: ቅጥቅጥ አደረኳት። አልቅሳ ሲደክማት እንቅልፍ ወሰዳት። እሷ ስትተኛ እኔ ተተካሁ። ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ። አብሮ አደጌ የልብ ጓደኛዬ ስትሞሸር መገኘት እንዳልችል ያደረገኝ ያብስራ ነው። እናቴ አጋጣሚ እየጠበቀች ምትወቅሰኝ በሱ ምክንያት ብዬ አሰብኩ ውስጤ የሚሰማኝ የጥላቻ ነደደ ይሄ ነው የሚባል አደለም። አቤል ሰርጉ ላይ ሄዷል። ከሀይሌ ልብስና ጫማ ተበድሮ በሙሽራው ልብስና ጫማ ሰርጉን ለመታደም ሄዶ ነበር። ምሽቱን ማልቀስ ማቆም አልቻልኩም። እራሴን ለማረጋጋት ብሞክርም አቃተኝ እቴቴ መጥታ ከአንዴም ሁለቴ በር ብታንኳኳም እንደተኛ ሰው ዝም አልኳት። ማታ እየመሸ ሲሄድ ህላዌ ከእንቅልፏ ነቅታ እማማጋ እንሂድ አለችኝ። እረፊ ብዬ ተቆጣኋት። አጠገቧ ተቀምጬ እላዬ ላይ ወጥታ እያቀፈችኝ እንባዬን ጥርግ እያደረገች ሳም ሳም ታደርገኝ ጀመር። መልሼ አቅፌ ሳምኳት። መልሳ አሳዘነችኝ እሷ ምን በወጣት እሷ ምን ባጠፋች ልገላምጣት ልቆጣት። ማታ አንድ ሰአት አካባቢ ላይ ለእናቴ ደወልኩ አታነሳም። ለሜሪ እንዳልደውል ጨነቀኝ። እቴቴጋ ሄድኩ አቤል ቆየኮ አልኳት። አዎ ቆየ ግን ሰርግ አደለ እንዴት ቶሎ ይመለሳል አለችኝ። ትንሽ እሷጋ ቁጭ አልኩና አባትየው ሳይመጣ ተነስቼ ወደቤቴ ሄድኩ። ቤት መግባት ስላልፈለኩ ህላዌን አቅፌ በሻርፔ ጥቅልል እንዳደረኳት ቁጭ ብዬ ሰማይ ሰማይ እያየን ሁለታችንም መሳሳቅ ጀመርን። እዛው ቁጭ ብለን ጎረቤቴ መጣ። ሲያየን ፈገግ ብሎ መቀላቀል ይቻላል አለ? ምኑ ላይ ነው ምትቀላቀለው አልኩት። አብሪያችሁ ልቀመጥ አለኝ። ዝም ብዬ አየሁት። ቁጭ አለ። ሞቅ ብሎት ነበር። እናትና ልጅ በቃ ፍቅራችሁ እያስቀናኝኮ ነው አባት አትፈልጉም ብሎ እራሱ ባወራው ቀልድ እራሱ ከት ብሎ ሳቀቀ ግራ ገብቶኝ አየሁት። በዛ መሀል ነው የእናቴ ስልክ ወደኔ ስልክ ሲጠራ ያየሁት። ተጣድፌ አነሳሁት የአቤል ድምፅ ከስልኩ ውስጥ ተሰማኝ። እየተርበተበተ ነበር ሄሎ ቅድስት እናትሽ እናትሽ ሀኪም ቤት ገብታለች አለኝ ከአጠገቡ የለቅሶ ድምፅና ጫጫታ እየተሰማኝ ነበር #እውነተኛ ታሪክ #ፅሁፍ #ስነፅሁፍ #fyp
mane shopping
Region: ET
Friday 28 August 2026 19:40:39 GMT
Music
Download
Comments
Boriifan🧕 :
Ba enkert lay joro dagef yelutal ehe nw😭kidest gen mechershawan lamawek guwgaw🥹
2026-08-28 19:48:21
8
zsh :
2026-08-29 04:14:00
0
painkiller :
ere and bemaryam
2026-08-28 19:50:34
0
Betsinat :
😳😳😳😳😳😳
2026-08-28 19:46:39
0
zsh :
😇😇😇😇😇😇😇😇😇😇😇😇😇
2026-08-29 04:14:13
0
To see more videos from user @mane.shopping, please go to the Tikwm
homepage.