@prosperityparty13: «የተቋማትየአመራሩና የባለሙያው የመፈጸም አቅም ለኢኮኖሚያዊ ብልጽግና ወሳኝ ነው» ርእሰመሥተዳድር አረጋ ከበደ የአማራ ክልል #ከፍተኛ እና #መካከለኛ አመራሮች የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲ እና የመንግስት ሥራዎች ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ እየተካሄደ ነው። መድረኩን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አቶ አረጋ ከበደ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ፈተናዎችን በጽናት በመሻገር በሁሉም ሴክተሮች አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግርዋል። ክልሉ የገጠሙትን ፈተናዎች ተሻግሮ በኢኮኖሚ እና በልዩ ልዩ የልማት መስኮች ተወዳዳሪ እንዲሆን በሁሉም ዘርፍ የተሻለ ውጤት መመዝገቡን የገለፁት ርእሰ መሥተዳድሩ በሰው ሃብት ልማት፣ በተቋም ግንባታ፣ በቴክኖሎጂ ልማት፣ ሠላምና ደኅንነትን በማረጋገጥ በኩል የተመዘገቡ ስኬቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም አስረድተዋል። ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ አክለውም የ25 ዓመት አሻጋሪ የልማት እና የ5 ዓመት ስትራቴጂካዊ ዕቅዶችን ለመተግበር የተደረገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ገልጸው የተቋማት፣ የአመራሩ እና የባለሙያው የመፈጸም አቅም ማደግ ለሕዝባችን ኢኮኖሚያዊ ብልጽግና ወሳኝ መሆኑንም አስረድተዋል። የጋራ ግንዛቤ ለጋራ ስኬት መሠረት ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ከታለመው ርዕይ ለመድረስ ተቋማት ተቀናጅተው መሥራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል። በመርሐ ግብሩ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይ የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲና የፖለቲካ ስራዎችን አፈጻጸም እና የቀጣይ ዕቅድ እያቀረቡ ሲሆን የክልሉ የ2019 በጀት ዓመት የፖለቲካ ስራዎች ዕቅድ እንዲሁም የአሻጋሪ ዕድገት እና ዘላቂ ልማት ዕቅድ ትውውቅ እንደሚደረግም የተያዘው መርሐ ግብር ያመላክታል።

prosperity party🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
prosperity party🇪🇹 🇪🇹🇪🇹
Open In TikTok:
Region: ET
Saturday 29 August 2026 08:34:20 GMT
12849
515
11
17

Music

Download

Comments

user62217475752903
ጊዜው ጆተኒ ነው። :
2026-08-29 10:50:27
1
geta.tegegne
love :
እውነት ነው ክቡርነትዎ!!
2026-08-29 09:58:40
1
user5435197278828
user5435197278828 :
?¿
2026-08-29 10:16:53
0
tekleslase.seife
Tekleslase Seife :
እውነት ነው
2026-08-29 17:55:02
0
user6600482355871
desu :
እውነት ነው ግን የአመራሩ አስተሳሰብና የባለሙየው አስተሳሰብ መመጣጠን/መናበብ አለበት። ማለትም ባለሙያው ከአመራሩ በልጦ እየተገኘ አመራሩ ሀሳብን ያለመቀበል አባዜ ይታያል
2026-08-29 17:59:21
0
mohammed.aragie5
Mohammed Aragie :
🥰🥰🥰
2026-08-29 10:20:11
1
tesfaye1774
Tesfaye :
🥰🥰🥰
2026-08-29 09:32:38
1
user999234709688
ልኑር በሱፍቃድ :
👌👌👌👌👌👌👌👌👌👌👌👌👌👌👌👌👌👌👌👌👌👌👌👌👌👌👌👌
2026-08-29 11:33:29
0
user8533287812755
ዋርካዉ :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-08-29 17:10:18
0
user522441440296
brsh :
😅😆😁
2026-08-29 20:56:05
0
seidmohammed53
s@❤❤ :
💪💪💪
2026-08-29 10:24:15
1
To see more videos from user @prosperityparty13, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About