@sarwitegetagiram: ‹‹ነሐሴ 24›› በዚህ ዕለት የአባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት የዕረፍታቸውን መታሰቢያ በዓል ነው። “ተክለሃይማኖት” ማለት ‹‹የሃይማኖት ተክል፣ ተክለ አብ፣ ተክለ ወልድ፣ ተክለ መንፈስ ቅዱስ›› ማለት ነው። አቡነ ተክለሃይማኖት በቡልጋ ደብረ ጽላሎሽ ከቅዱሳኑ አባታቸው ጸጋ ዘአብ እና እናታቸው እግዚእ ኃርያ ተወለዱ። የቤት ስማቸው ፍስሐ ጽዮን ሲሆን ትርጓሜውም የጽዮን ደስታና ተድላ ማለት ነው። በ15 ዓመታቸው ድቁናን፣ በ22 ዓመታቸውም ቅስናን ከአቡነ ቄርሎስ ተቀበሉ። ወላጆቻቸው በአምስት ቀን ልዩነት ካረፉ በኋላ በእጅጉ አዝነው ወደ ዱር ሄዱ። በዚያም ጌታችን ተገልጦ “ከእንግዲህ ነፍሳትን እንጂ እንስሳትን አታድንም፤ ስምህም ተክለሃይማኖት ይባላል” ብሎ መረጣቸው። ከዚያም ቤታቸውን ትተው ወንጌልን እያስተማሩ፣ ተአምራትን እያደረጉ፣ አብያተ ክርስቲያናትን እያሰሩ 10 ዓመት አገለገሉ። ከዚያም ወደ ደብረ ዳሞ ሄደው ከአባ ዮሐና ምንኩስናን ተቀብለው 12 ዓመት አገለገሉ። በ1267 ዓ.ም. በዓት አድርገው ለ22 ዓመት ቆመው በመጸለይ ከቆዩ በኋላ፣ አንድ እግራቸው ተሰበረ። በአንድ እግራቸውም ለ7 ዓመት በጸሎት ቆመው በጠቅላላው 29 ዓመት በጸሎት ቆዩ። በ99 ዓመት ከ10 ወር ከ10 ቀን የምድር ኑሮአቸውን ፈጽመው ነሐሴ 24 ቀን አረፉ። በዚችም ዕለት የእናታችን የቅድስት ክርስቶስ ሰምራ የዕርፍት መታሰቢያ በዓሏ ነው። ከአባታችን የአቡነ ተክለሃይማኖት ከእናታችን ከቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ምልጃና በረከት አይለየን። 🙏

@sarwite Geta Giram የተዋህዶ ልጆ
@sarwite Geta Giram የተዋህዶ ልጆ
Open In TikTok:
Region: BH
Sunday 30 August 2026 04:58:51 GMT
5360
1226
12
83

Music

Download

Comments

tigisthaile55
ማክርያና :
Bereketachew yideribin
2026-08-30 11:26:17
0
endalkkenaw6
ወርቅነሽ የለበዋ ቀበጥ :
አሜን
2026-08-30 07:02:16
0
adanuadmasu
adanuadmasu :
🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-08-30 06:15:19
0
user543_213
User890_21 :
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
2026-08-30 08:21:43
0
mesizeethiopia
mesi zeetihopia :
🙏🙏🙏
2026-08-30 07:30:23
0
meksebeee
✅🎼✈️🇩🇰🇩🇰 :
🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-08-30 06:06:37
0
shsr444
ረቡኒ :
🙏🙏🙏
2026-08-30 06:05:29
0
user3503781996227
user3503781996227 :
🥰🥰🥰
2026-08-30 05:18:01
0
user1958067698631
mesti tekle :
🥰🥰🥰
2026-08-30 05:06:00
0
user2056706825169
user2056706825169 :
🙏🙏🙏
2026-08-30 05:04:46
0
sasaw.kiflu
ቃጥላ ማርያም አንቺ ጠብቂኝ :
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-08-30 05:04:35
0
gursha.znabi
የተሰፋ ሸጋ እህት :
🥰🥰🥰
2026-08-30 11:31:45
0
To see more videos from user @sarwitegetagiram, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About