@chanmakara092: អារម្មណ៍….

Chan Makara
Chan Makara
Open In TikTok:
Region: KH
Sunday 30 August 2026 09:49:14 GMT
225
31
1
1

Music

Download

Comments

sipderman14
🪖✍️ :
Awww
2026-08-30 10:20:34
0
To see more videos from user @chanmakara092, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

አፈንዲ ሙተቂ ------
አፈንዲ ሙተቂ ------ "በኢትዮጵያ ስነ-ጽሑፍ ታሪክ ከታዩት ምርጥ የልብ ወለድ ድርሰቶች አንዱ "የታንጉት ሚስጢር" ይባላል። የዚህ መጽሐፍ ጸሐፊ እውቁ ደራሲና ጋዜጠኛ ብርሃኑ ዘርይሁን ነው። ብርሃኑ ዘርይሁን በርከት ያሉ መጻሕፍትን ለተደራሲያን አቅርቧል። በስነ-ጽሑፍ ምሁራንና በአንባቢያን በጣም የተደነቀለት ስራው ግን ይህ "የታንጉት ምስጢር" የተሰኘ ታሪካዊ ልብ ወለድ ነው። ይህ መጽሐፍ በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ በጎንደር የተነሳውን የካሳ ኃይሉ (አጼ ቴዎድሮስ) ንቅናቄ እና ከእርሱ ጎራ ጋር የተሳሰሩ የተለያዩ ገጸ-ባሕሪዎችን ኑሮ እና የሕይወት ፈተናዎች በስነ-ጽሑፍ መንገድ የሚያስቃኝ ነው። በደራሲው ምናብ የተፈጠረችው "ታንጉት" የተባለች ጉብል የመጽሐፉ ዋና ገጸ-ባሕሪ ስትሆን በገሃዱ ዓለም የሚታወቁት እቴጌ ተዋበች፣ ፊታውራሪ ገብርዬ ፣ ልጅ ጋረድ እና ሌሎች እውነተኛ ታሪካቸው ከፈጠራ ጋር ተቀይጦ የመጽሐፉ አካል ሆኗል። ------ ደራሲ ብርሃኑ ዘርይሁን በ20ኛው ክፍለ ዘመን ከተነሱትና የአማርኛን ስነ-ጽሑፍ ካዘመኑት ታላላቅ የብዕር ሰዎች አንዱ ነው። ደራሲው በርከት ያሉ መጽሐፎችን ከመጻፉ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ፕሬዚዳንትም ሆኖ ሰርቷል። ብርሃኑ በአማርኛ ስነ-ጽሑፍ በጣም የሚታወቅበት ልዩ ሪከርድ አለው። ይኸውም በታሪካችን የመጀመሪያውን የልብ ወለድ trilogy አሟልቶ የጻፈ መሆኑ ነው። "ማዕበል" የተሰኙትን ተከታታይ ድርሰቶች ታውቋችኋላችሁ አይደለምን? አዎን! ብርሃኑ ዘርይሁን "ማዕበል" የሚለውን ቃል እንደ ዋና ርእስ አድርጎ በተመሳይ ጭብጥ ላይ ያተኮሩ ሶስት ተከታታይ ድርሰቶችን አበርክቶልናል። የእነዚያ መጻሕፍት መቼት የወሎ ክፍለ ሀገር ነው። ታሪኩ በቅድመ አብዮት ኢትዮጵያ ጭሰኛው የሚኖረውን አሳዛኝ ህይወት በማስቃኘት ነው የሚጀምረው። ከዚያም በ1965 ተከስቶ ብዙዎችን ለእልቂት የዳረገውን የወሎ ረሃብ ስዕላዊ በሆነ እና ፈጠራን ከእውነታ ጋር በቀላቀለ መንገድ ያስነብባል። በመጨረሻም በ1966 የፈነዳውን የኢትዮጵያ ህዝብ አብዮት እና ከአብዮቱ ጋር ለገበሬው የተፈጠረለትን ዕድልና የተጋረጠበትን ፈተና ይተርካል። ደራሲው የመጽሐፉ ገጸ-ባሕሪዎች የሆኑትን እነ ሙሄ፣ ዘይኔ፣ ይመር፣ ፍስሐ፣ ተፈሪ ወዘተ የራሳችን ቤተሰብ አባላት እንዲመስሉን አድርጎ ነው የቀረጻቸው። ሶስቱ የ"ማዕበል" መጽሐፎች በሽፋናቸውና በንዑስ ርእስ ነው የሚለዩት። እንደቀደም ተከተላቸው የሚከተሉት ናቸው። ማዕበል-1: የአብዮት ዋዜማ ማዕበል- 2: የአብዮት መባቻ ማዕበል-3: የአብዮት ማግስት ብርሃኑ ዘርይሁን የመጀመሪያውን የኢትዮጵያ trilogy ከጻፈ ከረጅም ዓመታት በኋላ ደራሲ ፍቅረ ማርቆስ ደስታ ሁለተኛውን የሀገራችንን trilogy "ከቡስካ በስተጀርባ" ፣ "ኢቫንጋዲ" ፣ "የዘርሲዎች ፍቅር" በሚሉ ሶስት ርእሶች አበርክቶልናል። ------ አፈንዲ ሙተቂ ነሐሴ 13/2015 ------ የቴሌግራም ቻናሌ የሚከተለው ነው። You may join my telegram channel here https://t.me/afandishaHarar ----- ተማም። እናመሰግናለን። Galatoomaa

About