@clip_ajaaa: pink soldiers pada tobat, kalo mau nyoba main squid game tinggal ke Agora mall aja nihh #ThingsToDoJakarta #PlaceToGojkt #PandoraExperience #Wonderlab #SquidGameExperience

Clip ajaaa
Clip ajaaa
Open In TikTok:
Region: ID
Monday 31 August 2026 11:52:38 GMT
1662
14
0
1

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @clip_ajaaa, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

የመልአኩ የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ የንግሥ በዓል የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስና ብፁዓን አበው በተገኙበት በቢሾፍቱ ደብረ ዘይት ካቴድራል በታላቅ ድምቀት ተከበረ:: ጳጉሜን ፫ ቀን ፪ሺ፲፰ ዓ.ም #ሐመረ_ተዋሕዶ_ሚዲያ #ቢሾፍቱ — የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በቢሾፍቱ ደብረ ዘይት ቅዱስ ሩፋኤል ካቴድራል የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ቋሚ አባል እንዲሁም የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ተቋማት የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሰብሳቢ ብፁዕ አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስ ፣ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ (ዶ/ር)፣ የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ምክትል  ፀሐፊ መጋቤ ሐዲስ ቆሞስ አባ አብርሃም ገረመው፣ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሣሕል ቀሲስ ነጋሽ ሀብተ ወልድ፣ የባቱ ዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አበምኔት ሊቀ ሊቃውንት ቆሞስ አባ አትናቴዎስ ወልደ ጎርጎርዮስ፣ የሀገረ ስብከቱ የመምሪያ ክፍል ኃላፊዎች፣ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችና በርካታ ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን በተገኙበት ተከብሯል። በመጀመሪያ በካቴድራሉ አስተዳዳሪ አማካኝነት በካቴድራሉ የተከናወኑ ልዩ ልዩ የመንፈሳዊ ልማት ሥራዎችን አስመልክቶ ዓመታዊ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፤ በቀጣይም የካቴድራሉን ትምህርት ቤት ወደ ሁለተኛ ደረጃ (ሃይስኩል) የማደግና የአብነት ትምህርቱን አጠናክሮ የመቀጠል ሰፊ የልማት ዕቅዶች ቀርበዋል። በመቀጠል ብፁዕ አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ካስተላለፉ በኋላ፤ የዕለቱን ትምህርተ ወንጌል፣ ቃለ ምዕዳንና አባታዊ መመሪያ እንዲሰጡ መድረኩን ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ለብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ በመጋበዝ ሰጥተዋል። የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ «እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንዲህ ይባረካል» (መዝ. ፻፳፯፥፬) በሚለው የልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት መዝሙር መነሻነት ሰፊ ትምህርተ ወንጌል አስተምረዋል።  ብፁዕነታቸው በትምህርታቸው፦ «መባረክን ስንመለከት ሰላማችን፣ አንድነታችንና ሕይወታችን መባረክ አለበት» በማለት፣ የርዕሰ አበው የአብርሃምን ታሪክ በማንሳት ከቤተሰቡ ተለይቶ እግዚአብሔርን በማመኑ የተሰጠውን በረከት ለልጁ ለይስሐቅ፣ ይስሐቅም ለልጁ ለያዕቆብ ማስተላለፉን አብራርተዋል። አክለውም ጻድቁ ኢዮብ በብዙ ተፈትኖ እግዚአብሔር ከመከራው አውጥቶ በብዙ እንደባረከው እና በምድር ላይ አንድ ጻድቅ ሆኖ የተገኘውን ኖህን አስቦ እንደ ባረከው ገልጸዋል። በተጨማሪም በሰሬናክሬም ዘመን የነበረውን እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ ደግ፣ ትሁትና ጻድቅ የነበረውን የጦቢያን የልጁ ጦቢትን ታሪክ በማንሳት፦  ጦቢያን ሕገ እግዚአብሔርን በመፈጸም በስደት ላይ እያለ ሌሎችን ያጽናና እንደነበርና በእግዚአብሔርም ዘንድ ደስ የሚያሰኝ እንደነበረ አብራርተዋል።  «በሕይወታችንና በዘመናችን ሰጪ የነበረ ተቀባይ የሚሆንበትና ነገሮች የማይታወቁበት ዓለም በመሆኑ የጻድቁ  ሁለት ዓይኖች በታወሩ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ ልጁም በጭንቀት ውስጥ ሆና ስለ አባቷ ጸለየች፤ እግዚአብሔርም መልአኩን ቅዱስ ሩፋኤልን ልኮ ጎበኛቸው» በማለት በእምነት ውስጥ ትዕግሥትን ገንዘብ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ብፁዕነታቸው አያይዘውም፦ «በሕይወታችሁ ያለው ችግርና ፈተና ቅዱስ ሩፋኤል በረከትን ይዞ ይግባ፤ ወጥመድ በሚያጋጥማችሁ ጊዜ አለው ይበላችሁ፣ ይድረስላችሁ» በማለት አባታዊ መሻታቸውን የተመኙ ሲሆን፤ «በአዲሱ ዓመት ዋዜማ ላይ እንገኛለን፤ ዘመን የሚቆጠረው ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ የተሰጠ እድል ነው፤ ንስሐ ለመግባት፣ ወደ ሥጋወ ደሙ ለመቅረብና ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት የተሰጠ ነው» ብለዋል።  አክለውም ኢትዮጵያ ቅድስት ሀገር፣ ሕዝቧም ቅዱስ ሕዝብ በመሆኑ በፍቅር፣ በአንድነትና ከሁሉም በላይ በሰላምና በመረዳዳት መኖር እንደሚገባ አባታዊ መመሪያ ሰጥተዋል። በመርሃ ግብሩ ማጠቃለያ ላይ በካቴድራሉ ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ በጎ አድራጊዎች እንዲሁም በገዳሙ የአቋቋም ትምህርታቸውን አጠናቀው ለተመረቁ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እጅ የእውቅናና የምስጋና ሠርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል። የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ የንግሥ በዓል በአበው አባታዊ ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ በሰላም ተጠናቋል። የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት  ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ ዘገባና ፎቶ፦ ዲ/ን አየለ  #ቢሾፍቱ #ደብረ_ዘይት  #ቅዱስ_ሩፋኤል   የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት/ EOTC Broadcasting Service Agency/

About