@susuab40: #አሮጌ አምባ ቀንጠፊት ማርያም የበቀለው እሳት፣ ሰጠቃ የጠለቀው ፀሐይ እና የማይበጠሰው የትግል ጓዶቹ አደራ‼️ አማራ ሳይንት ደንሳ ልዩ ስሟ አሮጌ አምባ በተባለችው ታሪካዊ ምድር የበቀለው ቀኝ አዝማች ይታገሱ አራጋዉ ገና ከለጋነቱ ጀምሮ በውስጡ የሚንቀለቀል የወኔ ትንፋጎት፣የነብር ቁጣና የማይበገር የወንድነት አቋም የሚታይበት ትንታግ ነበር። አፄ ይኩኑ አምላክን ጨምሮ የብዙ ነገስታት መናገሻ ከነበረችዉ ታሪካዊት አምኃራ ሳይንት የበቀለዉ የዚህ ዘመን ክስተቱ ይህ አርበኛ የብዙወቻችን የማንቂያ ደወል የሆነዉ የአማራ ህዝብ ዘርፈ ብዙ ጥቃት፣የጅምላ እልቂት እና መፈናቀል በበዛበት በሰሜኑ ወረራ ወቅት ነበር። በወገኑ ላይ እየተፈፀመ የነበረዉ የማያባራ ግፍ ቢያንገፈግፈዉና የእናቶችና ህፃናት ደም እየከረፋዉ አላስተኛህ ያለዉ ይቴ የጥፋት ኃይሎች በአማራ ክልል ላይ የቃጠሎና የጥፋት እሳት በለኮሱ ጊዜ "ያ" ተንደላቆ የሚኖረዉ ምቹ የኑሮ ደረጃ ለአፍታም ሳያሳሳዉ ከልጅነት እስከ እልፈተ ሞት ድረስ በውስጡ የኖረው ሞቃት የጀግንነት ደም ወጥዉጦት ነበር የምስራቅ አማራ ፋኖን የተቀላቀለዉ። መድሎትን ቸል ብሎ ለወገን መድረስን እንደ ቅዱስ ጥሪ የቆጠረው ቀኝ አዝማች ይታገሱ አራጋዉ ለአፍታም ሳያመነታ “እኔ!” ብሎ በግንባር ቀደምትነት ተሰልፎ የወገኑ ጋሻ የጠላትም መቅሰፍትም ሆነ፣ከጁንታው ጋር በነበረው እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ የሞት ጥላ የጣለባቸውን የቃሊምና የበላጎን ምሽጎች እየሰበረ ሀያሌ ድሎችን በመቀናጀት ታሪኩን በደሙ የፃፈዉ ይታገሱ በሰሜኑ ጦርነት ማግስት ነዉረኛዉ የኦኸደድ ብልፅግናዉ ስርአት በአማራ ህዝብ ላይ ያወጀዉን የጥፋት አዋጅ ተከትሎ ከትቂት ጓደኞቹ ጋር በመሆን በአምኃራ ሳይንት ደንሳ ምድር የመጀመሪያዋን የነፃነት ጥይት አፈነዳ። ይህች ጥይት የአማራ ህዝብ በደል ያንገፈገፋቸው እልፍ አዕላፍ ጀግኖች እንዲሰባሰቡ የተለኮሰች የቁጭት እሳት ነበረች። ደቦል አንበሳዉ ቀኝ አዝማች ይታገሱ አራጋዉ የለኮሰዉ አቢወት በዉስን ቦታወችም አልተገደበም በወግድ ከአርበኛ ሀብታሙ ደምሴ፣ በመካነሰላም ከአርበኛ አብነዉ ታደሰ፣ በሳይንት አጅባር ከአርበኛ ብሩክ ሞገስ፣ በገነቴ ከህያዉ ጀግና ሳጅን አደም አሊ (አባናደዉ)፣በከላላ ከአርበኛ አለልኝ ተሰማ ጋር በመተባበር እስከ ሸዋ መራቤቴ ድረስ በአገዛዙ ኃይል ላይ የባሩድና የቦንብ ናዳ እያወረደ የትውልድ ታሪክን በአዲስ መልክ ጻፈ። ትግሉ እየተቀጣጠለ የፋኖ ድል እንደአድማስ እየሰፋ እንደቋጥኝ እያደገ ሲመጣ የህዝብ መድረኮችን እየፈጠረ ትግሉን ህዝባዊ ለማድረግ ያለ እረፍት እየታተረ በነበረበት የዛሬ ሁለት አመት ገደማ ህዝባዊ ዉይይት በሚያደርግበት ወቅት አገዛዙ አስርጎ ባስገባዉ የዉስጥ ባንዳ በተኮሳት ጥይት ነሀሴ 26 ቀን 2016 ዓ.ም በሰጠቃ ምድር የታሪኩ ማደማደሚያ ሆነ። የብልፅግናዉ ስርአት ሁለት አማራወችን እርስ በርስ በማገዳደሉ ጮቤ ቢረግጥም ጀግናዉ አርበኛ ቀኝ አዝማች ይታገሱ አራጋዉ ባፈነዳዉ አቢወት እንዳሸን የተፈለሆኑ አባላት ግን በዛዉ ቅፅበት ነበር የይቴን ገዳይመስቀል ግንባሩን በማለት ገዳይ ሞትን ሞታት-ጀግናዉ ግን አረፈ፣ እኩል አይጠራም ላገር የሞተና- ሀገር የዘረፈ።የተሰኘች ስንኝን በማቀንቀን ስለሀገሩ ሲል ዉድ ነፍሱን የገበረዉን ሀቀኛ አርበኛ በዚች ስንኝ ለዘላለም እንድዘከርና በፅናት አላማዉን እንደሚያስቀጥሉ ቃል የገቡት።ዛሬ አርበኛ ቀኝ አዝማች ይታገሱ አራጋዉ በአካል የለም፤ በስሙ ግን በየቀኑ ድል አለ የእሱ ታሪክና ያስቀመጠው ራዕይ ፈጽሞ አይሞቱም። አሁን ጥሪው ወደ ትግል ጓዶቹ ነው። ጀግናው የወደቀው ለአማራ ሕዝብ ነፃነት ነው። የትግል ጓዶቹ ሆይ! ይቴ ያስቀመጠው አደራ በእኛ ትከሻ ላይ ይገኛል። እሱ የጀመረውን፣ በደሙ የቀደደውን የነፃነትና የክብር መንገድ ሳናናዉጥ በመጓዝ የእሱን ታላቅ ራዕይ እስከ መጨረሻው ማሳካት የነፍስም የሥጋም ታሪካዊ ኃላፊነታችን ነው። ታሪኩ አይረሳም፣ አደራውም አይበጠስም። አፋብን ምኒልክ 1ኛ ዕዝ 15ኛ ኮር ህ/ግንኙነት መምሪያ ነሀሴ 25/2018 ዓ.ም
ŠŬŠŨ አማራዊት 💚💛❤️
Region: SA
Monday 31 August 2026 13:54:48 GMT
Music
Download
Comments
ባፈቀረ አልቀናም ባመሸለት እንጅ :
ወይኔ😭😭😭😭😭😭😭
2026-08-31 21:42:47
0
ሀይሚ የመካነ ሰላሟ 💚💛❤💪👈 :
እሣታችን😭😭😭
2026-08-31 18:27:23
0
መልካም ሴት 👸ጥበብ ሸማ 👗🛍👈 :
😢😢😢😢@
2026-08-31 15:19:02
0
[AMHARANESSCOMESFRiST 💚💛❤] :
🥺🥺🥺
2026-08-31 18:20:06
0
እርግቧ 💚💛❤👈 :
🥺🥺🥺🥺🥺
2026-08-31 16:46:39
0
ጀማል የቦረናው ፋኖ :
😭😭😢
2026-08-31 15:05:22
0
ጀማል የቦረናው ፋኖ :
💪💪💪
2026-08-31 15:05:11
0
እማራ :
💪💪💪😭😭😭
2026-09-01 11:17:12
0
To see more videos from user @susuab40, please go to the Tikwm
homepage.