@guragign: በ1930 ዓ.ም በጣልያናዊው የተሰራው የዋቤ ታሪካዊ ድልድይ እንዴት ተሰራ! #ታሪክ_የኋሊት ይህ የምታዩት ድልድይ ከመሰራቱ በፊት ወንዙ በሞላ ወቅት ዋና የሚችሉና ሌሎችንም የሚያሻግሩ ሶስት ታዋቂ ዋናተኞች ነበሩ እነሱም 1,ኬርጋ የንፉወ፣ 2,ሟራጋ ኬርስማ፣ 3,ኩተምበር፣ዋናዎቹ ነበሩ። በወቅቱ በዋና ስራ ከበርቴ ሆነዋል። ጣልያን ወልቅጤ ከተማ ገባ። ካፒቴን ካርፔ የተባለ ጣልያናዊ በክረምት ወራት በአንዱ እሁድ ቀን ወደ እምድብር ሄዶ የካቶሊክ ቄሶችን ለማግኘት ወደ ዋቤ ወንዝ ጉዞ ጀመረ። እዚያ እንደደረሰ የዋቤ ሙላት ወደመጣበት ወልቂጤ ከተማ መለሠው። የከተማውን ታላላቅ ሰዎችን አሰባስቦ ከዚህ ቀደም ህዝቡ በምን እንደሚሻገር እና እርሱም በምን መሻገር እንዳለበት ጠየቀ። ከላይ ስማቸው የጠቀስናቸው ድንቅ ዋናተኞች እንዳሉ ተነገረው።ዋናተኞችን አስፈልጎ ካስመጣቸው በኃላ አስከትሏቸው ወደ ዋቤ ወረደ። ካፒቴን ካርፔ ዋናተኞቹ ብዙ መንገደኞችንና ጓዛቸውን በዋና ሲያሻግሩ በአድናቆት ተመለከተ። በዚህም እጅጉን በመደሰቱ መጠነኛ ገንዘብም ሸለማቸው። ከሶስቱ ኩተምበር የተባለው ቀልጣፋ እንደሆነ ተገነዘበ።በእድሜም ከሌሎቹ ትንሹ እሱ ነበር። ኩተምበር ትምባሆ በወረቀት ጠቅልሎ ያጨሳል።የአልኮል መጠጥም ይጠጣል። ቀልጣፌው ከዚያን ግዜ በኃላ ወደ ወርቂጥየ ወጣ ማለት አዘወተረ።ጣሊያኖቹ ትንሹ(ፒኮሎ) የሚል ስም አውጥተውለት በጣም ቀረቡት።ጣልያንኛም እያወቀ መጣ።ከነሱ ጋር በቋንቋቸው ያዋራል።የመንደሩ ወሬ አንድ ሳይቀር ይነግራቸዋል። ካፒቴን ካርፔ በየግዜው በደራሽ ውሃ የሚወሰደው ፣ በድልድይ እጦት የሚሠቃየው፣....ህዝብ ችግር ለመገንዘብ በመቻሉ ፣ለራሱም ጥቅም ሲልም በአጭር ጊዜ ውስጥ ጥናትና ፕሮግራም አውጥቶ፣ ብረታ ብረትና የእንጨት ጣውላ ከውጭ አገር አስመጥቶ በጋሶሬ ቀበሌ ካሚዮን ማሻገር የሚችል ዘመናዊ ድልድይ ስራ ተጀመረ። ጣልያን በ1930 ዓ.ም ድልድዩን ከሠራው በኃላ ሰው በላውና ንብረት ጨራሹ ዋቤ በጣላት ቋሚ ስራ ተቀረፈ። ዳሩ ግን ጥቅም ያገኙ የነበሩ ዋናተኞች ስራ ፈቱ። ከዓመት አመት ኑሮአቸው ቀዘቀዘ፣ ሀብታቸው እየመነመነ ሄደ።"ይንቀልህ"ሲሉም ረገሙት። ጣልያንም ይህን ተገንዝቦ በዓል በመጣ ቁጥር የገንዘብ ድጎማ ያደርግላቸው ነበር። #ጉራጌን_እንወቅ ሰላም❤🙏
ጉራጌን እንወቅ❤🤝
Region: ET
Monday 31 August 2026 20:38:34 GMT
Music
Download
Comments
ያብ ሸመነ ኤቺ :
በጀነራል ወልደስላሴ በረካ ምክንያትነዉ የተሰራዉ
2026-09-01 17:12:27
1
black cityzns kdb 17 my 🐐🐐 :
መኪናውን ያወቀው እስኪ
2026-09-01 10:21:11
0
Abdi akmel :
መረሳት የሌለበት ትዝታ ( ያልተፈተነ አያልፍም )
2026-09-02 16:26:54
0
tohid seman @tohid seman tohid :
ዋቤ
2026-09-02 05:42:18
0
ዘ/ት አበባ የተክልዬ ልጅ💜👌 :
ጉብሬ መውጫ መንገድ ነዎ?
2026-09-01 08:52:34
1
Ebrahim ማንቼዉ :
😂😂Bdru
2026-09-01 11:42:30
0
ገብሩ online መዝናኛ :
ዌቤ ባውለታችን
2026-09-02 04:13:40
0
M. D .dada :
የን ውብ ዘመን ወዴት ሔደ?
2026-09-01 08:19:23
0
@ hana. bab :
ዋ
2026-09-01 12:54:42
0
demis tesema :
ዋቤ ድልድይ
2026-09-01 19:05:23
1
user80011441246246 :
ዋቤአገራቸኝ፣ኩሩ፣እኛጉራጌዎች❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
2026-09-01 07:17:36
0
Kalabi fikadu@merkeb# :
ማን ነው የዋቤ ድልድይ የሰራው😊
2026-09-01 06:00:41
1
E&b Auto Tapisery1 :
የሁሉም ጉራጌ ባለውለታ ድልድይ
2026-09-02 17:45:27
0
sura yegebreal lij :
🥰🥰🥰
2026-08-31 21:03:12
0
ቡርሳዊ :
👍👍👍
2026-09-01 17:28:29
0
Baha Murad :
🥰🥰🥰
2026-09-01 17:57:24
0
abdra የወልቅጤውair born :
🥰🥰🥰
2026-09-01 13:27:02
0
mohammed rashed :
🥰🥰🥰
2026-09-01 08:28:18
0
ማርያም ማርያም :
🥰🥰🥰
2026-09-01 08:36:12
0
Asefach :
👍👍👍👍👍👍
2026-09-01 06:32:52
0
Asefa(አሴ ጃክ )ራሱ የእናቱ ልጅ :
❤️❤️❤️
2026-09-01 06:26:58
0
suzi :
🥰🥰🥰🥰
2026-09-01 18:06:15
0
cherent :
🥰🥰🥰🥰🙏🙏🙏
2026-09-02 18:16:25
0
To see more videos from user @guragign, please go to the Tikwm
homepage.