@tsega_key: ሰሜ ፀጋአብ ይባላል የተወለድኩት ከክርስቲያን ቤተሰብ ነው ያደኩት በ ቸርች ውስጥ ነው ከልጅነቴ የሙዚቃ ፍቅር ነበረኝ እናም ይሄን ያየው የቸርቹ keyboardist ጠርቶ አናገረኝ /ላስተምርህ አለኝ በጣም ነበር ደስ ያለኝ ህልሜን መኖር ልጀምር ነው በህልሜ ያለው ሁሉ ይመስለኛል እናም ማይሆን የለም እኔም መማር ጀመርኩ family ይሄን አይቶ የ ሙዚቃ ትምህርት ቤት አስገባኝ በደንብ ክላሱን መከታተል ጀመርኩ ስማር ጎበዝ ነበርኩ ሙዚቃ መማር ስጀምር ገና 13 አመቴ ነበር የማያልቅ ነገር የለም ትምህርቴን ጨረስኩ ከዚ በኋላ ነበር ፈተናዬ ሚጀምረው ያው እንደማንኛውም keyboardist ወደ ቸርቼ ተመለስኩ በዚያ ሰአት keyboard መንካት በጣም ከባድ ነበር በብዙ ጊዜ አንዴ እነካ ነበር እሱንም ለትንሽ ደቂቃ በዚ ሁሉ ብዙ ፈተናዎች ነበሩ ከኔጋ የተማሩት ጓደኞቼ ከኔ በጣም ራቁ ያን ሳይ በራሴ ተስፋ መቁረጥ ጀመርኩ የምር በጣም ከባድ ጊዜ ነበር ለኔ በራስ መተማመኔን እያጣውት መጣው በዚ ሁሉ ሚገርመው ከዚ በፊት ስማር የሚያቁኝ ጓደኞቼ እኔን በጣም አተልቀው ነበር የሚያዩኝ ምን ልበላቹ የዚ ደሞ በጣም ልብ ይሰብራል 💔 እንደዚ እያለው 2 አመት ሞላኝ አሁንም ግን keyboardun አልተውኩትም በትንሹም ቢሆን ነገሮች እየተስተካከሉ መጡ ችግሩ ግን ብዙ ማስተካከል ያለብኝ ነገሮች ነበሩ /ማሻሻል የነበሩብኝ ነገሮች ነበሩ ያው 2 አመት ሙሉ አባክኚያለው keyboard ደሞ በደንብ የግል ስራ ይፈልጋል እና አሁንም እንደ አዲስ መጀመር ነበረብኝ በጣም ከባድ ነበር ለኔ ያ ጊዜ አስቡት ከኔ በኋላ የጀመሩት ከኔ የተሻሉ ሆነዋል ከባድ ነበር ህመሙ ይበልጥ የሚጎዳው ደሞ ብቸኛ መሆኔ ነው ግልፅ ሰው አይደለውም ያው አማራጭ ስላልነበረኝ ድጋሚ ከ 0 ልጀምር እራሴን አሳመንኩ church ተተኪ keyboardist ማፍራት አለብን ብላ አስተማሪ ቀጠረተለች ከእኔ ጋር 4 ልጆች መማር ጀመርን የ አስተማሪዬ ስም ቢኒያም ይባላል በጣም ጎበዝ keyboardist ነው ለኔ ደሞ መካሪዬ አባቴም ጭምር Keyboardist መሆን ብዚ ፈተናዎች እንዳሉት ታሪኩን እየነገረ አስተማረን ከነገረን ነገሮች ሁሉ ማልረሳው keyboardist ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሄር መጠቀሚያ መሳሪያ ሁኑ መንፈሳዊ ሂወታቹ ላይ ስሩ ይሄ ለኔ በጣም ትልቁ ትምህርቴ ነበር ከዚያ church በግሌ መስራት ጀመርኩ ያው እያሻልኩ እያሻልኩ የቸርቹ worship team ማስጠናት ጀመርኩ ከዛ የሆነ ቀን የቸርቹን ትንሹን ኳየር እሁድ ጠዋት ላይ ያዝኩላቸው ለኔ በጣም ትልቁ ቀን ነበር ሰው ሁሉ ጎበዝ አለኝ መድረክ ላይ ተፀለየልኝ የኔ special day ነበር እናት እና አባቴ ፊት ቀና አልኩ ከዚያ በኋላ በትንሹ እድል አገኝ ጀመር የሆነ ቀን ሁሉም የቸርቹ keyboardist ስለሌለ እኔን ያዝ አሉኝ የቸርቻችን ትልቁ ኳየር በጣም ነበር ደስ ያለኝ ለሊቱን ሙሉ ስዘጋጅ አደርኩ ነጋ ሄድኩ ኳየሩን አስጠናዋቸው ጨረሱ ወደ ትልቁ አዳራሽ ከገቡ በኋላ የኳየሩ መሪ መቶ የሆነ አዲስ ኪቦርዲስት ስለጠራን እሱ ይያዝልን አለኝ ምን ልበላቹ ኪቦርዱ ጋር በድን ሆኜ ቆምኩ እሺ ብቻ ነበር ያልኩት ከዛ ከቸርች ወጣሁ ለኔ በጣም ከባዱ ቀን ነበር መንገድላይ ብቻዬን እያለቀስኩ ወደ ቤቴ ሄድኩ 🥺💔 በራሴ ሙሉ በሙሉ ተስፋ ቆረጥኩ family ተሰብስበው ያፅናኑኛል ብዙ ሰው መከረኝ እንዳይደብራቸው እሺ አትጨነቁ ደና ነኝ አልኳቸው ከዛ በኋላ ለብዙ ጊዜ እራሴን ማግኘት አቃተኝ እየቀነስኩ መጣው በራስ መተማመኔን መመለስ አቃተኝ ግን ዝም ብዬ ብቻዬን እሰራ ነበር ሰው ምን ሆነህ ነው እየቀነስክ እኮ ነው አሻሽል አለኝ የሂወቴ ከባዱ ጊዜ ነበር የሆነ ቀን ክፍሌ እያለቀስኩ ፀለይኩ የምር በረታው ❤️🩹ከእግዚአብሄር ጋር ድጋሚ ወደ ፊት ነገሮች እየተስተካከሉ መጡ እግዚአብሄር ይመስገን አሁን All most 7 አመት ሞላኝ ከትላንትናዬ እሻላለው አሁንም ከእግዚአብሄር ጋር ወደ ፊት ከ እግዚአብሄር ጋር ዝቅ ከእግዚአብሄር ጋር ከፍ🥹❤️🩹
Tsega_key
Region: ET
Tuesday 01 September 2026 21:42:52 GMT
Music
Download
Comments
bini +ben :
Hulumga Yi Ale inde ?🥺🥺 Manm bihon
tinkiro kegeta gar hono Exercise(training ) 👈 Madreg newu plus Agilgilot silhone Wugiya ayikerem
2026-09-15 14:59:11
2
Fikru Jemal :
የኔ አባት አይዞህ 🙏 ይህንን ኮሜንት ከመጻፌ በፊት ጽሑፉን አንብቤ እያለቀስኩ ነበረ በጣም ነው fill ያደረኩት 🙏 እንኳን እግዚአብሔር ያዛክ ከዚህ በኃላ ያለፈውን አታስብ ወደ ፊት ቀጥል እወድሃለሁ ❤️
2026-09-05 06:09:51
12
Teneshua :
ወንድሜ ከባድ ነው እኔ ከህፃንነቴ ጀምሮ ለሙዚቃ የተለየ ፍቅር ነበረኝ ግን ማን አስደርሶኝ እንደምንም ብዬ ኳየር ገባው እና የኳየሩ ሊደር ኪቦርኪስቱ ነበር እና ኪቦርድ መማር የምትፈልጉ ሴቶች መማር ትችላላቹ እኔን አናግሩኝ አለ እኔ መማር ፈልጋለው ስለው አንቺን አላስተምርሽም አለኝ ከዛ ሌሎቹን ማስተማር ጀመረ እኔን ብቻ ለይቶ አላስተምርም አለኝ እና የገና ቀን ደሞ 3 ወር ምናምን መዝሙር አጥንተን የገና ቀን አንቺ አትቆሚም አለኝ 😭
ኳየር 2ወር ከእነሱ ጋር አጥንቼ ልበሱ የተባለውን ልብስ በስንት መከራ ከሰው ተውሼ ለብሼ መጥቼ ዛሬ አንቺ አትቆሚም ይሉኛል የኳየር ቦታ ተቀምጬ እነዙ መድረክ ላይ ወተው ሲዘምሩ አያቸዋለው ሲፈልጉ ደሞ መድረክ ላይ እየዘመርኩ ፓስተር ነው ያዘዘው ብለው ማይኩን ይቀሙኛል መድረክ ላይ ደርቄ ቀራለው 🥺🥺
ብቻ አሁን ቸርች የሚባል ጴንጤ የሚባል አስጠልቶኛል ቸርች ከሄድኩኝ 4 አመት ሆኖኛል መዝሙር እራሱ ጠፍቶብኛል እናት ብቻ ነው ያለኝ እሷ በጌታ ነች ህይወት የፈተነኝ አንሶኝ እነሱ ተጨመሩብኝ እናቴም በእኔ ምክንያት ቸርች ከሄደች ቆየች😭😭😭😭
2026-09-11 22:04:36
6
Fitsum Solomon🎵🎷 :
Hulachenem yehen menged kemsenewal Egzabeher hulunem yeteshale yadergewal emenegn🙏🙏
2026-09-05 19:11:03
2
dagi :
እኔን guitar አስተምረኝ ብዙ አላስቸግርህም ከ እግዚአብሔር ታገኘዋለህ ተስፍ ቆርጭ ነው ይሄን ሳነብ ለመመለስ ያሰብኩት 🙏
2026-09-08 19:47:25
3
GRACIA :
Same to my Story
2026-09-04 04:36:18
1
Megersa Feyisa :
ወንድሜ ጌታ አብዝቶ ይባርክህ ዬኔም ተረክ ልክ እንደተ ነበር ማያልፍ ነገር የለም
2026-09-09 15:55:55
1
Hope✌️🤞🥰 :
ስሜን ብቻ ነው ያልጠራሃው እንጂ የኔን ታሪክ የነገርከው🥺 አለን አሁን ግን እግዚአብሔር በሰው ሁሉ ፍት ሞገስ ሰጠኝ🙏
2026-09-05 08:25:41
6
Abela :
o bexam gerami new lb ynekal berta
2026-09-06 05:52:02
2
musican yisak🎹🥁🎤 :
yen abat wode fite🥰🥰
2026-09-06 16:08:26
1
⚜️yoska⚜️ :
1 advice lsteh kante teshye adelem and mtakewn tawaki musican teyk astedadegachewn moral lihonh yichlal bye new bmkniyat new hulum fetenaoch eshi geta liyaberetah new engam endezaw nen berta tlk stage lay entebkahalen 🙌🏽
2026-09-03 05:15:58
0
yab :
yenem tark new
2026-09-06 08:54:28
2
beki&fiker :
ywmigerm new yene tarik meslogn.... berta gena bebizu tichemirale b/c ene silalefkubet degmo tesfa alek
2026-09-05 12:51:44
2
Biruk 🎹 :
ያምር በርታ የሁላችንም ፈተና ነው እኔ በመድረክ ላይ ተቀምቼ አቀለወ ግን ያ ሁሉ አልፎ አሁን ጥሩ ላይ ነኝ
2026-09-07 04:29:12
2
ⓑbin family :
😍 የእኔ አባት በርታልን በትክክለኛው መንገድ ላይ ስትሆን ፈተና ይበዛል አይዞህ እግዚአብሔር ደግሞ በፈተናው መሀል መውጫ ያዘጋጃል 😍 እንወድሃለን በርታልን 😍
2026-09-05 18:49:18
3
Tame Ye Cj :
dess yemil new tebarikealew
2026-09-05 19:43:53
1
musician beki :
አረ በጌታ ለካ ሁሉመም ጋር ነው..
2026-09-08 19:40:05
1
Aste gezehagn :
ሙዝቃ ላይ ያለዉ ፍቅር ምን አይነት ፍቅር እንዳለ አላዉቅም ግን ከባድ ነዉ
እግዝአብሄሔር እንኳን ርዳሄ😍❤😍
2026-09-06 23:20:34
1
habtamu habte :
ያሳለፍከው ታሪክ ቁጭ የኔ መሰለኝ፣ና እግዚአብሔር የመረጡትን በማኔኛው መንገድ ያሳልፋል 🙏🙏🙏💗💗💗
2026-09-06 20:38:53
1
Bini Degela :
tsegi Tebarek . Bertalign aba. Alifebetalew ahunim eyalefkubet new. Atifra malefun. Egzabiher xatochihin Self yastemirachew. Madegih ayiqerim ena Tesfa atiqurex aba. Blessed aba.
2026-09-04 07:44:55
4
Efi Ha :
ስሜን አልጠራህም እንጂ የኔን ታሪክ የነገርከው
2026-09-04 08:51:57
2
yared zeleke :
Ante gobez lij beretalegn 🙌🔥
2026-09-04 18:48:57
2
Ghost :
አንተ ቢያንስ በቸርች ነዉ ያደከዉ እኔ ግን family አማኝ አይደሉም ከቤተሰብ ጋር ነዉ ምኖረዉ በጣም እየተፈተንኩ ነዉ ምን እንደማረግ አላቅም ዛሬ እሁድ ነዉ church ባገለግል ደስ ባለኝ ግን🥺🥺
2026-09-06 09:21:22
2
🅁🄾🄱🄸 🇪🇹🇨🇦 :
ያለፍኩበት ታሪኬ ሲነበብ 🥺
2026-09-04 19:30:15
3
Tariku Tamuno :
wudu leja Tankra Hesbe sellke Bart Gobze
2026-09-02 05:24:03
1
To see more videos from user @tsega_key, please go to the Tikwm
homepage.
© 2021-2026 TikWM. All rights reserved.