@engineer_leul_befekadu: በቃል የተሰጠህን variation ትፈጽማለህ ወይስ አትፈጽምም? መልስህ ትክክል ካልሆነ ገንዘብህን ልታጣ ትችላለህ። ታሪኩ በሳይት ላይ በየእለቱ ሊከሰት የሚችል ነው። Assistant RE መጥቶ "የfootingun rebar detail እንደዚህ ቀይሩት" ብሎ በቃል ይናገራል። ወረቀት የለም፣ ደብዳቤ የለም፣ ፊርማ የለም። ኮንትራክተሩ ግን መመሪያውን ተቀብሎ ስራውን ይሰራል፣ ተጨማሪ ወጪ ያወጣል፣ እና ኋላ ላይ claim ያስገባል። ኢንጂነሩ ግን በቀላሉ ውድቅ ያደርገዋል "ማንም በጽሑፍ የሰጠው መመሪያ የለም" ይላል። ጥያቄው እዚህ ጋር ይነሳል ትክክል ማን ነው? እና ኮንትራክተሩ ያ መመሪያ በተሰጠበት ቅጽበት ምን ማድረግ ነበረበት? ብዙ ሰዎች ስህተት የሚሰሩት እዚህ ጋር ነው፣ ስለዚህ ትንሽ ጠልቀን እንየው። ውሉ የሚተዳደረው በFIDIC Red Book (1987) ከሆነ መልሱ የሚገኘው clause 2.5 ውስጥ ነው። ይህ clause የሚናገረው ስለ ኢንጂነሩ(The Engineer) መመሪያዎች አሰጣጥ ነው እና ብዙ ሰዎች የተሳሳተ ግንዛቤ ይዘውበታል። "በጽሑፍ ካልተሰጠኝ መከተል የለብኝም" የሚል ግምት በጣም የተለመደ ነው ይህ ግን ስህተት ነው እናም ኮንትራክተሩን ውድ ዋጋ ሊያስከፍለው ይችላል። እውነታው ምንድን ነው? clause 2.5 መመሪያዎች "በጽሑፍ ሊሆኑ ይገባል" ይላል። ይህ ግን በጽሑፍ ካልሆኑ ዋጋ የላቸውም ማለት አይደለም REው በቃል order ቢያደርግም እንኳ ኮንትራክተሩ አሁንም እንዲሰራ ይገደዳል። ለምን? ምክንያቱም ፕሮጀክቱ በየእለቱ የሚንቀሳቀስ ስለሆነ ውሳኔዎች ብዙ ጊዜ በስፍራው ላይ በፍጥነት ያስፈልጋሉ ስራው እስኪቆም ድረስ ወረቀት መጠበቅ አይቻልም። ችግሩ ግን አለመታዘዝ ላይ ሳይሆን ራስን አለመከላከል ላይ ነው። ኮንትራክተሩ ማድረግ የነበረበት መመሪያውን አለመቃወም ብቻ ሳይሆን ወዲያውኑ ራሱን መከላከል ነበረበት። ይህም ማለት በ7 ቀናት ውስጥ የቃል መመሪያውን በደብዳቤ ማረጋገጥ ነበረበት "እንዲህ የሚል መመሪያ ተሰጥቶኛል፣ በዚህ መሰረት እየፈጸምኩ ነው" ብሎ በጽሑፍ መላክ ነበረበት። ይህን ካደረገ በኋላ ኢንጂነሩ በዚያው 7 ቀናት ውስጥ በጽሑፍ ካልተቃወመ የማንም ፊርማ ሳያስፈልገው ህጉ ራሱ መመሪያውን approved እንደሆነ ይቆጥረዋል። ይህ "deemed approval" የሚባለው መርህ ነው እና ብዙ ኮንትራክተሮች የማያውቁት ጠንካራ የመከላከያ መሳሪያም ነው። አንድ ተጨማሪ ወጥመድም አለ ብዙ ጊዜ ችላ የሚባል "Assistant" የሚባለው ሰው ማንነት ራሱ ጥያቄ ውስጥ መግባት አለበት። በFIDIC ውል መሰረት Variation የማዘዝ ስልጣን ያለው ኢንጂነሩ ራሱ ወይም ኢንጂነሩ በጽሑፍ ስልጣን የሰጠው ተወካይ ብቻ ነው። Assistant RE ግን በዋንኛነት የ quality inspection ስራ ላይ እንጂ የመወሰን ስልጣን የለውም። ስለዚህ ከዚህ ታሪክ ውስጥ ያ መመሪያ ራሱ ከጅምሩም በትክክለኛ ስልጣን ያልተሰጠ ሊሆን ይችላል፣ ይህም ሌላ ደረጃ ውስብስብነት ይጨምራል። #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #fyp #construction #fypシ
Lula onsite
Region: ET
Wednesday 02 September 2026 15:11:06 GMT
Music
Download
Comments
Firaol👷♂️ :
Site book
2026-09-03 17:12:25
5
Mati ARSENAL :
ቀላል ከሆነ እና ካሳመነኝ
2026-09-03 16:40:43
1
Blacky :
በፍፁም አይደረግም !
በ construction ስራ ውስጥ ቀላል ወጪ የለም!
2026-09-03 16:48:58
1
ቀerefa :
caption🔥
2026-09-09 09:45:47
1
paradox :
ende sirawu type yileyayal bay negn example bizu risik yelelewu change order kehone ena consultant bekelalu accept arigewu payment mikafelu kehone variation orderun oral bihon chigir yelewum bayinegn..
2026-09-02 16:29:15
1
Henok Amen :
ግደለኝ
2026-09-03 13:13:23
0
seni799 :
አልፈፅምም site book order
2026-09-08 06:49:05
1
Bahiru :
ንክች አላረግም፤ ቢያንስ ሳይት ቡክ ላይ ሳላስፈርም!
2026-09-04 09:23:51
0
Bekalu :
እንደሁኔታው
2026-09-04 14:44:47
0
ERTA CON :
አልሰራም እንኳን በቃል በፕላን የማይሆን ካየሁ አልሰራም
2026-09-05 12:29:06
0
Binaldo :
👏
2026-09-03 10:06:24
1
La pulga, the 🐐/👽. :
👌👌👌
2026-09-03 14:16:20
1
To see more videos from user @engineer_leul_befekadu, please go to the Tikwm
homepage.
© 2021-2026 TikWM. All rights reserved.